የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 2/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ መላውን ምድር የሚያስተዳድር አንድ መንግሥት ያቋቁማል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ሰላማዊው የአምላክ መንግሥት
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
  • ኢየሱስ ወደፊት ምን ያደርጋል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 2/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ዓለም በሙሉ በአንድ መንግሥት የሚተዳደርበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

ከተለያዩ ብሔራት የመጡ ሕዝቦች በአንድ መንግሥት ሥር

ዓለም በአንድ መንግሥት ብቻ በሚተዳደርበት ወቅት የዓለም ሕዝብ አንድነት የሚኖረው እንዴት ነው? ኢሳይያስ 32:1, 17፤ 54:13

ዓለም በአንድ መንግሥት ቢተዳደር የሰው ልጆች ምን ያህል ሊጠቀሙ እንደሚችሉ እስቲ አስበው። በዛሬው ጊዜ ብዙዎች በከፋ ድህነት ሲማቅቁ አንዳንዶች ግን ከልክ በላይ ሀብታም ናቸው። ዓለም በሙሉ የሚተዳደረው በአንድ ጥሩ መንግሥት ቢሆን ኖሮ የዓለም ሕዝብ በሙሉ የሚያስፈልገውን ነገር በበቂ መጠን ማግኘት ይችል ነበር። ታዲያ የሰው ልጆች እንዲህ ያለ መንግሥት ማቋቋም የሚችሉ ይመስልሃል?—ኤርምያስ 10:23⁠ን አንብብ።

ባለፉት ዘመናት፣ መንግሥታት የተገዢዎቻቸውን በተለይም የድሆችን ፍላጎት ማሟላት ሳይችሉ ቀርተዋል። እንዲያውም አንዳንድ መንግሥታት ሕዝባቸውን ይጨቁናሉ። (መክብብ 4:1፤ 8:9) ይሁንና ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ በዓለም ላይ ያሉትን መንግሥታት በሙሉ የሚተካ አንድ መንግሥት እንደሚያቋቁም ቃል ገብቷል። የዚህ መንግሥት ንጉሥ ተገዢዎቹ የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች በሙሉ ያሟላል።—ኢሳይያስ 11:4⁠ን እና ዳንኤል 2:44⁠ን አንብብ።

የአምላክ መንግሥት ምን ያከናውናል?

ይሖዋ አምላክ ከሁሉ የተሻለውን ገዢ ማለትም ልጁን ኢየሱስን የዚህ መንግሥት ንጉሥ አድርጎ ሾሞታል። (ሉቃስ 1:31-33) ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት ሰዎችን መርዳት ያስደስተው ነበር። ወደፊት ንጉሥ ሲሆን ደግሞ የዓለምን ሕዝብ በሙሉ የሚገዛ ሲሆን መከራን ያስወግዳል።—መዝሙር 72:8, 12-14⁠ን አንብብ።

ሁሉም ሰዎች ኢየሱስን ንጉሣቸው አድርገው ይቀበሉታል? በፍጹም። ያም ሆኖ ይሖዋ ትዕግሥተኛ ነው። (2 ጴጥሮስ 3:9) ሰዎች ኢየሱስን ገዢያቸው አድርገው እንዲቀበሉት አጋጣሚ እየሰጣቸው ነው። በቅርቡ ግን ኢየሱስ ክፉ ሰዎችን ከምድር ላይ የሚያጠፋ ሲሆን ሰላምና ደኅንነት እንዲሰፍን ያደርጋል።—ሚክያስ 4:3, 4⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 8 ተመልከት

መጽሐፉ www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ