የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w12 1/15 ገጽ 3
  • አልተሳሳትክም! ይህ የጥናት እትም ነው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አልተሳሳትክም! ይህ የጥናት እትም ነው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት አዲሱ የጥናት እትም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • በመጠበቂያ ግንብ ላይ የተደረጉ አስደሳች ለውጦች!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • ቀለል ባለ እንግሊዝኛ የተዘጋጀ አዲስ የመጠበቂያ ግንብ እትም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • መጠበቂያ ግንብ ቀለል ባለ ቋንቋ መዘጋጀት ያስፈለገው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
w12 1/15 ገጽ 3

አልተሳሳትክም! ይህ የጥናት እትም ነው

ይህ የጥናት እትም ይበልጥ ማራኪ እንዲሆን ብሎም ውድ የሆነውን የይሖዋን የእውነት ቃል በምታጠናበት ጊዜ ጠቃሚ መሣሪያ እንዲሆንልህ በመጽሔቱ ላይ አንዳንድ ለውጦችን አድርገናል።​—መዝ. 1:2፤ 119:97

መጠበቂያ ግንብን በሁለት እትሞች ማለትም አንዱ የሚበረከት ሌላው ደግሞ ለእኛ ለይሖዋ ምሥክሮችና እድገት እያደረጉ ላሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቻችን እንዲሆን አድርገን ማዘጋጀት ከጀመርን አራት ዓመት አልፏል።

ይሖዋን በማገልገል ረጅም ዓመታት ያሳለፈ አንድ ወንድም የጥናት እትሙን አስመልክቶ እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “የመጀመሪያውን የመጠበቂያ ግንብ የጥናት እትም በተመለከትኩበት ወቅት እጅግ ግሩምና ልብ ውስጥ ዘልቆ የሚገባ መሆኑን ተገነዘብኩ። ጥልቀት ባለው መንገድ የቀረቡት መንፈሳዊ እውነቶች ለእኔ ተብለው እንደተጻፉ ያህል ሆኖ ተሰማኝ። ድንቅ ለሆነው ለዚህ አዲስ ዝግጅት በጣም አመሰግናችኋለሁ።” አንድ ሌላ ወንድም ደግሞ “መጽሐፍ ቅዱሴን ተጠቅሜ በዚህ የጥናት እትም ላይ ጥልቀት ያለው ምርምር የማደርግበትን ውድ ጊዜ የምጠብቀው በጉጉት ነው” በማለት ጽፏል። አንተም ተመሳሳይ ስሜት እንደሚሰማህ እርግጠኞች ነን።

እንደሚታወቀው መጠበቂያ ግንብ መታተም የጀመረው ከ1879 አንስቶ ሲሆን ለዚህን ያህል ጊዜ ያለማቋረጥ ሊታተም የቻለው ይሖዋ በመንፈሱ አማካኝነት ስለረዳን ነው። (ዘካ. 4:6) በእነዚህ 133 ዓመታት ውስጥ በመጠበቂያ ግንብ ሽፋን ላይ በርካታ ለውጦች ተደርገዋል። በ2012 በእያንዳንዱ የጥናት እትም ሽፋን ላይ ምሥክርነት ሲሰጥ የሚያሳይ ሥዕል ይወጣል፤ ይህም ከይሖዋ የተቀበልነውን ስለ አምላክ መንግሥት የተሟላ ምሥክርነት የመስጠቱን ተልእኮ ያስታውሰናል። (ሥራ 28:23) በሽፋኑ ውስጠኛ ክፍል ማለትም በገጽ 2 ላይ ሥዕሉን ለመሥራት የተጠቀምንበትን ፎቶግራፍና ቦታው የት እንደሆነ እንዲሁም በዚያ ምን እየተከናወነ እንዳለ የሚያብራራ አጭር መግለጫ ታገኛለህ። ይህ የመጽሔቱ አዲስ ገጽታ የይሖዋ ምሥክሮች ምሥራቹን “በመላው ምድር” እየሰበኩ መሆኑን ዓመቱን ሙሉ እንድናስታውስ ያደርገናል።​—ማቴ. 24:14

በመጽሔቱ ላይ የተደረጉት ሌሎች ለውጦችስ ምንድን ናቸው? የክለሳ ሣጥኑ ቦታው ተቀይሮ እያንዳንዱ የጥናት ርዕስ በሚጀምርበት ገጽ ላይ እንዲሆን ተደርጓል። ይህም የጥናት ርዕሱን በምታነብበትና በምታጠናበት ጊዜ ትኩረት ልታደርግባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች የትኞቹ እንደሆኑ እንድትገነዘብ ይረዳሃል። እርግጥ ነው፣ የመጠበቂያ ግንብ ጥናት መሪዎች ቀደም ሲል እንደሚያደርጉት በጥናቱ መጨረሻ ላይ ትምህርቱን ለመከለስ በእነዚህ ጥያቄዎች መጠቀማቸውን ይቀጥላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ኅዳጎቹ ትንሽ ሰፋ እንዲሉ መደረጋቸውን እንዲሁም የገጾቹና የአንቀጾቹ ቁጥሮች ተለቅ ተለቅ ተደርገው የተጻፉ መሆናቸውን አስተውለህ ይሆናል።

በዚህ እትም የመጨረሻ ገጾች ላይ እንደተገለጸው በዘመናዊው የይሖዋ ምሥክሮች ታሪክ ውስጥ ስለተፈጸሙ ጉልህ ክንውኖች የሚያስቃኝ “ከታሪክ ማኅደራችን” የተሰኘ አዲስ ዓምድ መውጣት ይጀምራል። በተጨማሪም “ራሳቸውን በፈቃደኝነት አቅርበዋል” በሚል ርዕስ የሕይወት ተሞክሮዎች አልፎ አልፎ ይወጣሉ። እነዚህ ተሞክሮዎች፣ ወንድሞችና እህቶች የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ ሄደው በማገልገል ያገኙትን ደስታና እርካታ ሕያው በሆነ መንገድ የሚገልጹ ይሆናሉ።

በዚህ መጽሔት እየታገዝክ የአምላክን ቃል በማጥናት የምታሳልፈው ጊዜ በጣም አስደሳች እንዲሆንልህ ምኞታችን ነው።

አዘጋጆቹ

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

1879

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

1895

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

1931

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

1950

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

1974

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

2008

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ