የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp16 ቁጥር 3 ገጽ 4
  • ማዘን ስህተት ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማዘን ስህተት ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እንዲህ የሚሰማኝ የጤና ነው?
    የምትወዱት ሰው ሲሞት
  • ሐዘን ለደረሰባቸው የሚሆን እርዳታ
    ንቁ!—2018
  • ከሐዘኔ ልጽናና የምችለው እንዴት ነው?
    የምትወዱት ሰው ሲሞት
  • ሐዘንን መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?
    የወጣቶች ጥያቄ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
wp16 ቁጥር 3 ገጽ 4

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | የምትወደውን ሰው በሞት ስታጣ

ማዘን ስህተት ነው?

ለአጭር ጊዜ ታመህ ታውቃለህ? ምናልባትም ቶሎ ከመዳንህ የተነሳ ሁኔታውን ሙሉ በሙሉ ረስተኸው ሊሆን ይችላል። ሐዘን ግን እንዲህ በቀላሉ የሚረሳ ነገር አይደለም። ዶክተር አለን ውልፌልት ሂሊንግ ኤ ስፓውዝስ ግሪቪንግ ኸርት በተባለው መጽሐፋቸው ላይ “‘ሐዘንን መርሳት’ ብሎ ነገር የለም” ሲሉ ጽፈዋል። አክለው ግን “በጊዜ ሂደት እና ሌሎች በሚሰጧችሁ እርዳታ ሐዘኑ እየቀለላችሁ ይመጣል” ብለዋል።

ለምሳሌ ያህል፣ የቤተሰብ ራስ የነበረው አብርሃም ሚስቱ ሣራ ስትሞት የተሰማውን ስሜት እንመልከት። መጽሐፍ ቅዱስ “አብርሃምም በሣራ ሞት ያዝንና ያለቅስ ጀመር” ይላል። “ጀመር” የሚለው ቃል አብርሃም ከሐዘኑ ለመጽናናት የተወሰነ ጊዜ እንደፈጀበት ያሳያል።a ሌላው ምሳሌ ደግሞ ያዕቆብ ነው፤ ያዕቆብ ልጁ በአውሬ እንደተበላ የተነገረውን የሐሰት ወሬ አምኖ በመቀበሉ “ለብዙ ቀናት” አልቅሷል። እንዲያውም የቤተሰቡ አባላት ሊያጽናኑት አልቻሉም። ዓመታት ካለፉ በኋላም የዮሴፍ ሞት ያደረሰበት ሐዘን ከልቡ አልወጣም።—ዘፍጥረት 23:2፤ 37:34, 35፤ 42:36፤ 45:28

አብርሃም ከሣራ አስክሬን አጠገብ ሆኖ ሲያለቅስ

አብርሃም የሚወዳት ሚስቱ ሣራ ስትሞት በጣም አዝኗል

በዛሬው ጊዜ፣ የሚወዱትን ሰው በሞት ያጡ ሰዎችም ተመሳሳይ ሁኔታ ያጋጥማቸዋል። የሚከተሉትን ሁለት ምሳሌዎች እንመልከት።

  • “ባለቤቴ ሮበርት የሞተው ሐምሌ 9, 2008 ነው። ለሞት የዳረገው አደጋ በደረሰበት ዕለት ጠዋት የነበረው ሁኔታ ከሌሎች ቀናት የተለየ አልነበረም። ቁርስ በልተን ስንጨርስ ሁሌ ወደ ሥራ ሲሄድ እንደምናደርገው ተቃቅፈን ከተሳሳምን በኋላ ‘እወድሃለሁ’ ‘እወድሻለሁ’ ተባብለን ተለያየን። ከስድስት ዓመታት በኋላም ሐዘኑ ከውስጤ አልወጣም። ሮብን ማጣቴ ካስከተለብኝ ሐዘን መቼም ቢሆን የምጽናና አይመስለኝም።”—ጌል፣ ዕድሜ 60

  • “የምወዳት ባለቤቴን በሞት ካጣሁ 18 ዓመት አልፎኛል፤ ያም ሆኖ አሁንም ልቤ ውስጥ አለች፤ ሐዘኑም ቢሆን አለቀቀኝም። በአካባቢዬ ውብ የሆነ ተፈጥሮ ባየሁ ቁጥር ትዝ ትለኛለች፤ በሕይወት ኖራ እኔ የማየውን ነገር ብታይ ምን ያህል ልትደሰት እንደምትችል አስባለሁ።”—ኤይቴና፣ ዕድሜ 84

እንዲህ ያለ ከባድ ጉዳት የሚያደርስና ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ ስሜት መኖሩ ተፈጥሯዊ ነው። ሰዎች ሐዘናቸውን የሚገልጹበት መንገድ ከሰው ሰው ስለሚለያይ ሌሎች አሳዛኝ ሁኔታ ሲገጥማቸው በሚሰጡት ምላሽ ላይ መፍረድ ተገቢ አይደለም። በሌላ በኩል ደግሞ ሐዘናችን ከልክ እንዳለፈ በሚሰማን ጊዜ ራሳችንን ከመኮነን መቆጠብ ይኖርብናል። ታዲያ የደረሰብንን ሐዘን መቋቋም የምንችለው እንዴት ነው?

a የአብርሃም ልጅ ይስሐቅም ቢሆን ከደረሰበት ሐዘን ለመጽናናት ረጅም ጊዜ ወስዶበታል። በዚህ እትም ውስጥ ከሚገኘው “በእምነታቸው ምሰሏቸው” ከሚለው ርዕስ መረዳት እንደምንችለው ይስሐቅ እናቱ ሣራ ከሞተች ከሦስት ዓመታት በኋላም ሐዘኑ አልወጣለትም ነበር።—ዘፍጥረት 24:67

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ