የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 9/93 ገጽ 3
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
km 9/93 ገጽ 3

ማስታወቂያዎች

◼ በአገልግሎት የምንጠቀምባቸው ጽሑፎች በመስከረም፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። በጥቅምት፦ ንቁ! ወይም መጠበቂያ ግንብ መጽሔቶችን ኮንትራት ማስገባት ወይም የመጽሔቶቹን ነጠላ ቅጂዎች ማበርከት ይቻላል። በታኅሣሥ፦ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሰዎች ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው የተባለው የእንግሊዝኛ መጽሐፍ።

◼ መሪ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሰው መስከረም 1 ወይም ከዚያ ብዙ ሳይቆይ የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር አለበት። ሒሳቡ ከተመረመረ በኋላ የምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነገር ይኖርበታል።

◼ በጥቅምት ረዳት አቅኚዎች ለመሆን ያቀዱ አስፋፊዎች ማመልከቻቸውን ቀደም ብለው ሞልተው መመለስ ይኖርባቸዋል። ይህም ሽማግሌዎቹ አስፈላጊውን ጽሑፍና የአገልግሎት ክልል ለማዘጋጀት ያስችላቸዋል።

◼ ሽማግሌዎች በሚያዝያ 15, 1991 የመጠበቂያ ግንብ እትም ገጽ 21–23 ላይ ከውገዳ ለመመለስ የሚፈልጉ የተወገዱ ወይም ራሳቸውን ያገለሉ ሰዎችን አስመልክቶ የወጣውን መመሪያ እንዲከተሉ እናሳስባቸዋለን።

◼ አዲስ የዋጋ ዝርዝር ስለተዘጋጀ የዋጋ ለውጥ በተደረገባቸው አካባቢዎች ለሚገኙ ጉባኤዎች አራት አራት ቅጂዎች ተልከዋል። እነዚህ ቅጂዎች ለጉባኤው ጸሐፊና ለጽሑፍ፣ ለመጽሔት እንዲሁም ለሒሳብ አገልጋዮች መሰጠት ይኖርባቸዋል። በተደረገው የዋጋ ለውጥ ምክንያት እስከ ነሐሴ 31 ድረስ በእጃችሁ ያሉትን ጽሑፎች መዝግባችሁ በኢንቨንተሪ ቅጽ ላይ እንድታሰፍሩና እንድትልኩልን እንጠይቃችኋለን። በአንዳንድ ጽሑፎች ላይ ስለተደረገው የዋጋ ለውጥ ለጉባኤ ማስታወቂያ መንገር ሊያስፈልግ ይችላል። በዚህ መንገድ ከመስከረም 1 ጀምሮ አስፋፊዎችና አቅኚዎች በአዲሱ ዋጋ መሠረት ጽሑፎችን ለማበርከት ይሞክራሉ።

◼ ባለ ቀለም የመጠበቂያ ግንብ ከኅዳር 1, 1993 ይጀምራል። እስከ ጥቅምት 15 ድረስ ያለባችሁን የመጽሔት ዕዳ በሙሉ መክፈላችሁን አረጋግጡ።

◼ ማኅበሩ ከ1970 እስከ 1979 የወጡትን የእንግሊዝኛ የመጠበቂያ ግንብ ጥራዞች (ባውንድ ቮልዩምስ) በማተም ላይ ሲሆን አቅርቦቱም ቋሚ ይሆናል። እነዚህን ጥራዞች ለማግኘት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ጥያቄውን በጉባኤው በኩል መላክ ይችላል። ይሁን እንጂ ጥራዞቹን (ባውንድ ቮልዩሞቹን) ማግኘት የሚቻለው በልዩ ትዕዛዝ እንደሆነ እባካችሁ አስታውሱ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ