የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lff ትምህርት 7
  • ይሖዋ ምን ዓይነት አምላክ ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይሖዋ ምን ዓይነት አምላክ ነው?
  • ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጠለቅ ያለ ጥናት
  • ማጠቃለያ
  • ምርምር አድርግ
  • ኢየሱስ ምን ባሕርያት አሉት?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
lff ትምህርት 7
ምዕራፍ 7. ዓለታማ በሆነ የባሕር ዳርቻ ላይ ቆሞ አድማሱን የሚመለከት ሰው

ምዕራፍ 07

ይሖዋ ምን ዓይነት አምላክ ነው?

በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው

ስለ ይሖዋ አምላክ ስታስብ ወደ አእምሮህ የሚመጣው ምንድን ነው? እንደ ከዋክብት በጣም የሚያስደምም ሆኖም ከአንተ እጅግ የራቀ እንደሆነ ይሰማሃል? ወይስ እንደ መብረቅ በጣም ኃይለኛ ሆኖም ምንም ስሜት የሌለው አካል እንደሆነ አድርገህ ታስባለህ? በእርግጥ ይሖዋ ምን ዓይነት አምላክ ነው? ይሖዋ፣ ምን ባሕርያት እንዳሉት እንዲሁም በግለሰብ ደረጃ ለአንተ እንደሚያስብ በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ገልጿል።

1. አምላክን ማየት የማንችለው ለምንድን ነው?

“አምላክ መንፈስ ነው።” (ዮሐንስ 4:24) ይሖዋ ሥጋዊ አካል የለውም። ከዚህ ይልቅ መንፈስ ነው፤ የሚኖረውም በሰማይ እኛ ልናይ በማንችለው ቦታ ነው።

2. ከይሖዋ ባሕርያት መካከል አንዳንዶቹ የትኞቹ ናቸው?

ይሖዋ በዓይን ባይታይም ግሩም ባሕርያት ያሉትና የራሱ ማንነት ያለው አካል ነው። እነዚህን ባሕርያት ስናውቅ እሱን ለመውደድ እንነሳሳለን። መጽሐፍ ቅዱስ “ይሖዋ ፍትሕን ይወዳልና፤ ታማኝ አገልጋዮቹንም አይተዋቸውም” ይላል። (መዝሙር 37:28) በተጨማሪም ይሖዋ “እጅግ አፍቃሪና መሐሪ” ነው፤ በተለይ መከራ እየደረሰባቸው ላሉ ሰዎች ፍቅርና ምሕረት ያሳያቸዋል። (ያዕቆብ 5:11) “ይሖዋ ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፤ ተስፋ የቆረጡትንም ያድናል።” (መዝሙር 34:18 የግርጌ ማስታወሻ) እኛ የምናደርገው ነገር ይሖዋን ሊያስደስተው ወይም ሊያስከፋው እንደሚችልስ ታውቃለህ? አንድ ሰው መጥፎ ነገር ሲያደርግ አምላክ ያዝናል እንዲሁም ስሜቱ ይጎዳል። (መዝሙር 78:40, 41) ጥሩ ነገር ሲያደርግ ደግሞ አምላክ ይደሰታል።—ምሳሌ 27:11⁠ን አንብብ።

3. ይሖዋ እንደሚወደን ያሳየው እንዴት ነው?

ከይሖዋ ባሕርያት መካከል ጎልቶ የሚታየው ፍቅር ነው። እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ፍቅር እንዳለው ብቻ ሳይሆን ‘አምላክ ራሱ ፍቅር እንደሆነ’ ይናገራል። (1 ዮሐንስ 4:8) ይሖዋ ፍቅሩን የገለጸው በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ብቻ አይደለም፤ የፈጠራቸው ነገሮችም የእሱን ፍቅር ያሳያሉ። (የሐዋርያት ሥራ 14:17⁠ን አንብብ።) እኛን የፈጠረበትን መንገድ እንደ ምሳሌ መውሰድ ትችላለህ። ውብ ቀለማትን የማየት፣ አስደሳች ሙዚቃ የማዳመጥና ጣፋጭ ምግቦችን የማጣጣም ችሎታ ሰጥቶናል። አምላክ ደስተኛ ሆነን እንድንኖር ይፈልጋል።

ጠለቅ ያለ ጥናት

ይሖዋ አስደናቂ ነገሮችን ለማከናወን ምን እንደተጠቀመ እናያለን። ከዚያም ማራኪ ባሕርያቱን የገለጠው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።

4. መንፈስ ቅዱስ—አምላክ የተለያዩ ሥራዎችን ለማከናወን የሚጠቀምበት ኃይል

በአምላክ መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የተከናወኑትን ነገሮች የሚያሳዩ ሥዕሎች፦ 1. ፕላኔቶችና ጽንፈ ዓለም 2. አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ በአምላክ መንፈስ እየተመራ ጥቅልል ላይ ሲጽፍ

የተለያዩ ሥራዎችን ለማከናወን እጃችንን እንደምንጠቀም ሁሉ ይሖዋም ቅዱስ መንፈሱን ይጠቀማል። መንፈስ ቅዱስ ራሱን የቻለ አካል ሳይሆን አምላክ የተለያዩ ነገሮችን ለማከናወን የሚጠቀምበት ኃይል እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ሉቃስ 11:13⁠ን እና የሐዋርያት ሥራ 2:17⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • አምላክ፣ ቅዱስ መንፈሱን ለማግኘት በሚጠይቁት ሰዎች ላይ ይህን መንፈስ ‘ያፈስሳል።’ ታዲያ መንፈስ ቅዱስ ራሱን የቻለ አካል ነው ወይስ አምላክ የተለያዩ ነገሮችን ለማከናወን የሚጠቀምበት ኃይል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

ይሖዋ አስደናቂ ነገሮችን ለማከናወን ቅዱስ መንፈሱን ይጠቀማል። መዝሙር 33:6⁠ን እና 2 ጴጥሮስ 1:20, 21⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ይሖዋ መንፈስ ቅዱስን የተጠቀመባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

በአምላክ መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የተከናወኑትን ነገሮች የሚያሳዩ ሥዕሎች፦ 1. ፕላኔቶችና ጽንፈ ዓለም 2. አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ በአምላክ መንፈስ እየተመራ ጥቅልል ላይ ሲጽፍ

5. ይሖዋ ማራኪ ባሕርያት አሉት

ታማኝ የአምላክ አገልጋይ የነበረው ሙሴ ስለ ፈጣሪው ይበልጥ ማወቅ ፈልጎ ነበር። በመሆኑም አምላክን “እንዳውቅህ . . . መንገድህን አሳውቀኝ” በማለት ጠይቆታል። (ዘፀአት 33:13) በምላሹም ይሖዋ አንዳንድ ባሕርያቱን ለሙሴ ገልጦለታል። ዘፀአት 34:4-6⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ይሖዋ ለሙሴ የትኞቹን ባሕርያቱን ገልጦለታል?

  • ከይሖዋ ባሕርያት መካከል አንተን ይበልጥ የሚማርኩህ የትኞቹ ናቸው?

6. ይሖዋ ለሰዎች ያስባል

እየጸለየች ያለች ሴት

የአምላክ ሕዝቦች የሆኑት ዕብራውያን በግብፅ ባሪያዎች ነበሩ። ይሖዋ የሚደርስባቸውን መከራ ሲያይ ምን ተሰማው? ዘፀአት 3:1-10⁠ን አንብቡ። ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ከዚህ ዘገባ መረዳት እንደምንችለው ይሖዋ በሰው ልጆች ላይ የሚደርሰውን መከራ ሲያይ ምን ይሰማዋል?—ቁጥር 7 እና 8⁠ን ተመልከት።

  • ይሖዋ የሰው ልጆችን ለመርዳት ፍላጎቱም ሆነ ችሎታው እንዳለው ታምናለህ? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

7. ፍጥረት የይሖዋን ባሕርያት ይገልጣል

አንዲትን ዓሣ ነባሪና ልጇን፣ አበቦችን እንዲሁም ሃሚንግበርድ የተባለችውን ወፍ የሚያሳዩ ሥዕሎች

ይሖዋ የፈጠራቸው ነገሮች ስለ እሱ ባሕርያት ለማወቅ ይረዱናል። ቪዲዮውን ተመልከቱ። ከዚያም ሮም 1:20⁠ን አንብቡና በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

ቪዲዮ፦ ፍጥረት የይሖዋን ፍቅር ይገልጣል—የሰው አካል (1:57)

  • በይሖዋ የፍጥረት ሥራዎች ላይ የትኞቹ ባሕርያቱ ተንጸባርቀዋል?

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “አምላክ በእውን ያለ አካል ሳይሆን በየትኛውም ቦታ የሚገኝ ኃይል ነው።”

  • አንተ ምን ይመስልሃል?

  • እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

ማጠቃለያ

ይሖዋ በዓይን የማይታይ መንፈሳዊ አካል ነው፤ በርካታ ማራኪ ባሕርያት ያሉት ሲሆን ከእነዚህ መካከል ዋነኛው ፍቅር ነው።

ክለሳ

  • ይሖዋን ማየት የማንችለው ለምንድን ነው?

  • መንፈስ ቅዱስ ምንድን ነው?

  • ከይሖዋ ባሕርያት መካከል አንዳንዶቹ የትኞቹ ናቸው?

ግብ

ምርምር አድርግ

አምላክ በሁሉም ቦታ እንደማይገኝ የሚያሳዩ ማስረጃዎችን መርምር።

“አምላክ በሁሉም ቦታ ይገኛል?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)

መጽሐፍ ቅዱስ፣ መንፈስ ቅዱስን የአምላክ እጅ እንደሆነ አድርጎ የሚገልጸው ለምን እንደሆነ ተመልከት።

“መንፈስ ቅዱስ ምንድን ነው?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)

    የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ