-
ዘፍጥረት 1:9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 በመቀጠልም አምላክ “ከሰማያት በታች ያሉት ውኃዎች አንድ ቦታ ላይ ይሰብሰቡና ደረቁ መሬት ይገለጥ” አለ።+ እንዳለውም ሆነ።
-
-
ምሳሌ 8:29አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
29 የባሕሩ ውኃ
ከትእዛዙ አልፎ እንዳይሄድ በደነገገ ጊዜ፣+
የምድርን መሠረቶች ባቆመ* ጊዜ፣
-
ኤርምያስ 5:22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 ‘እኔን አትፈሩም?’ ይላል ይሖዋ፤
‘በፊቴስ ልትሸበሩ አይገባም?
ውኃው አልፎ እንዳይሄድ፣ በማይሻር ድንጋጌ
አሸዋውን የባሕሩ ወሰን አድርጌ የሠራሁት እኔ ነኝ።
ሞገዶቹ ቢናወጡም ጥሰው መሄድ አይችሉም፤
ቢያስገመግሙም ከዚያ አልፈው መሄድ አይችሉም።+
-
-
-