የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g99 5/8 ገጽ 16
  • ሕፃናት እንዴት ቢተኙ ይሻላል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሕፃናት እንዴት ቢተኙ ይሻላል?
  • ንቁ!—1999
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሕፃናት የሚያስፈልጋቸውና የሚፈልጉት
    ንቁ!—2004
  • ልጅ መውለድ በትዳር ውስጥ የሚያመጣው ለውጥ
    ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
  • የእናት ጡት ወተት የሚመረጥበት ምክንያት
    ንቁ!—1994
ንቁ!—1999
g99 5/8 ገጽ 16

ሕፃናት እንዴት ቢተኙ ይሻላል?

ድንገተኛ የሕፃናት ሞት (ኤስ አይ ዲ ኤስ) በዓለም ዙሪያ የብዙ ሕፃናትን ሕይወት በመቅጠፍ ላይ ይገኛል። በዩናይትድ ስቴትስ ከ1 እስከ 12 ወር ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሕፃናትን ለሕልፈተ ሕይወት ከሚዳርጉት የተለመዱ ችግሮች አንዱ ኤስ አይ ዲ ኤስ ነው። ይህን አደጋ መቀነስ ይቻል ይሆን? ዘ ጆርናል ኦቭ ዚ አሜሪካን መዲካል አሶሲዬሽን (ጃማ) እንዳለው ከሆነ ሕፃናትን በሆዳቸው ከማስተኛት ይልቅ በጀርባቸው እንዲተኙ ማድረግ ለኤስ አይ ዲ ኤስ የሚጋለጡበትን አጋጣሚ በእጅጉ እንደሚቀንስ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተካሄዱ ጥናቶች ያሳያሉ። በርካታ አገሮች በአተኛኘት ሁኔታና በኤስ አይ ዲ ኤስ መካከል ያለውን ዝምድና ለወላጆች ለማስገንዘብ ዕቅድ ነድፈዋል። በአውስትራሊያ፣ በእንግሊዝ፣ በዴንማርክ፣ በኒው ዚላንድና በኖርዌይ ወላጆች ልጆቻቸውን በጀርባቸው እንዲያስተኙ ለማበረታታት ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት የፈጀ ዘመቻ ከተካሄደ በኋላ በኤስ አይ ዲ ኤስ የሚቀጠፉ ሕፃናት ቁጥር 50 በመቶ ሊቀንስ ችሏል።

አንድ ሕፃን በሆዱ መተኛቱ ከኤስ አይ ዲ ኤስ ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችለው እንዴት እንደሆነ በትክክል ማስረዳት ባይቻልም አንዳንድ ተመራማሪዎች ሕፃኑ በሆዱ መተኛቱ ያስወጣውን አየር መልሶ እንዲስብ ሊያደርገው እንደሚችልና ይህ ደግሞ በደሙ ውስጥ ያለውን የካርቦን ዳይኦክሳይድ መጠን ከፍ እንደሚያደርገው ይናገራሉ። በተጨማሪም ሕፃኑ በሆዱ ሲተኛ ሰውነቱ ሙቀቱን ስለማያስወጣ ከልክ በላይ ሊሞቀው ይችላል። ያም ሆነ ይህ በጀርባቸውም ሆነ በሆዳቸው እንዲተኙ የተደረጉ ሕፃናት ብዙውን ጊዜ አይገላበጡም። በተጨማሪም አንድን ጤናማ ሕፃን በጎኑ ከማስተኛት ይልቅ በጀርባው ማስተኛት የተሻለ እንደሆነ የተደረጉት ጥናቶች ያሳያሉ።

እናቶች ልጆቻቸውን የሚያስተኙበት መንገድ የሚለያየው ለምንድን ነው? ብዙውን ጊዜ እናቶች የአካባቢውን ልማድ ይከተላሉ ሲል ጃማ ይገልጻል። ሕፃናት ልጆቻቸውን የእነሱ እናቶች ወይም ማኅበረሰቡ በሚያስተኛበት መንገድ ያስተኛሉ። አለዚያም ደግሞ በሆስፒታል ያዩትን ልማድ ሊከተሉ ይችላሉ። በተጨማሪም አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸው በአንድ በተወሰነ ሁኔታ መተኛት እንደሚመርጡ ወይም በዚያ ሁኔታ ቢተኙ የተሻለ እንደሚሆን አድርገው ያስባሉ። ብዙ እናቶች በመጀመሪያው ወር ላይ ልጃቸውን በጀርባው ያስተኙታል፤ ከዚያ በኋላ ግን በሆዱ ማስተኛት ይጀምራሉ። “ከ2 እስከ 3 ወር ዕድሜ ያላቸው ሕፃናት ለኤስ አይ ዲ ኤስ በጣም የተጋለጡ በመሆናቸው ይህ አዝማሚያ አሳሳቢ ነው” ይላል ጃማ። ዶክተሮች ትንንሽ ልጆች ያሏቸው ወላጆች ጤናማ ሕፃናትን በጀርባቸው ማስተኛት ቀላልና ለኤስ አይ ዲ ኤስ የሚጋለጡበትን አጋጣሚ በመቀነስ ረገድ ውጤታማ እንደሆነ እንዲገነዘቡ ለማድረግ እየጣሩ ነው።a

[የግርጌ ማስታወሻ]

a አንድ ሕፃን የመተንፈሻ አካል ሕመም ካለበት ወይም ደግሞ ቅርሻት የሚያስቸግረው ከሆነ በምን መልኩ ማስተኛት እንደሚሻል ሐኪም ማማከሩ ጠቃሚ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ