የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp19 ቁጥር 2 ገጽ 4-5
  • የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ማወቅ ተስፋን ያለመልማል
  • ዝግጁ ናችሁ?
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2020
  • የሚያስጨንቃችሁን ነገር ሁሉ በይሖዋ ላይ ጣሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • በአሰቃቂ ሁኔታ ሳቢያ የሚፈጠር ጭንቀት የማይኖርበት ጊዜ ይመጣል!
    ንቁ!—2002
  • ጭንቀትን መቋቋም የምትችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
wp19 ቁጥር 2 ገጽ 4-5
ሁለት ሰዎች ከአንድ የፈራረሰ ሕንፃ አጠገብ ተቀምጠው

የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም

“መጀመሪያ ላይ ሙሉ በሙሉ ተስፋ ቆርጠን ነበር። በአካባቢያችን በተከሰተው የመሬት መንሸራተትና ጎርፍ ምክንያት ንብረታችን ሁሉ ወድሞ ነበር።”—አንድሩ፣ ሴራ ሊዮን

“አውሎ ነፋሱ ካቆመ በኋላ ወደ ቤታችን ተመለስን። ምንም የተረፈ ነገር አልነበረም። በድንጋጤ ክው ብለን ቀረን። ልጄ ተንበርክካ ማልቀስ ጀመረች።”—ዴቪድ፣ ቨርጅን ደሴቶች

አንተም የተፈጥሮ አደጋ አጋጥሞህ የሚያውቅ ከሆነ ተመሳሳይ ሁኔታ ያጋጠማቸው ሰዎች የሚሰማቸውን ስሜት መረዳት አይከብድህ ይሆናል፤ እነዚህ ሰዎች በድንጋጤ ሊዋጡ፣ የተከሰተውን ነገር መቀበል ሊከብዳቸው፣ ግራ ሊጋቡ፣ ሊጨነቁ አልፎ ተርፎም በቅዠት ሊሠቃዩ ይችላሉ። የተፈጥሮ አደጋ የደረሰባቸው በርካታ ሰዎች ተስፋ ከመቁረጣቸው የተነሳ በሕይወት የመኖር ፍላጎታቸው ሊሟጠጥ ይችላል።

በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ያለህን ሁሉ ስታጣ ሁኔታው ከአቅምህ በላይ እንደሆነ ሊሰማህ ይችላል። አልፎ ተርፎም በሕይወት መኖርህ ምንም ዋጋ እንደሌለው ይሰማህ ይሆናል። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ሕይወት ዋጋ እንዳለው ይገልጻል፤ በተጨማሪም ወደፊት የተሻለ ጊዜ ይመጣል ብለህ ተስፋ እንድታደርግ የሚያስችል አሳማኝ ማስረጃ ይዟል።

የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ማወቅ ተስፋን ያለመልማል

መክብብ 7:8 “የአንድ ነገር ፍጻሜ ከጅማሬው ይሻላል” ይላል። የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥምህ፣ መጀመሪያ ላይ ሁሉም ነገር ጭልምልም ይልብህ ይሆናል። ወደ ቀድሞ ሕይወትህ ለመመለስ በትዕግሥት ጥረት ማድረግህን ስትቀጥል ግን ሁኔታዎች እየተሻሻሉ ሊሄዱ ይችላሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ “የለቅሶ ድምፅም ሆነ የጭንቅ ጩኸት [የማይሰማበት]” ጊዜ እንደሚመጣ ይናገራል። (ኢሳይያስ 65:19) በአምላክ መንግሥት አገዛዝ ሥር ምድር ወደ ገነትነት ስትለወጥ ይህ ትንቢት ፍጻሜውን ያገኛል። (መዝሙር 37:11, 29) በዚያን ጊዜ የተፈጥሮ አደጋ የሚባል ነገር አይኖርም። በተጨማሪም አደጋው ያስከተላቸው መጥፎ ትዝታዎችም ሆኑ አካላዊ ጠባሳዎች ለዘላለም ይወገዳሉ፤ ምክንያቱም ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ “የቀድሞዎቹ ነገሮች አይታሰቡም፤ ወደ ልብም አይገቡም” በማለት ቃል ገብቷል።—ኢሳይያስ 65:17

እስቲ አስበው፦ ፈጣሪ “የተሻለ ሕይወትንና ተስፋን” ሊሰጥህ ዝግጅት አድርጓል፤ ወደፊት፣ ፍጹም በሆነው አገዛዙ ሥር ሰላም የሰፈነበት ሕይወት ይሰጥሃል። (ኤርምያስ 29:11) ታዲያ ይህን እውነት ማወቅህ ተስፋህን ሊያለመልመው ይችላል? በመጀመሪያው ርዕስ ላይ የተጠቀሰችው ሳሊ እንዲህ ብላለች፦ “የአምላክ መንግሥት ወደፊት የሚያመጣልንን አስደሳች ነገሮች ማሰባችን፣ የደረሱብንን አሳዛኝ ነገሮች ወደኋላ ትተን ወደፊት እንድንራመድ ይረዳናል።”

ታዲያ የአምላክ መንግሥት በቅርቡ ለሰው ልጆች ስለሚያመጣቸው በረከቶች ለምን አትማርም? እንዲህ ማድረግህ በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ሕይወትህ ቢመሰቃቀልም ብሩህ አመለካከት ይዘህ እንድትቀጥል እንዲሁም ከአደጋ ነፃ የምንሆንበትን ጊዜ በጉጉት እንድትጠባበቅ ያስችልሃል። መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጣቸውን ምክሮች ተግባራዊ ማድረግህ በዛሬው ጊዜም እንኳ ከተፈጥሮ አደጋ ጋር ተያይዘው የሚመጡትን ችግሮች መቋቋም እንድትችል ይረዳሃል። እስቲ ከእነዚህ ምክሮች መካከል አንዳንዶቹን ተመልከት።

ሊረዱህ የሚችሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

በቂ እረፍት አድርግ።

“ብዙ በመልፋትና ነፋስን በማሳደድ ከሚገኝ ሁለት እፍኝ ይልቅ ጥቂት እረፍት በማድረግ የሚገኝ አንድ እፍኝ ይሻላል።”—መክብብ 4:6

ተመራማሪዎች እንደሚናገሩት አንድ ሰው አሰቃቂ ነገር ካጋጠመው በኋላ ባሉት ጊዜያት “ጥሩ እንቅልፍ የማይተኛ ከሆነ . . . የደረሰበት የስሜት ቀውስ ሊባባስና ስሜታዊ ሚዛኑን ለመጠበቅ ሊቸገር ይችላል።” በመሆኑም በቂ እረፍት ማድረግ የጥበብ እርምጃ ነው።

ስሜትህን አውጥተህ ተናገር።

“በሰው ልብ ውስጥ ያለ ጭንቀት ልቡ እንዲዝል ያደርገዋል [ወይም “የመንፈስ ጭንቀት ያስከትልበታል፣” የግርጌ ማስታወሻ]፤ መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል።”—ምሳሌ 12:25

የሚሰማህን ስሜት ለቤተሰብህ አባል ወይም ለቅርብ ወዳጅህ ተናገር። እነዚህ ሰዎች በትኩረት የሚያዳምጡህ ከመሆኑም ሌላ ሊያበረታቱህና ተግባራዊ እርዳታ ሊሰጡህ ይችላሉ።a

ወደፊት በሚመጣው የተሻለ ጊዜ ላይ ትኩረት አድርግ።

“አምላክ በገባው ቃል መሠረት አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር እንጠባበቃለን፤ በእነዚህም ውስጥ ጽድቅ ይሰፍናል።”—2 ጴጥሮስ 3:13

a ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ውጥረት ወይም ከባድ ጭንቀት ያጋጠመው ሰው የሕክምና እርዳታ ማግኘት ሊያስፈልገው ይችላል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ