የርዕስ ማውጫ
ከግንቦት 29, 2017–ሰኔ 4, 2017 ባለው ሳምንት
ለይሖዋ የትኞቹን ስእለቶች ተስለሃል? ስእለትህን ለመፈጸም የምትችለውን ሁሉ እያደረግክ እንደሆነ ይሰማሃል? ራስህን ስትወስን ወይም ትዳር ስትመሠርት የገባኸውን ቃልስ ጠብቀህ እየኖርክ ነው? ይህ ርዕስ ለአምላክ የገቡትን ቃል በመጠበቅ ረገድ ዮፍታሔና ሐና የተዉትን ግሩም ምሳሌ ያብራራል፤ ይህን መመርመራችን እኛም ለአምላክ የገባነውን ቃል ለመጠበቅ ይረዳናል።
ከሰኔ 5-11, 2017 ባለው ሳምንት
9 የአምላክ መንግሥት ሲመጣ የትኞቹ ነገሮች ይወገዳሉ?
ብዙውን ጊዜ የምናስበው ይሖዋ በገነት ውስጥ ስለሚሰጠን ነገሮች ነው፤ በዚህ ርዕስ ውስጥ ግን ይሖዋ የሚያስወግዳቸውን ነገሮች እንመለከታለን። ይሖዋ ሰላም የሰፈነበትና አስደሳች ዓለም ለማምጣት የትኞቹን ነገሮች ያስወግዳል? የዚህን ጥያቄ መልስ መመልከታችን እምነታችንን የሚያጠናከረው ከመሆኑም ሌላ ለመጽናት የሚያስችል ኃይል ይሰጠናል።
14 የሕይወት ታሪክ—የክርስቶስ ወታደር ለመሆን ቁርጥ ውሳኔ አድርጌያለሁ
ከሰኔ 12-18, 2017 ባለው ሳምንት
18 “የምድር ሁሉ ዳኛ” ምንጊዜም ትክክል የሆነውን ነገር ያደርጋል
ከሰኔ 19-25, 2017 ባለው ሳምንት
23 ስለ ፍትሕ የይሖዋ ዓይነት አመለካከት አለህ?
በራሳችንም ሆነ በሌላ ሰው ላይ የፍትሕ መጓደል እንደተፈጸመ ሲሰማን እምነታችን፣ ትሕትናችንና ታማኝነታችን ሊፈተን ይችላል። እነዚህ የጥናት ርዕሶች ፍትሕን በተመለከተ የይሖዋ ዓይነት አመለካከት ለማዳበር የሚረዱንን ሦስት ምሳሌዎች ያብራራሉ።
ከሰኔ 26, 2017-ሐምሌ 2, 2017 ባለው ሳምንት
28 የምታሳዩት የፈቃደኝነት መንፈስ ለይሖዋ ውዳሴ ያመጣል!
ይሖዋ ምንም የሚጎድለው ነገር የለም፤ ያም ሆኖ ሉዓላዊነቱን የመደገፍ ልባዊ ፍላጎት እንዳለን መመልከት ያስደስተዋል። መሳፍንት ምዕራፍ 4 እና 5 ይሖዋ፣ እሱ የሚሰጠንን ግልጽ መመሪያ በተግባር ለማዋል የምናደርገውን ጥረት ከፍ አድርጎ እንደሚመለከተው ያሳያል።