ኢዮብ 37:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ከመረዳት ችሎታችን በላይ ነው፤+ኃይሉ ታላቅ ነው፤+ደግሞም ፍትሑንና ታላቅ ጽድቁን አይጥስም።+ መዝሙር 11:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ይሖዋ ጻድቅ ነውና፤+ የጽድቅ ሥራዎችን ይወዳል።+ ቅን የሆኑ ሰዎች ፊቱን ያያሉ።*+ መዝሙር 45:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ጽድቅን ወደድክ፤+ ክፋትን ጠላህ።+ ስለዚህ አምላክ ይኸውም አምላክህ ከባልንጀሮችህ ይበልጥ በደስታ ዘይት+ ቀባህ።+