የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 10/11 ገጽ 24-31
  • ቤተሰብ የሚወያይበት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቤተሰብ የሚወያይበት
  • ንቁ!—2011
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከእነዚህ ሥዕሎች ውስጥ የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?
  • ካርድ በመሰብሰብ መማር
  • ሕዝቦችና አገሮች
  • ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
  • በገጽ 30 እና 31 ላይ ያሉት ጥያቄዎች መልስ
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2012
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2012
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2012
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2011
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2011
g 10/11 ገጽ 24-31

ቤተሰብ የሚወያይበት

ከእነዚህ ሥዕሎች ውስጥ የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?

ምሳሌ 18:10ን እና 26:17ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሎቹን ተመልከት። በጥቅሱ ውስጥ ከተገለጹት መካከል የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ። እንዲሁም ሥዕሎቹ የተሟሉ እንዲሆኑ ነጥቦቹን በመስመር ካገናኘህ በኋላ ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።

1. ․․․․․

2. ․․․․․

[ሰንጠረዥ]

(ጽሑፉን ተመልከት)

ለውይይት፦

ከእነዚህ ጥቅሶች ምን ትምህርት አገኘህ? የአምላክን ሞገስ ለማግኘት ስሙን ማወቅ ብቻ በቂ ነው?

ፍንጭ፦ መዝሙር 91:2⁠ን እና ምሳሌ 3:5, 6⁠ን አንብብ።

በሌሎች ሰዎች ጉዳይ ጣልቃ መግባት የሌለብህ ለምንድን ነው?

ፍንጭ፦ ገላትያ 6:5-7⁠ን፤ 1 ተሰሎንቄ 4:11⁠ን እና 1 ጴጥሮስ 4:15⁠ን አንብብ።

ከዚያም ምሳሌ 26:18, 19⁠ን አንብብ። አጉል ቀልድ ምንም ጉዳት የሌለው መዝናኛ ነው?

ፍንጭ፦ ምሳሌ 14:13⁠ን፤ ምሳሌ 15:21⁠ን እና ማቴዎስ 7:12⁠ን አንብብ።

ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦

ምሳሌ 31:10-31⁠ን በጋራ አንብቡ። ከመካከላችሁ አንደኛው በጥቅሱ ላይ የተገለጸችው ጠባየ መልካም ወይም ባለሙያ ሚስት የምታከናውናቸውን አንዳንድ ሥራዎች ምንም ድምፅ ሳያሰማ በእንቅስቃሴ ያሳይ። የተቀራችሁት ደግሞ ምን እየሠራ እንደሆነ ለማወቅ ሞክሩ። ይበልጥ ባለሙያ ለመሆን ምን ዓይነት የቤት ውስጥ ሥራዎችን መማር እንደምትችሉ ተወያዩ።

ካርድ በመሰብሰብ መማር

ቆርጠህ አውጣውና ለሁለት አጥፈህ አስቀምጠው

የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 10 ሰለሞን

ጥያቄ

ሀ. ሰለሞን ሀብት ወይም ረጅም ዕድሜን ከመለመን ይልቅ ምን እንዲሰጠው ጸልዮአል?

ለ. ክፍት ቦታዎቹን ሙላ። ሰለሞን ․․․․․ ምሳሌዎችን የተናገረ ሲሆን የመሓልዩም ቁጥር ․․․․․. ነበር።

ሐ. የሰለሞን ሌላኛው ስም ማን ነው?

[ሰንጠረዥ]

4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ

ሰለሞን የኖረበት ዘመን 1000 ዓ.ዓ. ገደማ

1 ዓ.ም.

98 ዓ.ም. የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጻፈ

[ካርታ]

ንግሥተ ሳባ የሰለሞንን ጥበብ ለመስማት 2,400 ኪሎ ሜትር ያህል ተጉዛለች

ሳባ

ኢየሩሳሌም

ሰለሞን

አጭር የሕይወት ታሪክ፦

የዳዊትና የቤርሳቤህ ሁለተኛ ልጅ ነው። ሰለሞን እስራኤልን ለ40 ዓመታት ገዝቷል። ለይሖዋ አምልኮ የሚያገለግል ታላቅ ቤተ መቅደስ ገንብቷል። (1 ነገሥት 5:2-5) ይሖዋ በሰለሞን አማካኝነት የምሳሌ፣ የመክብብና የማሕልየ መሓልይ መጻሕፍት እንዲጻፉ አድርጓል። ሰለሞን ይሖዋን የማያመልኩ መጥፎ ሴቶችን ማግባቱ ከይሖዋ እንዲርቅ አድርጎታል።​—1 ነገሥት 11:1-6

መልስ

ሀ. አስተዋይ ልብ።​—1 ነገሥት 3:5-14

ለ. 3,000፣ 1,005​—1 ነገሥት 4:29, 32

ሐ. ይዲድያ፤ ትርጉሙም “በይሖዋ የተወደደ” ማለት ነው።​—2 ሳሙኤል 12:24, 25

ሕዝቦችና አገሮች

3. ክሎዊ እባላለሁ። የዘጠኝ ዓመት ልጅ ስሆን የምኖረው በካናዳ ነው። በካናዳ ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 55,000፣ 88,000 ወይስ 110,000?

4. የምኖርበትን አገር የሚጠቁመው ፊደል የትኛው ነው? በፊደሉ ላይ አክብብ፤ ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከካናዳ በጣም ይርቃል?

ሀ

ለ

ሐ

መ

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

“ቤተሰብ የሚወያይበት” የሚለውን ዓምድ ተጨማሪ ቅጂ ለማግኘት www.pr418.com ከተባለው ድረ ገጽ ላይ ማተም ይቻላል።

● “ቤተሰብ የሚወያይበት” መልሶች በገጽ 24 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 30 እና 31 ላይ ያሉት ጥያቄዎች መልስ

1. ጽኑ ግንብ

2. ውሻ

3. 110,000

4. ሀ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ