ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
አርጀንቲና፦ በግንቦት ወር አርጀንቲና የ100,000ን ድንበር ካለፉት አገሮች 13ኛዋ ለመሆን በቅታለች። በተከታታይ ለ29ኛ ጊዜ የነበራቸው ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር 100,024 ነበረ።
ኮሎምቢያ፦ በግንቦት ወር 58,589 አስፋፊዎችን ሪፖርት በማድረግ በተከታታይ ለአምስተኛ ጊዜ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር አግኝታለች።
ማዳጋስካር፦ በግንቦት ወር ሪፖርት ያደረጉ 5,013 አስፋፊዎች ስለነበሩ የ5,000ን ድንበር አልፋለች።
ሩዋንዳ፦ በሰኔ ወር ሩዋንዳ 2,057 አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር የነበራት ሲሆን አስፋፊዎቹ እያንዳንዳቸው በአማካይ 30 ሰዓትና 2.7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ሪፖርት አድርገዋል!