የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • hf ክፍል 9 ገጽ 29-31
  • በቤተሰብ ሆናችሁ ይሖዋን አምልኩ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በቤተሰብ ሆናችሁ ይሖዋን አምልኩ
  • ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • 1 ከይሖዋ ጋር ያላችሁን ዝምድና አጠናክሩ
  • 2 የቤተሰብ አምልኳችሁን አስደሳች አድርጉት
  • ቤተሰቦችን ለመርዳት የተደረገ ዝግጅት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • የቤተሰብ አምልኮ ምንድን ነው?
    በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው?
  • የቤተሰብ አምልኮ—ይበልጥ አስደሳች እንዲሆን ማድረግ ትችላላችሁ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • “ወደ አምላክ ቅረቡ፤ እሱም ወደ እናንተ ይቀርባል”
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
ለተጨማሪ መረጃ
ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
hf ክፍል 9 ገጽ 29-31
ባልና ሚስት መጽሐፍ ቅዱስን አብረው ሲያጠኑ

ክፍል 9

በቤተሰብ ሆናችሁ ይሖዋን አምልኩ

“ሰማይን፣ ምድርን . . . የሠራውን አምልኩ።”—ራእይ 14:7

በዚህ ብሮሹር ውስጥ እንደተማራችሁት መጽሐፍ ቅዱስ ቤተሰባችሁን የሚጠቅሙ ብዙ መመሪያዎች ይዟል። ይሖዋ ደስተኛ እንድትሆኑ ይፈልጋል። የእሱን አምልኮ ካስቀደማችሁ ሌሎቹ “ነገሮች ሁሉ ይሰጧችኋል” በማለት ቃል ገብቷል። (ማቴዎስ 6:33) ይሖዋ ወዳጆቹ እንድትሆኑ ይፈልጋል። ከእሱ ጋር ያላችሁን ወዳጅነት ለማጠናከር የሚያስችሏችሁን አጋጣሚዎች ሁሉ ተጠቀሙ። አንድ ሰው ሊያገኘው ከሚችለው መብት ሁሉ የላቀው የአምላክ ወዳጅ መሆን ነው።—ማቴዎስ 22:37, 38

1 ከይሖዋ ጋር ያላችሁን ዝምድና አጠናክሩ

ባልና ሚስት አብረው ሲያገለግሉ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “‘እኔ አባት እሆናችኋለሁ፤ እናንተ ደግሞ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ትሆኑኛላችሁ’ ይላል ሁሉን ቻይ የሆነው ይሖዋ።” (2 ቆሮንቶስ 6:18) አምላክ የቅርብ ወዳጆቹ እንድትሆኑ ይፈልጋል። ወዳጆቹ እንድትሆኑ ከሚረዷችሁ ነገሮች አንዱ ደግሞ ጸሎት ነው። ይሖዋ “ዘወትር ጸልዩ” በማለት ይጋብዛችኋል። (1 ተሰሎንቄ 5:17) የልባችሁን ሐሳብና የሚያስጨንቋችሁን ነገሮች መስማት ይፈልጋል። (ፊልጵስዩስ 4:6) አባት ከቤተሰቡ ጋር ሆኖ ሲጸልይ የቤተሰቡ አባላት አምላክ ለእሱ ምን ያህል እውን እንደሆነ መመልከት ይችላሉ።

ለአምላክ ሐሳባችሁን ከመግለጽ በተጨማሪ እናንተም እሱን ማዳመጥ ይኖርባችኋል። ይህን ማድረግ የምትችሉት ቃሉንና በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ጽሑፎችን በማጥናት ነው። (መዝሙር 1:1, 2) የምትማሩትን ነገር አሰላስሉበት። (መዝሙር 77:11, 12) አምላክን ለማዳመጥ በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ አዘውትራችሁ መገኘትም ያስፈልጋችኋል።—መዝሙር 122:1-4

ከይሖዋ ጋር ያላችሁን ወዳጅነት ለማጠናከር ከሚረዷችሁ ጠቃሚ መንገዶች መካከል ሌላው ደግሞ ስለ እሱ ለሰዎች መናገር ነው። ይህን አዘውትራችሁ ባደረጋችሁ መጠን ይበልጥ ወደ እሱ እየቀረባችሁ ትሄዳላችሁ።—ማቴዎስ 28:19, 20

ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

  • በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብና ለጸሎት የሚሆን ጊዜ መድቡ

  • ቤተሰባችሁ ከመዝናኛ ይበልጥ ለመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ቅድሚያ ይስጥ

2 የቤተሰብ አምልኳችሁን አስደሳች አድርጉት

አባት ከቤተሰቡ ጋር ለማጥናት ሲዘጋጅ፤ ከዚያም የቤተሰብ አምልኮ ሲያደርጉ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ወደ አምላክ ቅረቡ፤ እሱም ወደ እናንተ ይቀርባል።” (ያዕቆብ 4:8) ቋሚ የሆነ የቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራም ማውጣትና አዘውትራችሁ ፕሮግራሙን መከተል ያስፈልጋችኋል። (ዘፍጥረት 18:19) ይሁን እንጂ ከዚህም የበለጠ የሚያስፈልግ ነገር አለ። አምላክ የየዕለቱ ሕይወታችሁ ክፍል መሆን አለበት። ‘በቤታችሁ ስትቀመጡ፣ በመንገድ ላይ ስትሄዱ እንዲሁም ስትተኙና ስትነሱ’ ስለ አምላክ በመናገር ቤተሰባችሁ ከአምላክ ጋር ያለውን ወዳጅነት እንዲያጠናክር አድርጉ። (ዘዳግም 6:6, 7) ግባችሁ “እኔና ቤተሰቤ ግን ይሖዋን እናገለግላለን” በማለት እንደተናገረው እንደ ኢያሱ ይሁን።—ኢያሱ 24:15

ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

  • እያንዳንዱ የቤተሰባችሁ አባል የሚያስፈልገውን ነገር ያገናዘበ ቋሚ የሆነ የልምምድ ፕሮግራም ይኑራችሁ

እናት ለትንሽ ልጇ ስታነብለት፤ ቤተሰቡ የመጽሐፍ ቅዱስን ዘገባ በድራማ መልክ ሲሠሩ፤ አባት ልጁን ሲያስጠናት

ደስተኛ የይሖዋ አገልጋዮች

ይሖዋ አምላክን ከማምለክ የሚበልጥ ምንም ነገር የለም። ይሖዋ በቤተሰብ ሆናችሁ ከልባችሁ ስታገለግሉት ይደሰታል። ይህን ስታደርጉ ይሖዋን ይበልጥ እየወደዳችሁትና እየመሰላችሁት ትሄዳላችሁ። (ማርቆስ 12:30፤ ኤፌሶን 5:1) አምላክን በትዳራችሁ ውስጥ ማስገባታችሁ ከትዳር ጓደኛችሁ ጋር ያላችሁን ትስስርም ያጠናክረዋል። (መክብብ 4:12፤ ኢሳይያስ 48:17) “አምላካችሁ ይሖዋ” ቤተሰባችሁን ‘እንደባረከው’ ስለምታውቁ ለዘላለም ደስተኛ መሆን ትችላላችሁ።—ዘዳግም 12:7

ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦

  • ከባለቤቴ ጋር አብረን ከጸለይን ምን ያህል ጊዜ ሆኖናል?

  • በይሖዋ ላይ ያለንን እምነት ለማጠናከር ከቤተሰቤ ጋር ምን ማጥናት እንችላለን?

ለቤተሰብ ራሶች

  • የቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራማችሁን ምንም ነገር እንዲያስተጓጉለው አትፍቀዱ

  • ቤተሰባችሁ ዝግጅት ማድረግ እንዲችል የምትወያዩበትን ነገር ቀደም ብላችሁ አሳውቁ

  • በፕሮግራማችሁ ላይ ሁሉም የቤተሰቡ አባላት እንዲገኙ አድርጉ

  • ሁሉም የሚደሰቱበት ሰላማዊ ሁኔታ እንዲሰፍን አድርጉ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ