የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w12 1/1 ገጽ 30-31
  • ከክፉ መናፍስት ራስህን ጠብቅ!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከክፉ መናፍስት ራስህን ጠብቅ!
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሰዶምና የገሞራ ጥፋት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ኢየሱስ ተአምራዊ ፈውሶችን አከናውኗል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ኢየሱስ ፈተናን ተቋቁሟል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ኢየሱስ አድማጮቹን አስደነቀ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
w12 1/1 ገጽ 30-31

ለታዳጊ ወጣቶች

ከክፉ መናፍስት ራስህን ጠብቅ!

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።

1 ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።​—ዘፍጥረት 6:1-6⁠ን እና የሐዋርያት ሥራ 19:11-20⁠ን አንብብ።

ኔፊሊሞቹ ምን ዓይነት መልክና ቁመና ያላቸው ይመስልሃል?

․․․․․

በሐዋርያት ሥራ 19:13-16 ላይ የተገለጹት ሰዎች ክፉ መንፈስ ካጋጠማቸው በኋላ ምን የተሰማቸው ይመስልሃል?

․․․․․

2 ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ምርምር ማድረግ የምትችልባቸውን መሣሪያዎች በመጠቀም ስለ ኔፊሊሞች ይበልጥ ለማወቅ ሞክር። እንዲህ ያለ የዓመፀኝነት መንፈስ የተጠናወታቸው ለምን ይመስልሃል?

․․․․․

ክፉ መናፍስት “ትክክለኛ መኖሪያቸውን የተዉት” እንዴት ነው? (ይሁዳ 6⁠ን አንብብ።) የሰው ልጆችን ሚስት ለማድረግ መፈለጋቸው ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ አልፎ ተርፎም አስነዋሪ ድርጊት ነው የምትለው ለምንድን ነው?

․․․․․

ያነበብካቸው ሁለት ዘገባዎች ክፉ መናፍስት የፆታ ብልግናንና ዓመፅን እንደሚወዱ የሚያሳዩት እንዴት ነው?

․․․․․

3 ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለሰፈረው ሐሳብ ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

ክፉ መናፍስት ጨካኞችና ራስ ወዳዶች ስለ መሆናቸው

․․․․․

ልትሠራበት የሚገባ ተጨማሪ ነገር፦

ክፉ መናፍስት ሥጋ መልበስ ባይችሉም በየትኞቹ መንገዶች በአንተ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ሊሞክሩ ይችላሉ?

․․․․․

በአሁኑ ጊዜ የክፉ መናፍስትን ዝንባሌና ፍላጎት የሚያንጸባርቁ ምን ዓይነት መዝናኛዎች አሉ?

․․․․․

ክፉ መናፍስት የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ ለመቋቋም መቁረጥህን በየትኞቹ መንገዶች ማሳየት ትችላለህ? (የሐዋርያት ሥራ 19:18, 19⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

4 ከእነዚህ ታሪኮች ውስጥ ልብህን ይበልጥ የነካው ምንድን ነው? ለምንስ?

․․․․․

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሌሎች ጽሑፎች ለማግኘት የይሖዋ ምሥክሮችን ጠይቅ ወይም www.watchtower.org ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ