በመስክ አገልግሎት አዘውታሪዎች ሁኑ
1 በመስክ አገልገሎት አዘውትረን ለመሳተፍ ቁርጥ ያሉ እርምጃዎችን እንወስዳለንን? በየወሩ የመስክ አገልግሎት ሪፖርታችንን በመንግሥት አዳራሹ ውስጥ በጊዜው ለመመለስ ትጉዎች ነንን? በአንድ ዓይነት መልኩ እምነታችንን በሕዝብ ፊት ሳንገልጽ አንድም ወር እንዲያልፍ ፈጽሞ መፍቀድ የለብንም። ይህን ለማድረግ ሁላችንም ጥረት ልናደርግ ይገባናል። — ሮሜ 10:9, 10
2 ራሳችን አዘውታሪዎች ከመሆን አልፈን ሌሎችም በመስክ አገልግሎቱ አዘውትረው እንዲሳተፉ ለመርዳት ንቁዎች ለመሆን እንፈልጋለን። (ፊል. 2:4) ይህንን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? በቅርቡ አገልግሎት የጀመሩትን ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ከእኛ ጋር እንዲሠሩ ለመጋበዝ እንችል ይሆናል። ቋሚ የሆነ የአገልግሎት ፕሮግራም መከተል እውነትን በልባቸው ውስጥ በጥልቀት ለመትከል ይረዳል።
3 በመስክ አገልግሎት አዘውታሪዎች ሁኑ። በየወሩ የመስክ አገልግሎት ሪፖርታችሁን በመመለስ የሚጠበቅባችሁን እንደምትፈጽሙ የምትታመኑ ሁኑ። ሌሎችም በአገልግሎት አዘውትረው እንዲካፈሉ እርዷቸው። “ሰውን ሁሉ አክብሩ፤ መላውን የወንድማማች ማኅበር አፍቅሩ፤ አምላክን ፍሩ። ንጉሥን አክብሩ።” — 1 ጴጥ. 2:17 አዓት