የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/93 ገጽ 2
  • የጥቅምት የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥቅምት የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ማሳሰቢያ:- የመንግሥት አገልግሎታችን የወረዳ ስብሰባው ለሚደረግበትም ወቅት የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም ያወጣል። ጉባኤዎች “መለኰታዊ ትምህርት” የወረዳ ስብሰባ ለመካፈል የሚያስችላቸውንና ከስብሰባው በኋላ ባለው ሳምንት በሚኖረው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለ30 ደቂቃ የወረዳ ስብሰባው ላይ የቀረቡት ጎላ ያሉ ነጥቦች የሚከለስበት የክለሳ ፕሮግራም እንዲኖር እንዳስፈላጊነቱ ማስተካከያዎችን ሊያደርጉ ይችላሉ። ጎላ ብለው በሚታዩት ነጥቦች ላይ ማተኮር የሚችሉ ብቃት ያላቸው ሁለት ወይም ሦስት ወንድሞች የወረዳ ስብሰባው በተደረገባቸው በእያንዳንዱ ቀናት የነበረውን ፕሮግራም እንዲከልሱ ክፍሉ አስቀድሞ ሊሰጣቸው ይገባል። በሚገባ ዝግጅት የተደረገበት ይህ ክለሳ ወንድሞች በግል ሊሠሩባቸው የሚያስፈልጓቸውንና ለመስክ አገልግሎት የሚጠቀሙባቸውን ቁልፍ ነጥቦች እንዲያስታውሷቸው ይረዳቸዋል። አድማጮች የሚሰጧቸው ሐሳቦችና የሚናገሯቸው ተሞክሮዎች አጫጭርና ነጥቡ ላይ ያተኮሩ ሊሆኑ ይገባል።
  • ጥቅምት 4 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥቅምት 11 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥቅምት 18 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥቅምት 25 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
km 10/93 ገጽ 2

የጥቅምት የአገልግሎት ስብሰባዎች

ማሳሰቢያ:- የመንግሥት አገልግሎታችን የወረዳ ስብሰባው ለሚደረግበትም ወቅት የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም ያወጣል። ጉባኤዎች “መለኰታዊ ትምህርት” የወረዳ ስብሰባ ለመካፈል የሚያስችላቸውንና ከስብሰባው በኋላ ባለው ሳምንት በሚኖረው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለ30 ደቂቃ የወረዳ ስብሰባው ላይ የቀረቡት ጎላ ያሉ ነጥቦች የሚከለስበት የክለሳ ፕሮግራም እንዲኖር እንዳስፈላጊነቱ ማስተካከያዎችን ሊያደርጉ ይችላሉ። ጎላ ብለው በሚታዩት ነጥቦች ላይ ማተኮር የሚችሉ ብቃት ያላቸው ሁለት ወይም ሦስት ወንድሞች የወረዳ ስብሰባው በተደረገባቸው በእያንዳንዱ ቀናት የነበረውን ፕሮግራም እንዲከልሱ ክፍሉ አስቀድሞ ሊሰጣቸው ይገባል። በሚገባ ዝግጅት የተደረገበት ይህ ክለሳ ወንድሞች በግል ሊሠሩባቸው የሚያስፈልጓቸውንና ለመስክ አገልግሎት የሚጠቀሙባቸውን ቁልፍ ነጥቦች እንዲያስታውሷቸው ይረዳቸዋል። አድማጮች የሚሰጧቸው ሐሳቦችና የሚናገሯቸው ተሞክሮዎች አጫጭርና ነጥቡ ላይ ያተኮሩ ሊሆኑ ይገባል።

ጥቅምት 4 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 215

10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በቅርብ የወጡትን መጽሔቶች በጉባኤው የአገልግሎት ክልል ውስጥ መጠቀም የሚቻልባቸውን መንገዶች ጠቁም። የመጽሔት ደንበኞች ለማፍራት በማቀድ መጽሔት የተበረከተላቸውን ሰዎች በሙሉ ተመልሶ በመሄድ ማነጋገሩ አስፈላጊ መሆኑን አበክረህ ግለጽ። ሰዎቹ እውነተኛ ፍላጎት ያላቸው ከሆኑ ኮንትራት እንዲገቡ መጠየቅ ይቻላል።

15 ደቂቃ፦ “ለአምልኮ ቦታህ አክብሮት ታሳያለህን?” በሰኔ 15, 1993 መጠበቂያ ግንብ ውስጥ በወጣው ርዕስ ላይ የተመሠረተ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ትምህርቱ ለጉባኤው እንዴት እንደሚሠራ አሳይ። ለጉባኤው ሊነገር የሚገባው አንድ ለየት ያለ ችግር ካለ በዘዴ ተገቢውን ምክር ስጥ።

20 ደቂቃ፦ በጥቅምት ወር ከቤት ወደ ቤት የምታደርጉትን አገልግሎት አጠናክሩት። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ወይም ብቃት ያለው ሌላ ወንድም ከቤት ወደ ቤት የሚደረገውን አገልግሎት አስፈላጊነት ከአድማጮች ጋር ይወያያል። በጥቅምት ወር ልዩ ልዩ ጽሑፎችን የማበርከት ምርጫ ስላለን በርካታና የተለያዩ አቀራረቦችን እንድንጠቀም ያስችሉናል። በሚከተሉት መሠረት ትዕይንቶች አሳይ:- (1) አስፋፊው በቅርብ በወጣ የንቁ! ወይም የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት ውስጥ ወደሚገኝ ርዕስ የሚያመራ ውይይት ይከፍታል። አስፋፊው የቤቱ ባለቤት ባሳየው ፍላጎት ላይ በመመርኮዝ በቅርቡ የወጡትን መጽሔቶች እንዲወስድ ሊጠይቀው ወይም ትራክት ሊሰጠው ይችላል። (2) ውይይቱን የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ ወደተባለው የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ለመምራት በማሰብ አስፋፊው ውይይት ይጀምራል። አስፋፊው እንደ ሁኔታው አመቺነት አንድ መጽሐፍ ወይም ሁለት መጽሔቶች እንዲወስድ ሰውየውን ይጠይቀዋል። (3) አስፋፊው በትራክት ተጠቅሞ መደበኛ ያልሆነ ውይይት ይጀምርና በቅርቡ የወጡትን መጽሔቶች እንዲወስድ ፍላጎት ያሳየውን ሰው ይጠይቀዋል። (4) የመጽሔት ደንበኞቹን በመጠየቅ ላይ ያለ አስፋፊ ኮንትራት እንዲገቡ ለመጠየቅ ይወስናል። ይህን የመሰለ የተለያየ ምርጫ መኖሩ አስፋፊዎች በጥቅምት ወር ከቤት ወደ ቤት የሚያደርጉትን አገልግሎት እንዲያጠናክሩት ሊያበረታታቸው ይገባል። በዚህ ወር በጉባኤው ውስጥ ረዳት አቅኚ ሆነው የሚያገለግሉ አንዳንድ አስፋፊዎች እንደሚኖሩ አያጠራጥርም። ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል የሚያመች ሁኔታ ያላቸው ሌሎችም ለመመዝገብ ጊዜ አላቸው።

መዝሙር 10 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥቅምት 11 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 155

10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ማኅበሩ የጉባኤው መዋጮ የደረሰው መሆኑን የገለጸበት ማስታወቂያ ካለ አንብብና ለጉባኤውና ለማኅበሩ ዓለም አቀፍ ሥራ ማካሄጃ ጉባኤው በልግስና ስለሚያደርገው የገንዘብ ድጋፍ ምስጋና አቅርብ። ለመስክ አገልግሎት የወጣውን የሳምንቱን ፕሮግራም በአጭሩ ተናገርና አስፋፊዎች ቅንዓት የተሞላበት ተሳትፎ ማድረግ እንደሚፈለግባቸው ግለጽ።

15 ደቂቃ፦ “ከቤት ወደ ቤት በምናደርገው አገልግሎት በመጽሔቶቻችን መጠቀም።” ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። በመስክ አገልግሎት ለምናገኛቸውም ሆነ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ለምንመሰክርላቸው ሰዎች ሁሉ መጽሔቶቹን በምናበረክትበት ጊዜ ሞቅ ያለ ስሜት የምናሳይበት ጥሩ ምክንያት አለን። ምንም እንኳን መጽሔቶቹ የወጡበት ቀን የሚጻፍ ቢሆን መጽሔት በሚበረከትበት ቀን የምናበረክተው በቅርብ የወጡትን እትሞች ቢሆንም አጋጣሚ ካገኘን የቆዩ መጽሔቶችንም ለማበርከት አናመነታም። የምታበረክቷቸው መጽሔቶች ግን ንጹሕና ያልተሻሹ ይሁኑ። ብቃት ያለው አስፋፊ በአንቀጽ 4 ላይ ያለውን አቀራረብ በመጠቀም ትዕይንት እንዲያሳይ አድርግ።

20 ደቂቃ፦ “ከ1993 ‘መለኰታዊ ትምህርት’ የወረዳ ስብሰባ ሙሉ በሙሉ ተጠቀም” — ክፍል 1። ከአንቀጽ 1–16 ላይ ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። አስፋፊዎች በስብሰባው ላይ ከሚገኙ ጥናቶቻቸው ጋር ተገቢ በሆኑ ነጥቦች ላይ ሊወያዩ ይገባል።

መዝሙር 105 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥቅምት 18 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 53

5 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።

15 ደቂቃ፦ “በአገልግሎታችን የማናዳላ መሆናችንን ማሳየት።” ጥያቄና መልስ። በዚህ ርዕስ ሥር የጉባኤያችሁን የአገልግሎት ክልል የሚመለከተውን ክፍል ጎላ አድርገህ ግለጽ።

15 ደቂቃ፦ “ያገኘሃቸውን ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች አትርሳቸው።” ለአድማጮች አንዳንድ ጥያቄዎች የሚቀርቡበት ንግግር። በጉባኤው የአገልግሎት ክልል ውስጥ አስፋፊዎች ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ያንን ፍላጎታቸውን እንዲያዳብሩት ያደረጉት እንዴት እንደሆነ ግለጽ፤ ወይም አንድ አስፋፊ የንቁ! እና የመጠበቂያ ግንብ ነጠላ ቅጂዎችን የወሰዱ ሰዎችን እየተመላለሱ በመሄድ ማነጋገሩ ጥቅም እንዳለው የሚያሳይ በቅርብ የተፈጸመ ተሞክሮ እንዲናገር አድርግ።

10 ደቂቃ፦ “ከ1993 ‘መለኰታዊ ትምህርት’ የወረዳ ስብሰባ ሙሉ በሙሉ ተጠቀም” — ክፍል 2። ከአንቀጽ 17–19 ከአድማጮች ጋር ተወያይበት፤ እንዲሁም “የወረዳ ስብሰባ ማሳሰቢያዎች” የሚለውን በጥንቃቄ ከልስ። በመጠበቂያ ግንብ 12–110 ገጽ 10–20 በሚገኘው ሐሳብ ላይ የተመሠረቱ ተገቢ ማሳሰቢያዎችንም ጨምረህ አቅርብ ወይም ስብሰባውን ከመካፈላቸው በፊት በእነዚህ የጥናት ርዕሶች ላይ ያሉትን ነጥቦች በቤተሰብ እንዲከልሷቸው አበረታታቸው።

መዝሙር 34 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥቅምት 25 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 174

10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። ለሳምንቱ የተደረጉትን የመስክ አገልግሎት ዝግጅቶች ጨምረህ አቅርብ፤ እንዲሁም አስፋፊዎች በፊታችን ባሉት ቀናት በመስክ አገልግሎት ሊጠቀሙ የሚችሉባቸውን በቅርብ በወጡት መጽሔቶች ውስጥ ባሉ የመነጋገሪያ ነጥቦች ላይ እንዲያተኩሩ አድርግ። ጊዜ ካለህ ለጉባኤያችሁ የአገልግሎት ክልል የሚስማሙ አንድ ወይም ሁለት አጠር ያሉ ትዕይንቶችን አቅርብ። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ሁሉ ተመልሶ በመሄድ ማነጋገር አስፈላጊ እንደሆነ አሳስባቸው።

15 ደቂቃ፦ ያዘኑትን ለማጽናናት የተዘጋጃችሁ ሁኑ። (ምክንያቱን ማስረዳት በተባለው መጽሐፍ ገጽ 102–104 ላይ የተመሠረተ።) (3 ደቂቃ።) ይህን ክፍል የሚያቀርበው ወንድም የይሖዋ ምስክሮች ከሞት ጋር የተያያዙትን ሁሉንም ልማዶች አንቀበልም እንደማይሉ ይገልጻል። (5 ደቂቃ።) የይሖዋ ምስክሮች አንዳንድ ባሕላዊ የልቅሶ ልማዶችን የማይፈጽሙበትን ምክንያት አንድ የይሖዋ ምስክር ምክንያቱን ማስረዳት በተባለው መጽሐፍ ገጽ 102–103 ላይ ያለውን በመጠቀም ለሥራ ባልደረባው እንዴት እንደሚገልጽለት የሚያሳይ ትዕይንት አቅርብ። (7 ደቂቃ።) በገጽ 103–104 ላይ ያለውን “አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ — ” በሚለው ርዕስ ሥር ያለውን ሐሳብ ከአድማጮች ጋር ተወያይበት።

20 ደቂቃ፦ “የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምራት።” በጥያቄና መልስ የሚሸፈን ትምህርት። አንድ አስፋፊ ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሱት ጥቅሶች በአንቀጹ ውስጥ ያለውን ሐሳብ እንዴት እንደሚደግፉት እንዲገባው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱን ሲረዳው የሚያሳይ በሚገባ ልምምድ የተደረገበት ትዕይንት አቅርብ። በዚያው ትዕይንት ውስጥ አስፋፊው ተማሪው እውነትን የራሱ እንዲያደርግ በሚረዱ አጋዥ ጥያቄዎች ይጠቀማል። በትዕይንቱ ላይ የሚወያዩት የአምልኮ አንድነት ወይም ለዘላለም መኖር ከተባሉት መጽሐፎች ውስጥ በተመረጡ ክፍሎች ላይ ይሁን።

መዝሙር 212 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ