ማስታወቂያዎች
◼ በአገልግሎት የምንጠቀምባቸው ጽሑፎች በጥቅምት፦ ንቁ! ወይም መጠበቂያ ግንብ ኮንትራት ማስገባት ወይም የመጽሔቶቹን ነጠላ ቅጂዎች ማበርከት ይቻላል። ተገቢ በሚሆንበት ጊዜ የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ የተባለውን የእንግሊዝኛ መጽሐፍም ማበርከት ይቻላል። በኅዳር፦ የአዲሲቱ ዓለም የቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉም እና መጽሐፍ ቅዱስ — የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው? የተባለው የእንግሊዝኛ መጽሐፍ። በታኅሣሥ፦ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሰዎች ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው የተባለው የእንግሊዝኛ መጽሐፍ። በጥር፦ ቀለሙ እየደበዘዘ ወይም እየለቀቀ በሚሄድ ወረቀት የታተሙ ወይም ከ1980 በፊት የታተሙ ማናቸውንም ባለ 192 ገጽ መጻሕፍት በግማሽ ዋጋ ማበርከት ይቻላል። ይህ የዋጋ ቅናሽ ቀለሙ በማይደበዝዝ ወይም በማይለቅ ወረቀት ላይ የታተሙ ጽሑፎችን አይጨምርም። እነዚህ መጻሕፍት የሌሏቸው ጉባኤዎች ሕይወት እንዴት ተገኘ? በዝግመተ ለውጥ ወይስ በፍጥረት? የተባለውን የእንግሊዝኛ መጽሐፍ አለዚያም የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ የተባለውን የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ማበርከት ይችላሉ። ማሳሰቢያ:- ከላይ የተጠቀሱት የዘመቻ ጽሑፎች የሚያስፈልጓቸው ጉባኤዎች በሚቀጥለው ወር በሚልኩት ወርኀዊ የጽሑፍ መጠየቂያ ቅጽ (S–14–AM) ላይ መጠየቅ ይችላሉ።
◼ ከዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን እትም ጋር “የ1994 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም” አብሮ ተልኳል። ትርፍ ቅጂዎች ስለማይኖሩ በ1994 ዓመቱን ሙሉ እንድትጠቀሙበት ፕሮግራሙን በጥሩ ቦታ ልታስቀምጡት ይገባል።
◼ ጉባኤዎች ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር — 1994 ከጥቅምት የጽሑፍ ጥያቄያቸው ጋር ማዘዝ መጀመር ይኖርባቸዋል። ቡክሌቱን በአማርኛ፣ በአረብኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በኪኛርዋንዳ እና በስዋሂሊ ማግኘት ይቻላል። ቅዱሳን ጽሑፎችን መመርመር የተባለው ቡክሌት በልዩ ትዕዛዝ ብቻ የሚገኝ ጽሑፍ ነው።
◼ ለ1993 የወረዳ ስብሰባ ደረት ላይ የሚለጠፍ የባጅ ካርድ ከሚላኩላችሁ ሌሎች ጽሑፎች ጋር አሁኑኑ አብሮ መላክ ይጀምራል። እነዚህን ካርዶች ማዘዝ አስፈላጊ አይደለም። በየጉባኤው ብዛት 25 25ቱ አንድ ላይ ታስሮ ይላካል። ጉባኤው ተጨማሪ ደረት ላይ የሚለጠፍ የባጅ ካርድ ካስፈለገው በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S–14–AM) ላይ ማዘዝ አለበት። ከፕላስቲክ የተሠሩ የባጅ ካርድ መያዣዎች የሚፈልግ ጉባኤ ግን ማዘዝ ያስፈልገዋል።
◼ ትልቅ ስብሰባ በሚደረግበት ወቅትና በእረፍት ወራት አስፋፊዎች በግለሰብ ደረጃም ሆነ በቤተሰብ በመስክ አገልግሎት ለመካፈል ቁርጥ ያለ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋቸዋል። ከጉባኤያችሁ ርቃችሁ ከሄዳችሁ የመስክ አገልግሎት ሪፖርታችሁን በወሩ መጨረሻ ላይ ለጉባኤያችሁ ጸሐፊ ላኩ። በምትልኩበትም ጊዜ የጉባኤያችሁ ጸሐፊ የናንተንም ሪፖርት የጉባኤው ወርኀዊ ሪፖርት ውስጥ ጨምሮ የሚልክበት በቂ ጊዜ እንዲኖረው አድርጋችሁ ላኩለት።
◼ “መለኰታዊ ትምህርት” የወረዳ ስብሰባ በመዝሙር ይሖዋን ለማወደስ ጥሩ አጋጣሚ ይሰጠናል። በደንብ ለመዘመር እንፈልጋለን። መዝሙሮቹን በደንብ ብትለማመዱባቸው ጥሩ ነው።
◼ አዲስ የመጣ ካሴት:-
በእንግሊዝኛ፦ በይሖዋ ዓይን ቅን የሆነውን ማድረግ (ድራማ፣ በአንድ ካሴት)
◼ የንቁ! መጽሔት በአማርኛ መታተም ሊጀምር ስለሆነ ጉባኤዎች የሚፈልጉትን ብዛት በቶሎ ሊያስታውቁን ይችላሉ። ጉባኤው ሊደርሰው የሚችለው በትዕዛዝ መሠረት ስለሆነ እባካችሁ ይህ ማስታወቂያ በተነገረ በ2 ሣምንት ውስጥ አስታውቁን።
◼ ሁለተኛ ደረጃ የእንግሊዝኛ የብሬይል ጽሑፍ:- በአራት ጥራዝ የተዘጋጀ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር 1994 የተባለው ቡክሌት ስለሚዘጋጅ ማዘዝ ይቻላል። በተጨማሪም የ1994 የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራምም በብሬይል በአንድ ጥራዝ ይወጣል።