ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
ኢስቶኒያ፦በመስከረም ወር ሪፖርት ያደረጉ 1,753 አስፋፊዎች ነበሩ። ይህ ባለፈው ዓመት ከነበረው አማካይ ወርኃዊ ሪፖርት ጋር ሲነጻጸር 24 በመቶ ጭማሪ ነበር።
ቱርክ፦በ“መለኮታዊ ትምህርት” የወረዳ ስብሰባ ላይ 1,510 ተሰብሳቢዎች ተገኝተው 44 ሕይወታቸውን ለአምላክ መወሰናቸውን በውኃ ጥምቀት አሳይተዋል። የአገሩ የቴሌቪዥን ጣቢያ ስብሰባውን የሚመለከት ጥሩ ሪፖርት አቅርቦ ነበር።
ኢትዮጵያ፦ በአዲስ አበባም ተመሳሳይ ስብሰባ ተደርጎ ከፍተኛው የተሰብሳቢዎች ቁጥር 9,556 የደረሰ ሲሆን ከ16 አገሮች የተወከሉ ልዑካንም ተገኝተዋል። በጣም ደስ የሚል አጋጣሚ ነበር፤ 530 የሚያክሉ ሲጠመቁ ማየቱም ስብሰባውን ይበልጥ ልዩ አድርጎታል።