የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 2/15 ገጽ 23
  • የወንድማማች ፍቅር አንቀሳቃሽ ነው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የወንድማማች ፍቅር አንቀሳቃሽ ነው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለእምነትና ለፍቅር የተሰጠ ምሥጋና
  • በፍቅር ላይ የተመሠረተ ጥብቅ ምክር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ፊልሞና እና አናሲሞስ በክርስቲያናዊ ወንድማማችነት ተስማሙ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • ጳውሎስ በሮም
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ፊልሞና የመጽሐፉ ይዘት
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 2/15 ገጽ 23

የወንድማማች ፍቅር አንቀሳቃሽ ነው

ከፊልሞና የተገኙ ዋና ዋና ነጥቦች

ኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮቹ ሁሉ እርሱ እንደወደዳቸው እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲዋደዱ “አዲስ ትዕዛዝ” ሰጥቶአቸው ነበር። (ዮሐንስ 13:34, 35) በዚህ ፍቅር ምክንያት አንዳቸው ለሌላው ይሞታሉ። አዎ፣ የወንድማማች ፍቅር ይህን ያህል ጠንካራና አንቀሳቃሽ ነው።

ሐዋርያው ጳውሎስ በታናሽቱ እስያ የምትገኘው የቆላስይስ ጉባኤ አባል የነበረው ፊልሞና በወንድማማች ፍቅር እንደሚገፋፋ እርግጠኛ ነበር። ከዚያም በፊት ቢሆን ፊልሞና የነበረው ፍቅር ቤቱን ለጉባኤ ስብሰባ ክፍት አድርጎ እንዲሰጥ ገፋፍቶት ነበር። አናሲሞስ የተባለው የፊልሞና ባሪያ ጠፍቶ ሄዶ ነበር። እስከ ሮማ የሚያጓጉዘው ገንዘብም ሳይሰርቀው አልቀረም። በሮማ ግን ከጳውሎስ ጋር ተገናኘና ክርስትናን ተቀበለ።

ጳውሎስ በሮማ ታስሮ እያለ ከ60-61 እዘአ ላይ አድራሻው ለፊልሞና የሆነ ደብዳቤ ጻፈ። ደብዳቤው ፊልሞና ተመልሶ የመጣውን አናሲሞስን በወንድማማች ፍቅር መንፈስ እንዲቀበል የሚማጸነው ነበር። ይህን ደብዳቤ አንብብ የፍቅርና የዘዴኛነት ጠባይ የተገለጸበት ደብዳቤ እንደሆነ ተገንዘብ። የይሖዋ ሕዝቦች እነዚህን ጠባዮች ቢቀዱ በጣም ጥሩ ይሆናል።

ለእምነትና ለፍቅር የተሰጠ ምሥጋና

ጳውሎስ በመጀመሪያ ፊልሞናንና ሌሎች ክርስቲያኖችን አመሰገነ። (ቁጥር 1-7) ሐዋርያው ፊልሞና ለክርስቶስና ለቅዱስና ሁሉ ስላለው ፍቅርና ስለ እምነቱ ይሰማ ነበር። ይህም ይሖዋን እንዲያመሰግን ገፋፍቶት ነበር። ብዙ ደስታና መጽናኛ አስገኝቶለት ነበር። እኛስ በፍቅርና በእምነት ምሳሌ የሚሆኑትን የእምነት ባልደረቦቻችንን እናመሰግናለንን? ማመስገን ይገባናል።

የጳውሎስ ቃል እንደሚያመለክተው ከክርስቲያኖች ጋር በሚኖረን ግንኙነት ሁሉ በፍቅር ላይ የተመሰረተ ምክር መስጠት ተፈላጊ ነው። (ቁጥር 8-14) ሐዋርያው በዘዴ ከቀረበ በኋላ ፊልሞና ተገቢ የሆነውን ነገር እንዲያደርግ ለማዘዝ ቢችልም ሊመክረው መርጦአል። ምን እንዲያደርግ ነበር የመከረው? አናሲሞስ የተባለውን ባሪያ በደግነት እንዲቀበል ነበር። ጳውሎስ የአናሲሞስ አገልግሎት ይጠቅመው ስለነበር ለራሱ ሊያስቀረው ፈልጎ ነበር። ግን ፊልሞና ሳይፈቅድለት ይህን ሊያደርግ አልፈለገም።

ጳውሎስ ቀጥሎ እንደገለጸው መጥፎ መስሎ የታየ ድርጊት በመጨረሻው ጠቃሚ ሆኖ ሊገኝ ይችላል። (ቁጥር 15-21) አናሲሞስ ጠፍቶ በመሄዱ ጥሩ ውጤት ተገኝቶአል። ምክንያቱም አሁን ፊልሞና አናሲሞስን አለፈቃዱ የሚገዛና አጭበርባሪ እንደሆነ ባሪያ ሳይሆን ፈቃደኛና ሐቀኛ እንደሆነ ክርስቲያን ወንድም ሊቀበለው ችሎአል። ፊልሞና አናሲሞስን ልክ ጳውሎስን እንደሚቀበለው አድርጎ እንዲቀበለው ጠይቆታል። አናሲሞስ በማንኛውም መንገድ ፊልሞናን በድሎ ከሆነ ጳውሎስ ይክሰዋል። አሁንም ፊልሞና ይበልጥ ፈቃደኛ እንዲሆን እርሱ ራሱ ክርስቲያን ለመሆን በመቻሉ ለጳውሎስ ባለ ዕዳ መሆኑን አሳስቦታል። ስለዚህ ፊልሞና ከተጠየቀው በላይ እንደሚያደርግ ጳውሎስ እርግጠኛ ነበር። በጣም ጥሩ በሆነ ዘዴና የፍቅር መንፈስ መማጸኑ ነበር። ከክርስቲያን ባልንጀሮቻችን ጋር በሚኖረን ግንኙነት ሁሉ እንዲህ ማድረግ ይኖርብናል።

ጳውሎስ ደብዳቤን የደመደመው በሰላምታና ተስፋውንና መልካም ምኞቱን በመግለጽ ነበር። (ቁጥር 22-25) ሌሎች በሚያቀርቡለት ጸሎት አማካኝነት ከእስር ቤት ቶሎ እንደሚፈታ ተስፋ እንዳለው ገለጸ። (ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የላከው ሁለተኛ ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ይህ ጸሎት ምላሽ አግኝቶአል።) ጳውሎስ ደብዳቤውን ሲያጠቃልል ሰላምታ ካቀረበ በኋላ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ፊልሞናና ሌሎች የይሖዋ አምላኪዎች ከሚያሳዩት መንፈስ ጋር እንዲሆን ምኞቱ እንደሆነ ገልጾአል።

[በገጽ 23 ላይ የሚገኝ ሣጥን/ሥዕሎች]

ከባሪያ የበለጠ ነገር፦ ጳውሎስ ጠፍቶ ስለነበረው የፊልሞና ባሪያ ስለ አናሲሞስ ሲናገር “ተቀብለህ ለዘላለም እንድትይዘው ስለዚህ ምናልባት ለጊዜው ተለይቶሃልና፤ ነገር ግን ለእኔ በተለይ የተወደደ ወንድም ከሆነ ለአንተማ ይልቅ በሥጋውም በጌታም ዘንድ ከባሪያ የሚሻል የተወደደ ወንድም እንዴት አይሆንም?” (ፊልሞና 15, 16) በሮማ ግዛት ውስጥ አጼያዊው መንግሥት የባርነትን ሥርዓት ያስከብር ነበር። ጳውሎስም ይህን “የበላይ ባለሥልጣን” ያከብር ነበር። (ሮሜ 13:1-7) ባሮች ክርስቲያን ሆነው መንፈሳዊ ነጻነት እንዲያገኙ ይረዳቸው ነበር እንጂ በጌቶቻቸው ላይ እንዲያምጹ አይመክርም ነበር። ጳውሎስ ባሮች ለጌቶቻቸው እንዲገዙ ከሰጠው ምክር ጋር በመስማማት አናሲሞስን ወደ ፊልሞና መለሰው። (ቆላስይስ 3:22-24፤ ቲቶ 2:9, 10) አሁን አናሲሞስ ከዓለማዊ ባሪያ የበለጠ ነበር። አሁን ለፊልሞና በተመጣጣኝ ሁኔታ የሚገዛ የተሻለ ባሪያ፣ በአምላካዊ ሥርዓቶች የሚገዛና የወንድማማች ፍቅር ያለው የተወደደ የእምነት ባልንጀራ ሆኖአል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ