መዝሙር
33 እናንተ ጻድቃን ሆይ፣ ይሖዋ ባደረጋቸው ነገሮች የተነሳ እልል በሉ።+
ቅኖች እሱን ማወደሳቸው የተገባ ነው።
2 ይሖዋን በበገና አመስግኑት፤
አሥር አውታር ባለው መሣሪያ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩለት።
3 አዲስ መዝሙር ዘምሩለት፤+
በባለ አውታር መሣሪያ ጥሩ አድርጋችሁ ተጫወቱ፤ እልልም በሉ።
4 የይሖዋ ቃል ትክክል ነውና፤+
ሥራውም ሁሉ እምነት የሚጣልበት ነው።
5 ጽድቅንና ፍትሕን ይወዳል።+
ምድር በይሖዋ ታማኝ ፍቅር ተሞልታለች።+
7 የባሕርን ውኃዎች እንደ ግድብ ያከማቻል፤+
የሚናወጠውንም ውኃ በማከማቻ ቦታ ይሰበስባል።
8 መላዋ ምድር ይሖዋን ትፍራ።+
የምድር ነዋሪዎች እሱን ይፍሩ።*
12 ይሖዋ አምላኩ የሆነ ብሔር፣
የራሱ ንብረት አድርጎ የመረጠው ሕዝብ ደስተኛ ነው።+
13 ይሖዋ ከሰማይ ሆኖ ይመለከታል፤
የሰው ልጆችን ሁሉ ያያል።+
14 ከመኖሪያ ቦታው ሆኖ
በምድር የሚኖሩትን በትኩረት ይመለከታል።
15 የሁሉንም ልብ የሚሠራው እሱ ነው፤
ሥራቸውን ሁሉ ይመረምራል።+
18 እነሆ፣ የይሖዋ ዓይን የሚፈሩትን፣
ደግሞም ታማኝ ፍቅሩን የሚጠባበቁትን በትኩረት ይመለከታል፤+
19 ይህም እነሱን* ከሞት ለመታደግ፣
በረሃብ ወቅትም እነሱን በሕይወት ለማኖር ነው።+
20 ይሖዋን በተስፋ እንጠባበቃለን።*
እሱ ረዳታችንና ጋሻችን ነው።+
21 ልባችን በእሱ ሐሴት ያደርጋል፤
በቅዱስ ስሙ እንታመናለንና።+