የጥናት እትም
ታኅሣሥ 15, 2013
© 2013 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania.
የጥናት እትም
ከየካቲት 3-9, 2014
ገጽ 6 • መዝሙሮች፦ 32, 7
ከየካቲት 10-16, 2014
ገጽ 11 • መዝሙሮች፦ 40, 28
ከየካቲት 17-23, 2014
ገጽ 17 • መዝሙሮች፦ 5, 18
ከየካቲት 24, 2014–መጋቢት 2, 2014
ገጽ 22 • መዝሙሮች፦ 30, 8
የጥናት ርዕሶች
▪ “የማመዛዘን ችሎታችሁ በቶሎ አይናወጥ”!
በግምታዊ ሐሳቦች ወይም ጥርጣሬ እንዲፈጠር በሚያደርጉ አመለካከቶች እንዳንታለልና እንደ እውነት አድርገን እንዳንቀበላቸው መጠንቀቃችን ምንኛ አስፈላጊ ነው! በአንደኛ እና በሁለተኛ ተሰሎንቄ መጻሕፍት ላይ በዚህ ረገድ ወቅታዊ የሆኑ ማሳሰቢያዎችን እናገኛለን።
▪ ለአምላክ መንግሥት መሥዋዕትነት ትከፍላላችሁ?
ከመንግሥቱ ጋር ለተያያዙ ጉዳዮች ቅድሚያ ለመስጠት ብዙ መሥዋዕት መክፈል ያስፈልገናል። በዚህ ርዕስ ላይ በጥንቷ እስራኤል ይቀርቡ ከነበሩ መሥዋዕቶች ምን ትምህርት እንደምናገኝ እንመረምራለን። በተጨማሪም በዛሬው ጊዜ ብዙዎች መንግሥቱን ለመደገፍ ስለሚከፍሉት መሥዋዕት እንመለከታለን።
▪ ‘ይህ ለመታሰቢያ ይሁናችሁ’
▪ ‘ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት’
እውነተኛ ክርስቲያኖች የኢየሱስን ሞት መታሰቢያ የሚያከብሩት አይሁዳውያን ፋሲካን በሚያከብሩበት ወቅት አካባቢ ነው። ስለ ፋሲካ በዓል ማወቅ የሚያስፈልገን ለምንድን ነው? የጌታ ራት መቼ መከበር እንዳለበት ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው? ይህ በዓል ለእያንዳንዳችን ምን ትርጉም አለው?
ሽፋኑ፦ በዚምባብዌ በጣም ግዙፍ ዐለቶችን የተሸከሙ ቋጥኞች (ኮፒ) በብዛት የሚገኙባቸው አካባቢዎች አሉ፤ በእነዚህ አካባቢዎች ተራርቀው ለሚኖሩ ሰዎች መስበክ በጣም አስቸጋሪ ነው። ይሁንና ወንድሞች በማታቤሌላንድ፣ ዚምባብዌ እንዲህ ዓይነት ቋጥኞች በሚገኙበት በማቶቦ ሂልስ ምሥራቹን እየሰበኩ ነው
ዚምባብዌ
የሕዝብ ብዛት፦
12,759,565
አስፋፊዎች፦
40,034
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች፦
90,894
በዚምባብዌ የሚኖሩ ሰዎች ጽሑፎቻችንን ማንበብ ያስደስታቸዋል። እያንዳንዱ የይሖዋ ምሥክር በየወሩ በአማካይ 16 መጽሔቶችን ያበረክታል