“ለመታሰቢያው በዓል የሚደረግ ዝግጅት
ሁሉም ሰው፣ ተናጋሪውም ጭምር በዓሉ የሚከበርበት ትክክለኛ ጊዜና ቦታ ተነግሮታልን? ተናጋሪው መጓጓዣ አለውን?
ቂጣና ወይኑን ለማዘጋጀት እንዲሁም በተገቢው ሰዓት ቦታው ድረስ ለማምጣት ቁርጥ ያለ ዝግጅት ተደርጓልን?
ጠረጴዛ፣ ንጹህ የጠረጴዛ ልብስና በቂ ብርጭቆዎችና ሳህኖች ቀደም ብሎ ለማምጣት ዝግጅቶች ተደርገዋልን? ቂጣውና ወይኑ ስብሰባው ከመጀመሩ ቀደም ብሎ በሚቀርቡበት ዕቃ ላይ ሊደረጉ ይችላሉ። ልክ እስከሚዞሩበት ሰዓት ድረስ ሸፍኖ ማቆየቱም አስፈላጊ አይደለም።
በዓሉ ከመከበሩ በፊት አዳራሹን ለማጽዳት ምን ዝግጅቶች ተደርገዋል? እርግጥ ማናቸውም የአበባ ዝግጅቶች ልከኛ፣ ለዛ ያላቸው ሊሆኑ እንዲገባና በተገቢ መያዣዎች ውስጥ መቀመጥ እንዳለባቸው የተረጋገጠ ነው። በለስላሳ መጠጥ ጠርሙሶች ውስጥ መደረግ የለባቸውም።
አስተናጋጆችና ቂጣውንና ወይኑን የሚያሳልፉ ወንድሞች ተመድበዋልን? እንደተመደቡ ተነግሯቸዋል? በዓሉ ከመጀመሩ በፊት ኃላፊነታቸው ምን እንደሆነ ለማስታወስ ስብሰባ ለማድረግ ፕሮግራም ወጥቷልን? ይህስ ስብሰባ የሚደረገው መቼ ነው? ቂጣውና ወይኑ በስብሰባው ላይ ለተገኙ ሁሉ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲዞር ለማድረግ ምን ሥርዓት መከተል ያስፈልጋል?
በዕድሜ የሸመገሉትንና በአካልም ድካም ያለባቸውን ወንድሞችና እህቶች ለመርዳት የተሟላ ዝግጅት ተደርጓልን? ከቤት ለመውጣት የማይችሉ በመሆናቸው ምክንያት ከጉባኤው ጋር ሊገኙ ላልቻሉ ቅቡዓን ክርስቲያኖች አስፈላጊውን አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቶች ተደርገዋልን?