የመስከረም የአገልግሎት ስብሰባዎች
መስከረም 6 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 53
10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
20 ደቂቃ፦ ልጆቻችሁ በትምህርት ቤት ለሚያጋጥሟቸው ፈተናዎች አጠናክሯቸው። ከቃለ ምልልሶችና ከትዕይንት ጋር የሚቀርብ ንግግር። በዛሬው ጊዜ ክርስቲያን ወጣቶች በጉባኤ ውስጥ ያሉት ብዙዎች ሊገምቷቸው እንኳን የማይችሏቸው አስቸጋሪ ሁኔታዎች ያጋጥሟቸዋል። በተለይ ወላጆች ልጆቻቸው የሚያጋጥሟቸውን ንጹሕ አቋማቸውን ለማጉደፍ የሚመጡትን እነዚህን ፈተናዎች ለመቋቋም ይችሉ ዘንድ እንዲያጠነክሯቸው ስለነዚህ ፈታኝ ሁኔታዎች ከልጆቻቸው መስማት አለባቸው። የተለያየ ዕድሜ ላላቸው ሦስት ወጣቶች ቃለ ምልልስ አድርግ። በትምህርት ቤት በየዕለቱ የሚያጋጥሟቸው አንዳንድ ተጽዕኖዎች ምንድን ናቸው? ከይሖዋ ጋር ያላቸውን ጥሩ ዝምድና እንዲጠብቁ የሚረዳቸው ምንድን ነው? አንድ ቤተሰብ ትምህርት ቤት በተባለው ብሮሹር ገጽ 11 አንቀጽ 2 እና 3 ላይ አብረው ሲወያዩበት የሚያሳይ አንድ ትዕይንት አቅርብ። ልጆቹ በትምህርት ቤት ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን ከፍተኛ የሥነ ምግባር ደረጃዎች በመከተላቸው ምክንያት እንደሚቀልዱባቸው እንዲሁም ገለልተኛ እንደሆኑ እንደሚሰማቸው በግልጽ ይነግሯቸዋል። የቤተሰቡ ራስ ልጆቹ በአርዓያነት የሚጠቀሱ በመሆናቸው ምክንያት እንደተደሰቱባቸው በመግለጽና ይሖዋ በሚያሳዩት ጠባይ እንደሚደሰት በማስታወስ ያበረታታቸዋል። (ምሳሌ 27:11) ክፍሉን የሚያቀርበው ወንድም በጉባኤው ውስጥ ያሉት ወጣቶች መልካም ሥራ እንደሚሠሩ ገልጾ በማመስገን እንዲሁም በሚመጣው የትምህርት ዓመት በመንፈሳዊ ጠንካሮች ለመሆን እንዲችሉ ለወላጆቻቸው ሐሳባቸውን እንዲገልጹላቸው አጥብቆ በማሳሰብ ክፍሉን ይደመድማል።
15 ደቂቃ፦ “ሌሎች አንድን ታላቅ ሀብት እንዲያውቁ መርዳት።” በጥያቄና መልስ የሚሸፈን። አስፋፊዎች ለጽሑፎቻችን በመዋጮ መልክ የሚከፈለውን ክፍያ በሚናገሩበት ጊዜ አዎንታዊ ስሜት ማሳየት እንደሚያስፈልጋቸው ጉባኤውን አስታውስ። አንቀጽ 4ን በምትወያዩበት ጊዜ አንድ አስፋፊ ለአንድ ወላጅ ለዘላለም መኖርን ሲያበረክት የሚያሳይ ትዕይንት አቅርብ።
መዝሙር 121 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 13 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 155
10 ደቂቃ፦ የሒሳብ ሪፖርትና ማኅበሩ የጉባኤው መዋጮ የደረሰው መሆኑን የገለጸበት ማስታወቂያ አክለህ የጉባኤውን ማስታወቂያዎች አቅርብ። ለጉባኤውና ለማኅበሩ ዓለም አቀፍ ሥራ ማካሄጃ ጉባኤው በልግስና ስለሚያደርገው የገንዘብ ድጋፍ ምስጋና አቅርብ።
10 ደቂቃ፦ “በመጽሔቶች አማካኝነት ሌሎች እንዲጠቀሙ አድርግ።” ንግግርና ትዕይንቶች። በቅርብ ጊዜ በወጡትም ሆነ በቆዩት መጽሔቶች ሙሉ በሙሉ መጠቀማችን ያለውን ዋጋ ጎላ አድርገህ ግለጽ። አንዱ በቅርብ የወጡትን እትሞች በመጠቀም ሌላው ደግሞ የቤቱ ባለቤት ለሚያስፈልገው ነገር የሚስማማ የቆየ እትም በመጠቀም እንዴት መጽሔት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሁለት ትዕይንቶችን አቅርብ።
15 ደቂቃ፦ “በዚህ የአገልግሎት ዓመት ምን ለማከናወን አስበናል?” ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት የታከለበት ንግግር። በመሪ የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ። ጉባኤው ባለፈው ዓመት ያከናወነውን አገልግሎት ከልስና ሁሉም በ1994 የአገልግሎት ዓመት ካለፈው የበለጠ ለመሥራት ዕቅድ እንዲያወጡ አበረታታቸው።
10 ደቂቃ፦ “ለዘላለም መኖር እና የአምልኮ አንድነት የተባሉትን መጽሐፎች አስጠና።” ክፍሉን ከአድማጮች ጋር በመወያየት ከሸፈንክ በኋላ በደንብ የተዘጋጀ አንድ አስፋፊ ታላቁ ሰው የተባለውን የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ሲያስጠናው የነበረውን ሰው ለዘላለም መኖር ን እንዲያጠና እንዴት እንደሚቀይር የሚያሳይ ትዕይንት እንዲያቀርብ አድርግ።
መዝሙር 191 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 20 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 19
10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። በዚህ ሳምንት ሊጠቀሙባቸው የሚችሉትን የመነጋገሪያ ነጥቦች በቅርብ ከወጡት መጽሔቶች ውስጥ ጠቅሰህ ሐሳብ አቅርብ።
20 ደቂቃ፦ “በግ መሰል የሆኑ ሰዎች በጠንካራ መሠረት ላይ እንዲታነጹ እርዳቸው።” ከአድማጮች ጋር ተወያይበት። ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ በሄድን ቁጥር የመዘጋጀትን አስፈላጊነት አጉላ። ችሎታ ያለው አንድ አስፋፊ ቀደም ሲል ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ ወስዶ ለነበረ ሰው በአንቀጽ 3 ወይም 5 ላይ ባለው ሐሳብ ተጠቅሞ ተመላልሶ መጠየቅ ሲያደርግለት የሚያሳይ ትዕይንት እንዲያቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ “የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ማስጀመር።” ጥያቄና መልስ። አንቀጽ 4ን ከተወያያችሁበት በኋላ ለዘላለም መኖር ወይም ምክንያቱን ማስረዳት በተባሉት ጽሑፎች ውስጥ ባሉት ክፍሎች ላይ ተዘጋጅቶ በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ በመጠቀም ተመላልሶ መጠየቅ ሲደረግ የሚያሳይ ሞቅ ያለ ትዕይንት አቅርብ።
መዝሙር 136 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 27 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 172
10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።
20 ደቂቃ፦ እናፈቅራቸው የነበሩ ሙታን አሁን የት ናቸው? የቤተሰብ ወይይት። የቤተሰቡ የቅርብ ወዳጅ የነበረውን የአንድ ሰው ሞት በተመለከተ ምክንያቱን ማስረዳት በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 98 እስከ 100 ላይ ባሉት የተመረጡ ሐሳቦች በመጠቀም የቤተሰቡ ራስ የሚያደርግላቸው ውይይት። የመጽሐፍ ቅዱስ አመለካከት እንዲገባቸው ልጆቹን በመርዳት ላይ ያተኩራል። ልጆቹ ሞት ምን ማለት እንደሆነ ገብቷቸው እንደሆነና ለሌሎች ሰዎችም እንደየአቅማቸው በግልጽ ለማስረዳት ይችሉ እንደሆነ ለማረጋገጥ ጥያቄዎችን ይጠይቃቸዋል። በተጨማሪም ምክንያቱን ማስረዳት በተባለው መጽሐፍ ተጠቅመው ሌሎችን እንዴት ማጽናናት እንደሚችሉ ያሳያቸዋል።
15 ደቂቃ፦ በጥቅምት ወር መጽሔቶችን አበርክቱ። ሦስት ትዕይንቶችን አዘጋጅ። ትዕይንቶቹም አንዱ በቅርብ ጊዜ የወጣውን መጠበቂያ ግንብ ሌላው በቅርብ ጊዜ የወጣውን ንቁ! ሌላው ደግሞ የቤቱ ባለቤት በጣም ሥራ ስለበዛበት ትራክት ሲወስድ የሚያሳዩ ይሁኑ። ከየትዕይንቶቹ በኋላ አቀራረቡ ውጤታማ የሆነበትን ምክንያት አንድ በአንድ ተንትንላቸው።
መዝሙር 113 እና የመደምደሚያ ጸሎት።