የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w96 1/15 ገጽ 31
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የቤተሰብ ደስታ የሚገኝበት ቁልፍ ይኖራልን?
    ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?
  • በቤተሰብ ኑሮ ተደሰት
    በቤተሰብ ኑሮ ተደሰት
  • ቤተሰብ ለሰው ልጅ የግድ አስፈላጊ ነው!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • በይሖዋ ቤተሰብ ውስጥ ያለህን ቦታ ከፍ አድርገህ ተመልከት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
w96 1/15 ገጽ 31

የአንባብያን ጥያቄዎች

ኤፌሶን 3:14, 15 “በሰማይና በምድር ያለ ቤተሰብ ሁሉ . . . ስሙን የሚያገኘው” ከአምላክ እንደሆነ ይናገራል። በሰማይ ቤተሰቦች አሉን? እያንዳንዱ ቤተሰብ ስሙን ከይሖዋ የሚያገኘው እንዴት ነው?

እዚህ ምድር ላይ እንዳሉት ቤተሰቦች ዓይነት አባትን፣ እናትንና ልጆችን ያቀፉ በሥጋ የሚዛመዱ ቤተሰቦች በሰማይ የሉም። (ሉቃስ 24:39፤ 1 ቆሮንቶስ 15:50) ኢየሱስ መላእክት እንደማያገቡ በግልጽ የተናገረ ሲሆን ልጅ እንደሚወልዱ የሚጠቁም ምንም ነገር የለም።—ማቴዎስ 22:30 የ1980 ትርጉም

ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋ አምላክ ከሰማያዊ ድርጅቱ ጋር እንደተጋባ ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ ይናገራል፤ ያገባው በመንፈሳዊ ሁኔታ ነው። (ኢሳይያስ 54:5) ይህ ሰማያዊ ድርጅት እንደመላእክት ያሉትን ልጆች አፍርቷል። (ኢዮብ 1:6፤ 2:1፤ 38:4-7) በዚህ መንገድ በሰማይ አንድ ግሩም የሆነ መንፈሳዊ ቤተሰብ አለ ማለት ነው።

በተጨማሪም ኢየሱስ ክርስቶስንና የእርሱ ሙሽራ የሆነችውን የ144,000 ጉባኤ የያዘ አዲስ ምሳሌያዊ ቤተሰብ በሰማይ እየተመሠረተ ነው። (2 ቆሮንቶስ 11:2) ሰማያዊ ሕይወት ከሚጠባበቁት ከእነዚህ ቅቡዓን ውስጥ አብዛኞቹ ሞተዋል። ጥቂቶቹ አሁንም እዚህ ምድር ላይ በሕይወት አሉ። ሁሉም በሰማይ የሚከናወነውን ‘የበጉን ሰርግ’ በጉጉት ይጠባበቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ሰርግ እየቀረበ ካለው ታላቁ መከራ ማለትም ከታላቂቱ ባቢሎን መውደምና ከዚያ ቀጥሎ ከሚሆነው የተቀረው የሰይጣን ዓለም ጥፋት ጋር ያያይዘዋል።—ራእይ 18:2-5፤ 19:2, 7, 11-21፤ ማቴዎስ 24:21

ሐዋርያው ጳውሎስ በኤፌሶን 3:15 ላይ እያንዳንዱ ምድራዊ ቤተሰብ ስሙን በቀጥታ ከይሖዋ እንደሚያገኝ አይናገረም። ሐዋርያው ጳውሎስ የተናገረው አንድ ስም እንዳይጠፋ ጠብቆ ስለሚያቆየው የቤተሰብ ተዋረድ ነበር። ኢያሱ 7:16-19 አንድ ምሳሌ ይሰጠናል። እዚህ ጥቅስ ላይ ይሖዋ የአካንን ኃጢአት እንዳጋለጠ ይናገራል። መጀመሪያ ላይ በአጥፊነት የተተኮረበት ወይም እንደ አጥፊ የተወሰደው የይሁዳ ነገድ ነበር። ከዚያም በዛራን ቤተሰብ ላይ ተነጣጠረና እየጠበበ መጣ። በመጨረሻም የአካን ቤተሰብ ተጋለጠ። አካን፣ ሚስቱና ልጆቹ የአካን አያት የሆነው የዘንበሪ ቤተሰብ አባላት እንደሆኑ ተደርገው ይታዩ ነበር። ይህ ቤተሰብ ደግሞ የቅድመ አያታቸውን የዛራንን ስም ጠብቆ የሚያቆይ ቡድን ነበር።

በዕብራውያን ዘንድ እንዲህ ያሉ የቤተሰብ ተዋረዶች ከፍተኛ ቦታ የሚሰጣቸው ሲሆን ብዙዎቹ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተዘርዝረዋል። ወራሽ የሚሆኑ ልጆች የቤተሰቡን ስም ይዘው እንዲወለዱ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከወንድም ሚስት ጋር መጋባትን በመፍቀድ አምላክ የቤተሰብ ተዋረድ እንዳይጠፋ ዝግጅት አድርጓል።—ዘፍጥረት 38:8, 9፤ ዘዳግም 25:5, 6

ኢየሱስ የዳዊት ልጅ ተደርጎ መጠቀሱን ተመልከት፤ ይህም ረጅም ተዋረድ ላላቸው ቤተሰቦች ሌላ ምሳሌ ይሆነናል። ኢየሱስ የተወለደው ዳዊት ከሞተ በመቶ ከሚቆጠሩ ዓመታት በኋላ ስለሆነ ቃል በቃል የዳዊት ልጅ እንዳልነበረ ግልጽ ነው። ቢሆንም አይሁዶች በጠቅላላ እንደሚያውቁት አንዱ የመሲሑ መለያ ምልክት የዳዊት ቤተሰብ መሆኑ ነው። (ማቴዎስ 22:42) ኢየሱስ በእናቱም ሆነ በአሳዳጊ አባቱ በኩል የዳዊት ዘር ነበር።—ማቴዎስ 1:1፤ ሉቃስ 2:4

ነገር ግን እነዚህ ቤተሰቦች ስማቸውን ከይሖዋ ያገኙት እንዴት ነው? ይሖዋ እንደ አብርሃምና ይስሐቅ የቤተሰብ ራስ ለሆኑ ሰዎች ቃል በቃል ስም ያወጣበት ጊዜ በጣት የሚቆጠር ነው። (ዘፍጥረት 17:5, 19) የእነዚህ ሰዎች ሁኔታ የተለየ ነበር። በተቀረ ግን ይሖዋ ለእያንዳንዱ ቤተሰብ ከልጅ ወደ ልጅ የሚተላለፍ ስም አያወጣም።

ቢሆንም ይሖዋ አዳምንና ሔዋንን “ብዙ፣ ተባዙ፣ ምድርንም ሙሉአት” ብሎ ባዘዛቸው ጊዜ ሰብዓዊ ቤተሰብ መሥርቷል። (ዘፍጥረት 1:28) ከዚህም በተጨማሪ ፍጹም ያልሆኑት አዳምና ሔዋን ልጅ እንዲወልዱ በመፍቀድ ለሰብዓዊ ቤተሰብ መሠረት ጥሏል። (ዘፍጥረት 5:3) ስለዚህ አምላክ የቤተሰብ ስሞች መገኛ ተብሎ የሚጠራበት የተለያዩ መንገዶች አሉ።

በዛሬው ጊዜ በአብዛኞቹ አገሮች የቤተሰብን ስም ከትውልድ ወደ ትውልድ ማስተላለፍ እየቀረ ነው። ሆኖም በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ይሖዋ ቤተሰብ የሚባለውን መዋቅር ስላዘጋጀ ከማመስገናቸውም በላይ የቤተሰባቸውን ኑሮ የተሳካ ለማድረግ ጠንክረው በመሥራት ከፍ ከፍ ያደርጉታል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ