የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/93 ገጽ 2
  • “የመጋቢት የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “የመጋቢት የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • ንዑስ ርዕሶች
  • መጋቢት 1 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 8 የሚጀምር ሳምንት
  • መዝሙር 13
  • መጋቢት 15 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 22 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
km 3/93 ገጽ 2

“የመጋቢት የአገልግሎት ስብሰባዎች

መጋቢት 1 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 10

15 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎችና በመንግሥት አግልግሎታችን ላይ የወጡ ማስታወቂያዎች። “የአምላክን ቃል መቀበል፣ በሥራ ላይ ማዋልና ከእርሱ መጠቀም” በሚለው ርዕሰ ትምህርት ላይ በጥያቄና መልስ የሚደረግ ውይይት።

15 ደቂቃ፦ “‘ና!’ ማለትህን ቀጥል” በጥያቄና መልስ የሚሸፈን። አንቀጽ 4⁠ን በምታብራራበት ጊዜ ራእይ ታላቁ መደምደሚያው በተባለው መጽሐፍ ላይ ራእይ 21:4–6⁠ን የሚያብራሩትን ምዕራፍ 42 አንቀጽ 6–10 ድረስ ያሉትን ጎላ ያሉ ሐሳቦች በደንብ ዝግጅት ያደረገ አንድ አስፋፊ እንዲያቀርብ አድርግ።

15 ደቂቃ፦ “የአገልግሎት ስልታችሁን የምትቀያይሩ ሁኑ።” በጥቂቱ የአድማጮች ተሳትፎ ያለበት ንግግር። ከአንቀጽ 3–5 ያለውን በምታብራራበት ጊዜ ሁለት አጠር አጠር ያሉ ትዕይንቶችንም አቅርብ። በአንቀጽ 4 እና 5 ላይ ያለውን ሐሳብ በትዕይንት ስታቀርብ በርዕሰ ትምህርቱ ላይ ባለው መሠረት አንድ በዕድሜ ከፍ ያለ አስፋፊና ሌላ በዕድሜ አነስ ያለ ወጣት ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት እንዴት አብረው ሊሠሩ እንደሚችሉ አሳይ። ውጤቱ ምንም ይሁን ምን በአገልግሎት ደስታ የማግኘትን አስፈላጊነት አጥብቀህ ግለጽ።

መዝሙር 215 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 8 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 13

7 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎችና ቲኦክራቲካዊ ዜናዎች ውስጥ ያሉትን ጎላ ያሉ ሐሳቦች አቅርብ። በሚያዝያ ረዳት አቅኚ እንዲሆኑ የተፈቀደላቸውን አስፋፊዎች ቁጥር ጥቀስ። አቅኚ ለመሆን ዕቅድ ያላቸው የአቅኚነት ማመልከቻቸውን አስቀድመው እንዲሰጡ አበረታታ።

18 ደቂቃ፦ “ይሖዋን ለማክበር አሁን ከምታደርገው የበለጠ ለመሥራት ትችላለህን?” ከአንቀጽ 1 እስከ 10 ላይ በጥያቄና መልስ የሚደረግ ውይይት።

20 ደቂቃ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችንን መደገፍ። ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን ጥናት ከመምራታችንም በተጨማሪ እርዳታ የመስጠትን አስፈላጊነት በማጥበቅ ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። (1 ተሰ. 2:8) በስብሰባዎች ላይ ለመገኘትና በዚያም ለመሳተፍ ልባዊ ስሜት እንዲኖራቸው ፍላጎታቸውን ለመቀስቀስ ተጨማሪ ሰዓት ውሰድ። ስለ ክልል ስብሰባዎች፣ የልዩ ስብሰባ ቀናትና የወረዳ ስብሰባዎች በማብራራት ለድርጅቱና ለዓለም አቀፍ ወንድማማችነት ያላቸውን አድናቆት ገንባ። የይሖዋ ምስክሮችና ከስሙ በስተጀርባ ያለው ድርጅት፣ ወይን ጠጅ ትራያንግሎች እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ — ትክክለኛ ታሪክና እምነት ሊጣልባቸው የሚቻል ትንቢቶች ያሉት መጽሐፍ የተባሉትን የቪድዮ ፊልሞች አብራችሁ በመመልከት ተማሪው ከነዚህ ፊልሞች ምን እንደተማረ ልትጠይቀው ትችል ይሆናል። የተማሩትን ነገር መደበኛ ባልሆነ መንገድ እንዴት አድርገው ለሌሎች ማካፈል እንደሚችሉ ቀስ በቀስ አሳያቸው። በአገልግሎታችን መጽሐፍ ገጽ 51ና 52 ላይ ያሉትን ብቃቶች የሚያሟሉና ለሕዝብ በሚደረገው አገልግሎት ተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ለመሆን እንዲችሉ እርዳታ ሊደረግላቸው ይገባል። በጥናቱ ወቅትና ከዚያ በኋላ ተማሪው ራሱን የመወሰንና የመጠመቅ ፍላጎት እንዲያዳብር እርዳታ ለማድረግ የተወሰነ ሰዓት ማጥፋቱ አስፈላጊ ነው። በስብሰባዎቻችን ላይ ስለተደረጉት ጥምቀቶች የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን ወይም ጋዜጣ ላይ የወጡ ርዕሶችን ለተማሪው ማሳየት ይቻላል። ትዕይንት:- አስፋፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ መደበኛ ላልሆነ ምስክርነት ለመዘጋጀት እርዳታ ያደርግለታል። ለዘላለም መኖር ከተባለው መጽሐፍ ውስጥ ለመስክ አገልግሎት የሚሆኑ ነጥቦችን ይመርጥና “ይህንን ነጥብ ለአንዳንድ ዘመዶችህ ወይም ጎረቤቶችህ ብታካፍላቸው መልካም ይሆናል። ከአሁን በፊት የማታውቀውን ነገር ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደተማርክ ልትጠቅስላቸው ትችላለህ” ይለዋል። አስፋፊዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻቸው ከተጠመቁ በኋላም እንኳን ቢሆን ፍቅራዊ እንክብካቤ በማድረግ እንዲረዷቸው አበረታታ።

መዝሙር 34 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 15 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 136

10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች፣ የሒሳብ ሪፖርትና ለተደረገው መዋጮ የተላከውን ምስጋና ጨምረህ አቅርብ። በገጽ 7 ላይ ያለውን “ወቅታዊ መልእክት” የሚለውን አንብብ። ሁሉም መጋቢት 28 ላይ የሚቀርበውን ልዩ ንግግር ርዕስ በማስታወሻቸው ላይ ጽፈው ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ንግግሩን እንዲያዳምጡ እንዲጋብዟቸው አበረታታ።

15 ደቂቃ፦ “ፍላጎት ያሳዩትን ሁሉ መርዳት።” በጥቂቱ የአድማጮች ተሳትፎ ያለበት ንግግር። ጊዜ ካለህ አውጥተህ እንድታያቸው የቀረቡትን ጥቅሶች አንብባቸው። በአንቀጽ 3 ላይ በቀረቡት ሐሳቦች ላይ ትዕይንት አቅርብ። ለመጀመሪያ ጊዜ በስብሰባው ላይ የተገኙት ሰዎች ያሳዩትን ፍላጎት መከታተል አስፈላጊ መሆኑን አጉላ።

20 ደቂቃ፦ “ይሖዋን ለማክበር አሁን ከምታደርገው የበለጠ ለመሥራት ትችላለህን?” ከአንቀጽ 11 እስከ 22 ድረስ በጥያቄና መልስ የሚደረግ ውይይት።

መዝሙር 53 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 22 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 155

10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። የጥያቄ ሣጥን። በሚያዝያ ወር ሁሉም በአገልግሎቱ ከፍ ያለ ተሳትፎ እንዲኖራቸው አበረታታ።

20 ደቂቃ፦ በዕድሜ የገፉትን መንከባከብ። ውይይትና በሁለት ወንድሞች የሚደረግ ቃለ ምልልስ። “ብርሃን አብሪዎች” በተባለው የወረዳ ስብሰባ ላይ ቅዳሜ ጠዋት የቀረበው ተከታታይ ንግግር “በክርስቲያን ቤት ውስጥ እርስ በርስ መተሳሰብ” የሚለውን አጠቃላይ መልእክት ያጎላ ነበር። “በዕድሜ የገፉትን በመንከባከብ” የተባለው የማጠቃለያ ክፍል በዕድሜ የገፉ ሰዎች ለቤተሰቡና ለጉባኤው የሚያበረክቱትን ጠቃሚ አስተዋፅዖ አጉልቷል። (ምሳሌ 16:31) አዛውንቶችን በምን በምን መንገዶች ልንደግፋቸው እንችላለን? የመጀመሪያ ኃላፊነት ያለበት ቤተሰቡ ነው። (1 ጢሞ. 5:3, 4, 8, 16) ትዕግሥትና ርኅራኄ ያስፈልጋሉ። ያደጉ ልጆችና የልጅ ልጆች ወላጆቻቸውና አያቶቻቸው እነርሱን ለማሳደግ ያሳለፏቸውን የፍቅር፣ የሥራና የእንክብካቤ ዓመታት ያላቸውን አድናቆት ለማሳየት አጋጣሚ ያገኛሉ። (መግ 11–108 ገጽ 15–21) ጉባኤውም ቢሆን በዕድሜ የገፉትን ለመርዳት ይችላል። አንዳንዶች የመንግሥትን እርዳታ ለማግኘት እንዲችሉ እርዳታ እንዲደረግላቸው ያስፈልግ ይሆናል። ለምግብ ጊዜና ለመጨዋወት በምታደርጓቸው ስብሰባዎች ላይ አብረዋችሁ እንዲሆኑ በመጋበዝ እንግዳ ተቀባይነታችሁን አሳዩ። (ሮሜ 12:13) በመስክ አገልግሎት ላይ እርዳታ አድርጉላቸው። ወደ ጉባኤ ስብሰባዎችና ትልልቅ ስብሰባዎች በመኪና ውሰዷቸው። በመገብየትና ቤታቸውን በማጽዳት እርዷቸው። (መግ 11–108 ገጽ 4–7) በዕድሜ ለገፉ ሰዎች ሁልጊዜ አክብሮት አሳዩ። (1 ጢሞ. 5:1, 2) ጥሩ ምሳሌ ለሆኑ አንድ ወይም ሁለት አዛውንቶች ቃለ ምልልስ አድርግላቸው። ቤተሰባቸውና ጉባኤያቸው ካሳያቸው ደግነት እንዴት እንደተጠቀሙ አጉላ።

15 ደቂቃ፦ በሚያዝያ ረዳት አቅኚ ከሚሆኑ ወይም ባለፈው ጊዜ ረዳት አቅኚ ከነበሩ ሦስት ወይም አራት አስፋፊዎች ጋር አንድ ሽማግሌ የሚያደርገው ቃለ ምልልስ። አቅኚ እንዲሆኑ ያነሳሳቸው ምንድን ነው? ለሚያዝያ ምን ዕቅድ አውጥተዋል? ረዳት አቅኚነት እነሱን በግላቸው የረዳቸው እንዴት ነው? በሚቀጥለው ወር ረዳት አቅኚ ለመሆን ያቀዱ ሁሉ ማመልከቻውን እንዲወስዱና በቶሎ ሞልተው እንዲመልሱት አበረታታ።

መዝሙር 172 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 29 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 105

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ፍላጎት ያላቸውን ሰዎችና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻቸውን በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ እንዲጋብዟቸው ሁሉንም አሳስባቸው። የታተሙትን የግብዣ ወረቀቶች በጥሩ ሁኔታ ተጠቀሙባቸው። አስፋፊዎች በግብዣ ወረቀቶቹ ላይ የመታሰቢያው በዓል የሚከበርበትን ሰዓትና ቦታ በንጽሕና እንዲጽፉበት አበረታታ።

25 ደቂቃ፦ “የዘላለም ሕይወት ተስፋ የሚሰጠውን ሞት ለማስታወስ የተዘጋጀውን በዓል ማክበር።” በመሪ የበላይ ተመልካቹ በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። “ለመታሰቢያው በዓል የሚደረግ ዝግጅት” በሚለው ሣጥን ውስጥ ያለውንም ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ። አምስተኛውን አንቀጽ ከተመለከታችሁ በኋላ አንድ አስፋፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱን ወደ መታሰቢያው በዓል ሲጋብዘው የሚያሳይ ትዕይንት አቅርብ። አስፋፊው ከሚያዝያ 1–6 ባለው ጊዜ ውስጥ እንዲነበቡ ስለተዘጋጁት የተመረጡ ጥቅሶች ያብራራለታል። በመኪና ሊወስደው እንደሚችልም ሐሳብ ያቀርብለታል።

10 ደቂቃ፦ በሚያዝያ መጠበቂያ ግንብ አበርክቱ። በወሩ ውስጥ ልንጠቀምባቸው የምንችላቸውን የተለዩ የመነጋገሪያ ነጥቦችና ርዕሶችን አጉላ። በእያንዳንዱ አጋጣሚ በመጽሔቶች ላይ ወዳሉት ነጥቦች ቀጥተኛ ትኩረትን ለመሳብ ንቁ ሁን።

መዝሙር 19 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ