የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/93 ገጽ 8
  • የወረዳ ስብሰባ ማሳሰቢያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የወረዳ ስብሰባ ማሳሰቢያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
km 10/93 ገጽ 8

የወረዳ ስብሰባ ማሳሰቢያዎች

ተገቢ የሆነ ሥነ ሥርዓት፦ በስብሰባው ላይ የሚገኙ ሁሉ የመሰብሰቢያውን ቦታ እንደ “እግዚአብሔር ቤት” አድርገው በአክብሮት በመመልከት ተገቢ በሆነ ሥነ ሥርዓት መመላለሳቸው አስፈላጊ ነው። (መዝ. 55:14) በንግግሮቹ፣ በድራማዎቹ፣ በመዝሙሮቹ በተለይም በጸሎቶቹ ላይ ሌሎች ፕሮግራሙን በትኩረት እንዳያዳምጡ የሚያደርግ ምንም ነገር እባካችሁ አታድርጉ። ሳያስፈልግ ወዲያ ወዲህ ማለት፣ ማውራት ወይም የሚነገረውን ነገር በትኩረት ለመከታተል የሚሞክሩትን አድማጮች በሚረብሽ መንገድ በባለ ፍላሽ ካሜራዎች ፎቶግራፍ ማንሳት ወይም ፕሮግራሙን በቪድዮ ካሜራ መቅረጽ አክብሮት ማሳየት አይሆንም። አሳቢነታችንና መልካም ጠባያችን መለኰታዊውን ትምህርት ከልባችን እንደምናደንቅና ወደ ስብሰባው የመጣነውም በይሖዋ ለመማር መሆኑን እናሳያለን።

ማረፊያ፦ በስብሰባው በተመደበላችሁ ማረፊያ ብቻ በመጠቀም መተባበር በጣም ያስፈልጋችኋል። ስብሰባው በሚደረግበት ከተማ ለማደር የምትፈልጉ ከሆነና እስካሁን ድረስ መኝታ እንዲያዝላችሁ ካላደረጋችሁ አሁኑኑ እንዲያዝላችሁ አድርጉ። የተያዘላችሁን ማረፊያ መተው ካስፈለጋችሁ ክፍሉ ለሌላ ሰው እንዲሰጥ በተቻላችሁ መጠን አስቀድማችሁ በቀጥታ ለሞቴሉ መጻፍ ወይም መደወል አለባችሁ።

የጉባኤ ጸሐፊዎች የልዩ ማረፊያ መጠየቂያ ቅጾችን ሞልተው ወደ ትክክለኛው የስብሰባ አድራሻ በቶሎ መላክ አለባቸው። በልዩ ማረፊያ መጠየቂያ አማካኝነት የተያዘውን ማረፊያ መሠረዝ ካለባችሁ ክፍሉ ለሌላ እንዲያገለግል ለሆቴሉ ወይም ለቤቱ ባለቤት እንዲሁም ለስብሰባው የማረፊያ ማዘጋጃ ክፍል ወዲያውኑ ማሳወቅ ይኖርባችኋል።

የሕፃናት ጋሪዎች፦ በብዙ ቦታዎች የሕፃናት ጋሪዎችን ወደ ሕዝብ መሰብሰቢያዎች ማምጣት አይቻልም። የእሳት አደጋ መከላከያ ደንቦች ጋሪዎቹን በኮሪደሮችና በመተላለፊያዎች ወይም በመቀመጫዎች መካከል ማቆምን ይከለክላሉ። የሰው ብዛት የተጨናነቁ ሁኔታዎችን ሊፈጥር ስለሚችል የሕፃናት ጋሪዎች ውስጡ ላለው ሕፃን ብቻ ሳይሆን ጋሪው ሊያደናቅፋቸው ለሚችሉ ሰዎችም አደጋ ያስከትላሉ። ስለዚህ እባካችሁ የሕፃናት ጋሪዎችን ወደ ስብሰባ ቦታ አታምጡ። የሕፃናት መቀመጫዎች ከወላጆች ጎን ባለው መቀመጫ ላይ ሊታሠሩ ስለሚችሉ እንደዚህ ዓይነት መቀመጫዎችን ማምጣት ይቻላል። በዚህ ጉዳይ ላይ ትብብራችሁ ያስፈልጋል።

ጥምቀት፦ የጥምቀት ዕጩዎች ዓርብ ጠዋት ፕሮግራሙ ከመጀመሩ በፊት በተመደበላቸው ቦታ መቀመጥ አለባቸው። እያንዳንዱ ተጠማቂ ልከኛ የሆነ የዋና ልብስና ፎጣ ይዞ መምጣት ይኖርበታል። የጥምቀት ንግግሩና ጸሎቱ በተናጋሪው ከቀረበ በኋላ የመድረኩ ሊቀ መንበር ለጥምቀት ዕጩዎች አጠር ያለ መመሪያ ይሰጥና መዝሙር እንዲዘመር ይጋብዛል። የመጨረሻው ስንኝ ከተዘመረ በኋላ አስተናጋጆች የጥምቀት ዕጩዎችን ጥምቀቱ ወደሚከናወንበት ቦታ ወይም ወደዚያ ወደሚወስዷቸው መኪናዎች እየመሩ ይወስዷቸዋል። ጥምቀት አንድ ሰው ራሱን መወሰኑን የሚያሳይበት ምልክትና በግለሰቡና በይሖዋ መካከል ብቻ ያለ የግል ጉዳይ ስለሆነ የጓደኛሞች ጥምቀት ተብሎ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑ የጥምቀት ዕጩዎች ተቃቅፈው ወይም እጅ ለእጅ ተያይዘው እንዲጠመቁ አይፈቀድም።

የፈቃደኝነት አገልግሎት፦ የወረዳ ስብሰባው የተሳካ እንዲሆን የፈቃደኛ ሠራተኞች እርዳታ ያስፈልጋል። በስብሰባው ላይ ለመሥራት የምትችለው ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ቢሆንም እንኳን አገልግሎትህ ይፈለጋል። ልትረዳ የምትችል ከሆነ በስብሰባው ቦታ ስትደርስ ለፈቃደኝነት አገልግሎት ክፍል አስታውቅ። ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆችም ለስብሰባው መሳካት አስተዋፅኦ ሊያደርጉ ይችላሉ፤ ይሁን እንጂ የሚሠሩት ከወላጆቻቸው ጋር ወይም ኃላፊነት ሊወስድ ከሚችል ሌላ ትልቅ ሰው ጋር መሆን አለበት።

ደረት ላይ የሚለጠፉ ካርዶች፦ በስብሰባው ላይ እንዲሁም ወደ ስብሰባው ቦታ ስትሄዱና ስትመጡ ለስብሰባው የተዘጋጀውን ደረት ላይ የሚለጠፍ ካርድ እባካችሁ አድርጉ። አብዛኛውን ጊዜ ይህን ደረት ላይ የሚለጠፍ ካርድ ማድረግ በምንጓዝበት ጊዜ ጥሩ ምስክርነት ለመስጠት ያስችለናል። የስብሰባው ተካፋይ መሆናችንን የሚያሳውቀው ይህ በጥሩ ሁኔታ የተጻፈበት ደረት ላይ የሚለጠፍ ካርድ የቀላል ምግቦች ዝግጅት የተቀላጠፈ እንዲሆን ሊያደርግም ይችላል። በደረት ላይ የሚለጠፉትን ካርዶች በጉባኤያችሁ በኩል ልታገኙ ትችላላችሁ። በስብሰባው ላይ ግን አይገኙም።

የግል መታወቂያ ካርድ፦ ለ“መለኰታዊ ትምህርት” የወረዳ ስብሰባ ከተዘጋጀው ደረት ላይ የሚለጠፍ ካርድ በተጨማሪ እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ የሕክምና መረጃ ካርዱን ይዞ ቢመጣ ጥሩ ነው። የቤቴል ቤተሰብ አባሎችና አቅኚዎችም የመታወቂያ ካርዳቸውን ይዘው መምጣት አለባቸው።

የማስጠንቀቂያ ምክር፦ መኪናችሁን ያቆማችሁት የትም ይሁን የት ሁልጊዜ መኪናችሁን መቆለፍ ይኖርባችኋል። እንዲሁም ከውጭ ሊታይ የሚችል ምንም ነገር በፍጹም ውስጥ ትታችሁ አትሂዱ። የሚቻል ከሆነ ዕቃዎቻችሁን መኪናው ኮፈን ውስጥ አድርጉና ቆልፉባቸው። በተጨማሪም የሰዎችን መብዛት ተመልከተው ከሚመጡ ሌቦችና ኪስ አውላቂዎች ተጠንቀቁ። ውድ ዋጋ ያለውን ማንኛውንም ነገር ያለ ጠባቂ በስብሰባ መቀመጫዎች ላይ መተው አይገባንም። ሕገ ወጥ ግለሰቦች ሕፃናትን ከስብሰባው ቦታ አባብለው ለመውሰድ እንደሞከሩ የሚገልጹ አንዳንድ ሪፖርቶች ደርሰውናል። እባካችሁ ተጠንቀቁ።

ጉባኤዎች ለስብሰባው ጉዞ ብለው የተኰናተሯቸውን ወይም የተከራዩአቸውን ተሽከርካሪዎች ከልክ በላይ ላለመጫን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል። የቄሳርን ሕግ ከመጣስ ወይም ከዚያም በከፋ ሁኔታ ተሽከርካሪውን ከመጠን በላይ በመጫን ወይም ወደ ስብሰባው ቦታ ቀደም ብላችሁ ለመድረስ ስትሉ ሹፌሩ በፍጥነት እንዲነዳ በማበረታታት ወንድሞችና እህቶችን ለአደጋ ከማጋለጥ በዚህም የተነሳ ሊከሰት የሚችለውን የሕይወት ጥፋት ከመጋፈጥ ይልቅ ለመጓጓዣ ተጨማሪ ገንዘብ ለማውጣት ተዘጋጅቶ መምጣት የተሻለ ነው። (ሮሜ 13:1–7፤ ዘዳ. 21:1–9) እንዲህ ባሉ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚጓዙ ኃላፊነት ያላቸው ወንድሞች አስፈላጊ ሲሆን ፍቅራዊ ምክር ከመስጠት ወደኋላ ማለት አይኖርባቸውም።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ