የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lff ትምህርት 14
  • አምላክ የሚቀበለው አምልኮ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ የሚቀበለው አምልኮ
  • ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጠለቅ ያለ ጥናት
  • ማጠቃለያ
  • ምርምር አድርግ
  • በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ላይ መገኘትህ የሚጠቅምህ እንዴት ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ለጉባኤህ ድጋፍ ማድረግ የምትችልባቸው መንገዶች
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሥራና ስለ ገንዘብ ምን ይላል?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
lff ትምህርት 14
ምዕራፍ 14. የይሖዋ ምሥክሮችና እንግዶች በጉባኤ ስብሰባ ላይ ሲዘምሩ

ምዕራፍ 14

አምላክ የሚቀበለው አምልኮ

በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው

ከዚህ በፊት ባለው ምዕራፍ ላይ እንደተመለከትነው አምላክን የሚያስደስቱት ሁሉም ሃይማኖቶች አይደሉም። ሆኖም ፈጣሪያችንን እሱ በሚፈልገው መንገድ ማምለክ እንችላለን። እሱን የሚያስደስተው “አምልኮ [ወይም፣ ሃይማኖት]” የትኛው ነው? (ያዕቆብ 1:27 የግርጌ ማስታወሻ) መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምር ተመልከት።

1. አምልኳችን በምን ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይገባል?

አምልኳችን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይገባል። ኢየሱስ ወደ አምላክ ሲጸልይ “ቃልህ እውነት ነው” በማለት ተናግሯል። (ዮሐንስ 17:17) አንዳንድ ሃይማኖቶች በአምላክ መንፈስ መሪነት በተጻፈው ቃሉ ማለትም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን እውነት ችላ ይላሉ። ይህን እውነት በሰዎች ትምህርትና ወግ ተክተውታል። ይሖዋ ግን ‘ትእዛዙን ገሸሽ በሚያደርጉ’ ሰዎች ደስ አይሰኝም። (ማርቆስ 7:9⁠ን አንብብ።) በሌላ በኩል ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ስንመራና በውስጡ የሚገኘውን ምክር ተግባራዊ ስናደርግ ልቡን ደስ እናሰኛለን።

2. ይሖዋን ልናመልክ የሚገባው እንዴት ነው?

ይሖዋ ፈጣሪያችን እንደመሆኑ መጠን ሊመለክ የሚገባው እሱ ብቻ ነው። (ራእይ 4:11) እሱን ብቻ መውደድ ይኖርብናል፤ እንዲሁም ምንም ዓይነት ቅርጻ ቅርጽ ወይም ምስል ሳንጠቀም ልናመልከው ይገባል።—ኢሳይያስ 42:8⁠ን አንብብ።

አምልኳችን “ቅዱስና በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው” መሆን ይኖርበታል። (ሮም 12:1) ይህም ሲባል እሱ ባወጣቸው የሥነ ምግባር መሥፈርቶች መመራት አለብን ማለት ነው። ለምሳሌ ያህል፣ ይሖዋን የሚወዱ ሰዎች እሱ ከጋብቻ ጋር በተያያዘ ያወጣውን መመሪያ ሊቀበሉና ሊታዘዙ ይገባል። በተጨማሪም ሲጋራ እንደማጨስ፣ ጫት እንደመቃም እንዲሁም ዕፆችን ወይም አልኮልን አላግባብ እንደመጠቀም ካሉ ጎጂ ልማዶች ይርቃሉ።a

3. ከሌሎች ጋር አብረን ይሖዋን ማምለክ ያለብን ለምንድን ነው?

በየሳምንቱ የምናደርጋቸው ስብሰባዎች “በጉባኤ ይሖዋን [የምናወድስበት]” አጋጣሚ ይሰጡናል። (መዝሙር 111:1, 2) አምላክን የምናወድስበት አንዱ መንገድ የውዳሴ መዝሙር መዘመር ነው። (መዝሙር 104:33⁠ን አንብብ።) ይሖዋ በስብሰባዎች ላይ እንድንገኝ ያዘዘን ስለሚወደንና እንዲህ ማድረጋችን ለዘላለም በደስታ የምንኖርበት አጋጣሚ እንደሚከፍትልን ስለሚያውቅ ነው። በስብሰባዎች ላይ ስንገኝ እርስ በርስ መበረታታት እንችላለን።

ጠለቅ ያለ ጥናት

ይሖዋ ምስሎችን ተጠቅመን የምናቀርበውን አምልኮ የማይቀበለው ለምን እንደሆነ እንመረምራለን። በተጨማሪም ይሖዋን ማወደስ የምንችልባቸውን ዋና ዋና መንገዶች እንመለከታለን።

4. ምስሎችን ለአምልኮ መጠቀም የለብንም

ምስሎችን ለአምልኮ መጠቀማችን አምላክን እንደሚያሳዝነው እንዴት እናውቃለን? ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

ቪዲዮ፦ አምላክ ምስሎችን ተጠቅመን የምናቀርበውን አምልኮ ይቀበላል? (3:26)

እስራኤላውያን በሲና ተራራ ግርጌ ለወርቅ ጥጃ አምልኮ ሲያቀርቡ  2. መቁጠሪያ የያዘ አንድ ሰው በድንግል ማርያም ምስል ፊት ሲጸልይ
  • በጥንት ዘመን ከአምላክ ሕዝቦች መካከል አንዳንዶቹ ጣዖት ተጠቅመው አምላክን ለማምለክ መሞከራቸው ምን ውጤት አስከትሏል?

አንዳንድ ሰዎች በአምልኳቸው ላይ ምስሎችን መጠቀማቸው ይበልጥ ወደ አምላክ እንዲቀርቡ እንደሚረዳቸው ይሰማቸዋል። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን፣ እንዲህ ማድረጋቸው ወደ አምላክ እንዲቀርቡ ይረዳቸዋል ወይስ ከአምላክ ያርቃቸዋል? ዘፀአት 20:4-6⁠ን እና መዝሙር 106:35, 36⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ሰዎች የትኞቹን ነገሮች ወይም ምስሎች ለአምልኮ ሲጠቀሙ ተመልክተሃል?

  • ይሖዋ ምስሎችን ለአምልኮ ስለ መጠቀም ምን ይሰማዋል?

  • አንተስ ምስሎችን ለአምልኮ መጠቀም ተገቢ ይመስልሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

5. ይሖዋን ብቻ ማምለካችን ከሐሰት ትምህርቶች ነፃ ያወጣናል

ይሖዋን በትክክለኛው መንገድ ማምለክ ከሐሰት ትምህርቶች ነፃ የሚያወጣን እንዴት ነው? ቪዲዮውን ተመልከቱ።

ቪዲዮ፦ እውነት ነፃ ያወጣል (5:16)

መዝሙር 91:14⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ይሖዋ እሱን ብቻ በማምለክ እንደምንወደው የምናሳይ ከሆነ ምን እንደሚያደርግልን ቃል ገብቷል?

6. በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ መገኘት የአምልኳችን ክፍል ነው

በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ መልስ ስንመልስና መዝሙር ስንዘምር ይሖዋን እናወድሳለን እንዲሁም እርስ በርስ እንበረታታለን። መዝሙር 22:22⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • በስብሰባዎች ላይ የሚሰጡትን ሐሳቦች መስማት ያስደስትሃል?

  • አንተስ መልስ ለመመለስ እንዴት መዘጋጀት እንደሚቻል ማየት ትፈልጋለህ?

አምላክን በትክክለኛው መንገድ ማምለክ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ እየተማረች ያለችን ሴት የሚያሳዩ ሥዕሎች፦ 1. በጉባኤ ስብሰባ ላይ ለአምላክ የውዳሴ መዝሙር ስትዘምር 2. በጉባኤ ስብሰባ ላይ ሐሳብ ስትሰጥ 3. ለአንዲት እናትና ለልጇ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ቪዲዮ ስታሳይ

7. የተማርነውን ነገር ለሌሎች ስንናገር ይሖዋ ይደሰታል

የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለሌሎች መናገር የምንችልባቸው ብዙ አጋጣሚዎች አሉ። መዝሙር 9:1⁠ን እና 34:1⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከተማርካቸው ነገሮች መካከል ለሌሎች መናገር የምትፈልገው የትኛውን ነው?

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “አምላክ ልባችንን ስለሚያይ በየትኛውም መንገድ ብናመልከው ይቀበለናል።”

  • አንተ ምን ይመስልሃል?

ማጠቃለያ

ፈጣሪያችንን ማስደሰት ከፈለግን እሱን ብቻ ልናመልከው፣ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ልናወድሰውና የተማርነውን ነገር ለሌሎች ልንናገር ይገባል።

ክለሳ

  • አምላክን በትክክለኛው መንገድ ማምለክ የምንችለው እንዴት እንደሆነ የምንማረው ከየት ነው?

  • ይሖዋን ብቻ ማምለክ ያለብን ለምንድን ነው?

  • ከሌሎች ጋር አብረን ይሖዋን ማምለክ ያለብን ለምንድን ነው?

ግብ

ምርምር አድርግ

አንድ ወጣት በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ መገኘት ይከብደው ነበር፤ ሆኖም እንዲህ በማድረጉ ምን ጥቅም አግኝቷል?

ይሖዋ ስለ እኔ ያስባል (3:07)

ብዙ ሰዎች መስቀል የክርስትና ምልክት እንደሆነ ይሰማቸዋል፤ ሆኖም መስቀልን ለአምልኮ መጠቀም ተገቢ ነው?

“የይሖዋ ምሥክሮች መስቀልን ለአምልኮ የማይጠቀሙበት ለምንድን ነው?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)

a እነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች በሌሎች ምዕራፎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ይሰጥባቸዋል።

    የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ