የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/94 ገጽ 6
  • የተሳሳተ ደግነት ከማሳየት ተጠበቁ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የተሳሳተ ደግነት ከማሳየት ተጠበቁ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የክርስቲያን ጉባኤ አደረጃጀት ምን ይመስላል?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • በጉባኤም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመንግሥቱን ሥራ መደገፍ
    የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
  • ሽማግሌዎች—የሐዋርያው ጳውሎስን አርዓያ መከተላችሁን ቀጥሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
  • ‘ሽማግሌዎችን ጥራ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2025
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 2/94 ገጽ 6

የተሳሳተ ደግነት ከማሳየት ተጠበቁ

1 የይሖዋ ሕዝቦች ባላቸው የደግነትና የልግስና መንፈስ የታወቁ ናቸው። እንዲህ ዓይነቱ ደግነት አብዛኛውን ጊዜ ኢየሱስ ስለ መልካሙ ጎረቤት በተናገረው ልብ የሚነካ ምሳሌው ላይ እንደጠቀሰው ሳምራዊ ቁሳዊ ነገር በመስጠት ይገለጣል። (ሉቃስ 10:29–37) ሆኖም ቁሳዊ እርዳታ ሊደረግላቸው የማይገቡ አንዳንዶች በደግነታችን ለመጠቀም ይሞክራሉ። ስለዚህ ለሌሎች የምናሳየው ፍቅር “በትክክለኛ እውቀትና በሙሉ ማስተዋል” ሚዛኑን የጠበቀ መሆን አለበት። — ፊል. 1:9 አዓት

2 በጉባኤ ውስጥ፦ ለምሳሌ አንድ ሰው ከሥራ ወጣሁ በማለት ወይም ሌላ ምክንያት በመስጠት እርዳታ እንዲደረግለት ይጠይቅ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ እንዲህ ዓይነት ሰዎች ቶሎ ብለው ሥራ ከመፈለግ ይልቅ ለመኖር የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ሌሎች ሰዎች እንዲለግሷቸው ይፈልጉ ይሆናል። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደነዚህ ዓይነቶቹን ሰዎች አስመልክቶ “ሊሠራ የማይወድ አይብላ” ሲል አዟል። — 2 ተሰ. 3:10

3 “ጊዜና አጋጣሚ” በሁላችንም ላይ ለውጥ ያመጣል፤ ስለዚህ የገንዘብ ችግር ኖሮብን “የዕለት እንጀራችንን” ብናጣ ይሖዋ እርሱን ለሚወዱትና ፈቃዱን ለሚያደርጉ ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን ስለሚሰጣቸው ከሚገባ በላይ መጨነቅ አያስፈልገንም። (መክብብ 9:11 አዓት ፤ ማቴ. 6:11, 31, 32) አንድ የተቸገረ ሰው ከአንድ ሽማግሌ ጋር ስለ ችግሩ ቢወያይ ጠቃሚ ሆኖ ሊያገኘው ይችላል። ሽማግሌዎች መንግሥት ለእንዲህ ዓይነት ሰዎች እገዛ ለማድረግ ስላወጣቸው ፕሮግራሞች የሚያውቁት ነገር ይኖር ይሆናል። ማመልከቻ በሚጽፍበት ጊዜ እንዲሁም መንግሥት ባወጣው ፕሮግራም ተጠቃሚ ለመሆን እንዲያሟላ ስለሚፈለግበት ነገር በማስረዳት ሊረዱት ይችላሉ። በዚህም ሆነ በዚያ ሽማግሌዎች የእርዳታ ፈላጊውን ሁኔታ አመዛዝነው መደረግ የሚገባውን ነገር ሊወስኑ ይችላሉ። — ከ1 ጢሞቴዎስ 5:3–16 ጋር አወዳድሩ።

4 ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወሩ የሚያታልሉ፦ ማኅበሩ በጉባኤ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ወንድሞች ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወሩ በሚያታልሉ አጭበርባሪዎች ገንዘብና ቁሳቁስ እንደተወሰደባቸው የሚገልጹ ሪፖርቶች ይደርሱታል። ይህ ሊያስደንቀን አይገባም፤ ምክንያቱም ቅዱሳን ጽሑፎች “ክፉ ሰዎችና አታላዮች፣ እያሳቱና እየሳቱ፣ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ” በማለት አስጠንቅቀውናል። (2 ጢሞ. 3:13) አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ ሰዎች የሚረዳቸው ሰው እንደሌለ፣ ወደ መጡበት እንዳይመለሱ ደግሞ ለመጓጓዣና ለምግብ የሚሆን ገንዘብ እንደሌላቸው ይናገራሉ። ሰዎቹ የተናገሩት እውነታቸውን ቢመስልም እንኳን አብዛኛውን ጊዜ እንደዚህ የሚሉ ሰዎች የይሖዋ ምስክሮች ሳይሆኑ የይሖዋ ምስክር መስለው የቀረቡ ሰዎች ሆነው ተገኝተዋል።

5 አንድ የማታውቁት ሰው እንድትረዱት ከጠየቃችሁ ስለ ጉዳዩ የጉባኤ ሽማግሌዎችን ማማከሩ የተሻለ ነው። እነሱም ሰውየው ወንድማችን መሆን አለመሆኑን ለማወቅ ጥረት ያደርጋሉ። ብዙውን ጊዜ ሰውየው በሚገኝበት ጉባኤ ላለ አንድ ሽማግሌ ስልክ ደውሎ ግለሰቡ ስላለው ሁኔታ ማረጋገጥ ይሻላል። ሳያስቡት የገንዘብ ችግር የገጠማቸው እውነተኛ ወንድሞችና እህቶች ሽማግሌዎች ስለነሱ የሚያጠያይቁት ጉዳዩ የሚመለከታችውን ሁሉ ከችግር ለማዳን በማሰብ መሆኑን ሊረዱ ይገባል። በሌላ በኩል ደግሞ አታላዮች በእንዲህ ዓይነቱ ምርመራ ማንነታቸው ይጋለጣል። የማናውቃቸውና እርዳታ የሚጠይቁንን ሰዎች ሁሉ መጠርጠር ባያስፈልገንም ከክፉ አታላዮች ግን መጠበቅ አለብን።

6 ጠቢቡ ንጉሥ ሰሎሞን “ለተቸገረ ሰው [እርዳታ እንድታደርግለት ለሚገባው ሰው የ1980 ትርጉም ] በጎ ነገር ማድረግ አትከልክል፣ ልታደርግለት የሚቻልህ ሲሆን” የሚል ምክር ሰጥቷል። (ምሳሌ 3:27) የሰዎቹን ማንነት በጥበብ በመለየት የተሳሳተ ደግነት እንዳናሳይ እየተጠነቀቅን ደግነት ማሳየታችንን መቀጠል እንችላለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ