የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w02 1/1 ገጽ 3-4
  • የመደብ ልዩነት የፈጠረው ችግር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመደብ ልዩነት የፈጠረው ችግር
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ተስፋ ሰጭ ጭላንጭል ይኖር ይሆን?
  • የመደብ ልዩነት የሌለበት ኅብረተሰብ መፍጠር ይቻል ይሆን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • በጊዜያችን የተንሰራፋው የእኩልነት አለመኖር መቅሰፍት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • የዘር እኩልነት የሚሰፍንበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • የመጠበቂያ ግንብ የትምህርት ማዕከል ሚስዮናውያንን እያሠለጠነ ይልካል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
w02 1/1 ገጽ 3-4

የመደብ ልዩነት የፈጠረው ችግር

“እኩልነት እንደ መብት ሊቆጠር የሚችል ቢሆንም በምድር ላይ ይህን እውን ሊያደርግ የቻለ ምንም ኃይል የለም።”

ይህን የተናገሩት ኦኖሬ ድ ባልዛክ የተባሉ የ19ኛው መቶ ዘመን ፈረንሳዊ የልብ ወለድ ደራሲ ናቸው። አንተስ ከእርሳቸው አባባል ጋር ትስማማለህ? ብዙዎች የመደብ ልዩነት ትክክል እንዳልሆነ ይሰማቸዋል። ሆኖም በዚህ በ21ኛው መቶ ዘመን እንኳን ሳይቀር ሰብዓዊው ኅብረተሰብ በአያሌ ማኅበራዊ መደቦች በመሰነጣጠር ላይ ይገኛል።

ከ1923 እስከ 1929 ድረስ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የነበሩት ካልቪን ኩሊጅ ማኅበራዊው የመደብ ክፍፍል ለፈጠረው ችግር አሳስቧቸው ስለነበር “ወደፊት የመኳንንት መደብ ፈጽሞ አይኖርም” በማለት ተናግረው ነበር። ይሁን እንጂ ኩሊጅ በፕሬዚዳንትነት ካገለገሉ ከ40 ዓመት በኋላ ከዘር ጋር የተያያዙ ሁኔታዎችን እንዲያጠና የተቋቋመው የከርነር ኮሚሽን፣ ዩናይትድ ስቴትስ “ፈጽሞ በተለያዩና እኩል ባልሆኑ በጥቁርና በነጭ” መደቦች መከፈልዋ እንደማይቀር የተሰማውን ፍርሃት ገልጿል። አንዳንዶች ይህ ትንቢት በአሁኑ ጊዜ ፍጻሜውን እንዳገኘና በዚያች አገር ውስጥ “በኢኮኖሚና በዘሮች መካከል ያለው ልዩነት ይበልጥ እየሰፋ መምጣቱን” ይናገራሉ።

በሰው ልጆች መካከል እኩልነትን ማስፈን ይህን ያህል አስቸጋሪ የሆነው ለምንድን ነው? ትልቅ እንቅፋት የሆነው የራሱ የሰው ልጅ ባሕርይ ነው። የዩ ኤስ ምክር ቤት አባል የነበሩት ዊልያም ራንዶልፍ ኸርስት በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ተናግረዋል:- “ሰዎች ሁሉ ቢያንስ በአንድ ነገር እኩል ሆነው ተፈጥረዋል። ይህም ከሌሎች ጋር እኩል ላለመሆን ያላቸው ፍላጎት ነው።” እንዲህ ሲሉ ምን ማለታቸው ነው? የ19ኛው መቶ ዘመን ፈረንሳዊ ጸሐፊ ተውኔት ኦንሬ ቤክ “እኩልነትን ማምጣት እንዲህ አስቸጋሪ ያደረገው ነገር እኩል መሆን የምንፈልገው ከሚበልጡን ሰዎች ጋር ብቻ መሆኑ ነው” በማለት ጉዳዩን ይበልጥ ግልጽ አድርገውታል። በሌላ አነጋገር ሰዎች እኩል መሆን የሚፈልጉት በሕብረተሰቡ ውስጥ ከእነርሱ የሚበልጥ ደረጃ ካላቸው ሰዎች ጋር ነው። ሆኖም ብዙዎቹ የበታች አድርገው ከሚቆጥሯቸው ሰዎች ጋር እኩል ለመሆን ሲሉ ካሉበት ደረጃ ዝቅ ለማለትና ጥቅማቸውን መሥዋዕት ለማድረግ ፈቃደኞች አይሆኑም።

ድሮ ድሮ ሰዎች ከተራ ቤተሰብ፣ ከመኳንንት ቤተሰብ ወይም ከንጉሣን ቤተሰብ ይወለዱ ነበር። ይህ አሁንም ቢሆን በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ይታያል። ይሁን እንጂ ዛሬ በብዙ አገሮች ውስጥ አንድን ሰው ከዝቅተኛ፣ ከመካከለኛ ወይም ከከፍተኛ መደብ የሚያስፈርጀው ገንዘብ ማግኘቱ ወይም ማጣቱ ነው። ሆኖም የመደብ ልዩነት እንዲፈጠር የሚያደርጉ እንደ ዘር፣ የትምህርት ደረጃ እንዲሁም መማር አለመማር የመሳሰሉ ሌሎች ምክንያቶችም አሉ። እንዲሁም በአንዳንድ ቦታዎች ሴቶች ዝቅ ተደርገው ስለሚታዩ ጾታም ለመደብ ልዩነት መፈጠር አንድ ራሱን የቻለ ምክንያት ሆኗል።

ተስፋ ሰጭ ጭላንጭል ይኖር ይሆን?

የሰብዓዊ መብት ድንጋጌ አንዳንድ ከፋፋይ መደቦችን ለማስወገድ ረድቷል። በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የፀረ መድልዎ ሕግ ጸድቋል። በደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ በሕግ ታግዷል። ባርነት ርዝራዡ ባይጠፋም በብዙ የዓለም ክፍል የሚታየው ሕገ ወጥ ድርጊት እንደሆነ ተደርጎ ነው። የፍርድ ቤት ውሳኔዎች በተወሰኑ አገሮች ውስጥ የመሬት ባለቤትነትን መብት ለአገሬው ሕዝብ ያስከበሩ ሲሆን የዘር መድልዎን የሚቃወሙ ሕጎች ለአንዳንድ ጭቁን መደቦች እፎይታ አስገኝተዋል።

ታዲያ ይህ ማኅበራዊ የመደብ ልዩነት ማክተሙን ያመለክታል? በጭራሽ። በአሁኑ ጊዜ ያሉ አንዳንድ ማኅበራዊ የመደብ ልዩነቶች የተዳከሙ ሊሆን ቢችልም አዳዲስ ከፋፋይ ልዩነቶች ብቅ ማለት ጀምረዋል። ክላስ ዋርፌር ኢን ዘ ኢንፎርሜሽን ኤጅ የተባለው መጽሐፍ “ሰዎችን ባለ ሀብትና ሠራተኛ ብሎ መከፋፈል እየቀረ ያለ ቢመስልም ይህ የሆነው እነዚህ ሁለት ታላላቅ ጎራዎች ተፈረካክሰው ብሶት የሞላባቸው ሰዎችን ያቀፉ አነስተኛ ቡድኖች በመሆናቸው ነው” ይላል።

የመደብ ልዩነቶች ሰዎችን መከፋፈላቸው የሚያቆምበት ጊዜ ይመጣ ይሆን? የሚቀጥለው ርዕስ እንደሚያሳየው ሁኔታው ተስፋ አስቆራጭ አይደለም።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ