“ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች በመጋቢት፦ ራእይ — ታላቁ መደምደሚያው ቀርቧል! (እንግሊዝኛ) በሚያዝያና በግንቦት፦ መጠበቂያ ግንብ ኮንትራት ማስገባት፣ በሰኔ፦ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሰዎች ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው። (እንግሊዝኛ) ማሳሰቢያ:- ከላይ የተጠቀሰውን “ታላቁ ሰው” የተባለውን የእንግሊዝኛ መጽሐፍ የሚፈልጉ ጉባኤዎች ቀጥለው በሚልኩት ወርኀዊ የጽሑፍ መጠየቂያ ቅጽ ላይ (S-14-AM) ሊጠይቁ ይችላሉ።
◼ መሪ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሰው መጋቢት 1 ወይም ከዚያ ብዙ ሳይቆይ የጉባኤው ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ሒሳቡ ከተመረመረ በኋላ ውጤቱን ለጉባኤው አስታውቁ።
◼ የካቲት 14, 1992 ለሁሉም ጉባኤዎች በተላከ የማኅበሩ ደብዳቤ ላይ ሚስዮናውያን የትውልድ አገራቸውን እንዲጎበኙና በዚህ ዓመት ከሚደረጉት የወረዳ ስብሰባዎች አንዱን እንዲካፈሉ ለመርዳት ይቻል ዘንድ ለ1993 የስብሰባ እርዳታ እንዲሰበሰብ ማስታወቂያ ተነግሮ እንደነበር ይታወሳል። መጋቢት ይህ የ1993 የእርዳታ መዋጮ ለማኅበሩ የሚላክበት የመጨረሻው ወር ይሆናል። ለዚህ ዝግጅት ያደረጋችሁትን የልግስና ድጋፋችሁን በጣም እናደንቃለን።
◼ በዚህ ዓመት ከሐምሌ እስከ መስከረም በሚደረገው የገለልተኛ ክልሎች ዘመቻ ጊዜያዊ ልዩ አቅኚዎች በመሆን ለማገልግል የሚፈልጉ የዘወትር አቅኚዎች በጉባኤያቸው የሽማግሌዎች አካል (ወይም የአገልግሎት ኮሚቴ) በኩል ሊያመለክቱ ይችላሉ። ሽማግሌዎቹ (ኮሚቴውም) ማመልከቻውንና የድጋፍ ደብዳቤያቸውን ሐሳባቸውን ግፋ ቢል እስከ ሚያዝያ 15, 1993 ድረስ መላክ አለባቸው።
◼ በቅርቡ የሚደርሱ ጽሑፎች:-
አማርኛ፦ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? (ብሮሹር) የአምልኮ አንድነት (ለጥናቶች የሚሰጥ እንጂ የሚበረከት የዘመቻ ጽሑፍ አይደለም)፤ ቀጥሎ ያሉት ትራክቶች:- መጽሐፍ ቅዱስን ማመን የሚችሉት ለምንድን ነው? (ቁጥር 13)፣ የይሖዋ ምስክሮች ምን ብለው ያምናሉ? (ቁጥር 14)፣ ሰላም በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ሕይወት (ቁጥር 15)፣ እናፈቅራቸው የነበሩ ሙታን ምን ተስፋ አላቸው? (ቁጥር 16) በተጨማሪም በእንግሊዝኛ የ1993 የዓመት መጽሐፍ እና ሌሎች። ትዕዛዛችሁን መላክ ትችላላችሁ።
◼ እንደገና የመጡ የአማርኛ ጽሑፎች:-
በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር! (ብሮሹር)፣ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። የሚያስፈልጋችሁን ያህል ማዘዝ ትችላላችሁ።