የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/94 ገጽ 1
  • የይሖዋን በኩር በእልልታ ተቀበል!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የይሖዋን በኩር በእልልታ ተቀበል!
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ፍላጎት ያሳዩትን ሁሉ መርዳት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • ‘ምሥራቹን በሚገባ መሥክሩ’
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • መልካም ለማድረግ የምትቀኑ ሁኑ!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ይሖዋ የመታሰቢያውን በዓል ለማክበር የምናደርገውን ጥረት ይባርካል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 2/94 ገጽ 1

የይሖዋን በኩር በእልልታ ተቀበል!

1 በ33 እዘአ ኒሳን 9 ቀን እሁድ ዕለት በእጆቻቸው የዘንባባ ዝንጣፊ የያዙ ሰዎች ያሉበት እጅግ ብዙ ሕዝብ የይሖዋ የበኩር ልጅ የሆነውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን “በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ” አድርጎ በእልልታ ተቀበለው። (ሉቃስ 19:38፤ ዕብ. 1:6) የመጨረሻ ቀናት የነበሩትን የኒሳን 10 ሰኞ ዕለትና የኒሳን 11 ማክሰኞ ዕለት ኢየሱስ ለሕዝብ በሚሰጠው አገልግሎት ተወጥሮ በማሳለፉ በምድራዊ ሕይወቱ የመጨረሻ ቀኖች ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ በሥራ ተጠመዶ ነበር።

2 ዛሬም ከዚያ የሚበልጥ ቁጥር ያለው እጅግ ብዙ ሕዝብ በምሳሌያዊ መንገድ የዘንባባ ዝንጣፊ በእጆቻቸው በመያዝ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአምላካችንና ለበጉ ማዳን ነው” እያሉ ይጮኻሉ። (ራእይ 7:9, 10) መጋቢት 26 (እንደ አገራችን አቆጣጠር መጋቢት 17) ቀን የክርስቶስን ሞት መታሰቢያ በዓል ለማክበር በአንድ ላይ እንሰበሰባለን። ይህ ቀን እየቀረበ በሄደ መጠን አገልግሎታችንን ከፍ ለማድረግ በመጣር ይህንን የውዳሴ ድምጽ ይበልጥ ልናደምቀው እንችላለንን?

3 በመስክ አገልግሎት የምናደርገውን እንቅስቃሴ ከፍ ማድረግ፦ ብዙ አስፋፊዎች በመጋቢት ወር ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል ካሁኑ ተመዝግበዋል። ከእነርሱ ጋር ለመሰለፍ ትፈልጋለህን? የምትፈልግ ከሆነ ሳትዘገይ ማመልከቻውን ሞልተህ ስጥ። ስለሥራው ለማወቅ የምትፈልገው ነገር ካለ ከሽማግሌዎቹ አንዱን ብትጠይቀው አንተን ለመርዳት ደስተኛ ነው።

4 ረዳት አቅኚ ሆነህ ባታገለግልም በመጋቢት ወር ግን በአገልግሎቱ ሙሉ ተሳትፎ ለማድረግ ትፈልግ ይሆናል። በዚህ ወር በየዕለቱ የሚካሄድ የቡድን ምስክርነት ለማደራጀት ጉባኤው ዝግጅት ያደርግ ይሆናል። ለዚህ ዓላማ የሚያገለግል በቂ የአገልግሎት ክልል መዘጋጀት ይኖርበታል።

5 ሁሉም ጉባኤዎች ቅዳሜ መጋቢት 26 ልዩ የመስክ ስምሪት ስብሰባ ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል። ለመታሰቢያው በዓል ሲባል የሚደረጉ ብዙ ዝግጅቶች ቢኖሩም በዚያ ለመገኘት የሚችሉ ሁሉ ቅዳሜ ጠዋት በሚደረገው የመስክ አገልግሎት ላይ ቢሳተፉ ጥሩ ነው። ከቤት ወደ ቤት ከምታደርጉት አገልግሎት በተጨማሪ በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ የጋበዛችኋቸው ሰዎች በዚያ ለመገኘት የሚያስችል መጓጓዣ እንዳላቸው እንዲሁም የስብሰባው ትክክለኛ ቦታና ሰዓት በግልጽ ገብቷቸው እንደሆነ አረጋግጡ።

6 ሌሎችን ጋብዟቸው አበረታቷቸውም፦ ኢየሱስ “ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” በማለት ተከታዮቹን አዝዟል። (1 ቆሮ. 11:24) የኢየሱስን ፈለግ የሚከተሉት ቅቡዓን ይህንን ትዕዛዝ ሲፈጽሙ እያንዳንዱ የይሖዋ አገልጋይ በመታሰቢያው በዓል ላይ ተገኝቶ እንዲመለከት ተጋብዟል። ከሌሎች ሰዎች በተጨማሪም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን፣ ከዚህ በፊት ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያነጋገራችኋቸውን ዘመዶቻችሁን፣ የማያምኑ የትዳር ጓደኛችሁንና በሥራ ቦታችሁ የምታገኟቸውን ሰዎች ልትጋብዟቸው ይገባል። የምትረሱት ሰው እንዳይኖር የስም ዝርዝራቸውን ጽፋችሁ ያዙ።

7 በመታሰቢያው በዓል ላይም እንኳ ፍላጎት ያሳዩትን ሰዎች ለማበረታታት የሚያስችል ተጨማሪ አጋጣሚ ይኖራል። ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኙትን አዳዲሶች ለመቀበል እንድትችሉ ቀደም ብላችሁ ድረሱ። ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችህ መካከል ሦስት ወይም አራት የሚያህሉ ከተገኙ በስብሰባው ወቅት አንድ ሌላ አስፋፊ ከጥቂቶቹ ጋር አብሯቸው እንዲቀመጥ ማድረግህ ጥሩ ይሆናል። ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኙትን ሰዎች በጉባኤው ቋሚ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ ጋብዟቸው። የሕዝብ ንግግሩን እንዲያቀርብ የተመደበው ወንድም የሚያነቃቃ ንግግር ለመስጠት እንዲችል በደንብ መዘጋጀት ይኖርበታል።

8 በሞቱ መታሰቢያ በዓል መደምደሚያ ላይ ድምፃችንን በአንድ ላይ አስተባብረን “የይሖዋን በኩር በእልልታ ተቀበል!” የሚለውን መዝሙር 105⁠ን ስንዘምር ለይሖዋ ውዳሴ በሚያመጣ ቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ያሳለፍነውን ወር ወደኋላ መለስ ብለን ለመመልከት የምንችል ያድ ርገን!

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ