የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/94 ገጽ 2
  • የጥቅምት የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥቅምት የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ጥቅምት 3 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 10/94 ገጽ 2

የጥቅምት የአገልግሎት ስብሰባዎች

ጥቅምት 3 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 191

10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።

17 ደቂቃ፦ “ጊዜው አሁን ነው።” በጥያቄና መልስ። በኅዳር 1993 የመንግሥት አገልግሎታችን በገጽ 4 እና 5 ላይ “መንፈሳዊ ግቦችን ተከታተሉ” በሚለው ንዑስ ርዕስ የተሰጡትን ሐሳቦች ጨምረህ አቅርብ።

18 ደቂቃ፦ “በጥቅምት መጽሔት ላይ አተኩሩ።” ከአድማጮችህ ጋር ተወያይበት። መጽሔቶችን ተጠቅሞ እንዴት ውይይት መጀመር እንደሚቻል የሚያሳዩ ጥሩ ዝግጅት የተደረገባቸው ሁለት ትዕይንቶች አቅርብ። የመጽሔት ደንበኛ ማግኘትን ግብ በማድረግ በየቤቱ መጽሔት ለማበርከት የመጣርን አስፈላጊነት አጉላ።

መዝሙር 212 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥቅምት 10 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 136

10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ማኅበሩ ለተላከለት መዋጮ ያቀረበው ምስጋና ካለ ጨምረህ አቅርብ። የወረዳ ስብሰባ ማሳሰቢያዎች።

15 ደቂቃ፦ መልካም የሆነውን ለማድረግ አንታክት። በሽማግሌ የሚሰጥ ንግግር። መንፈሳዊ ድካም ደስታችንንና ለይሖዋ አገልግሎት ያለንን ቅንዓት ሊቀንስብን ይችላል። መጠበቂያ ግንብ 1–107 በገጽ 13 ባለው ሣጥን ላይ በተሰጡት ሐሳቦች በመጠቀም መንፈሳዊ ጥንካሬያችንን የምናድስባቸውን አንዳንድ መንገዶች ከልስ።

20 ደቂቃ፦ “ፍላጎት ያሳዩትን በፍቅር እርዷቸው።” ከአድማጮች ጋር ተወያይበት። የተሰጡትን አቀራረቦች በመጠቀም ሁለት ትዕይንቶችን አቅርብ።

መዝሙር 121 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥቅምት 17 የሚጀምር ሳምንት

“አምላካዊ ፍርሃት” የወረዳ ስብሰባ የሚደረግበት ሳምንት።

ጥቅምት 24 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 53

10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። ቋሚ የመጽሔት ትእዛዝ አላችሁን? በማለት አድማጮችህን ጠይቅ። መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! የመንግሥቱን መልእክት በማሰራጨት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያበረክታሉ። በማናቸውም አጋጣሚዎች ልናበረክታቸው ይገባል። የመጋቢት 1994 የመንግሥት አገልግሎታችን እያንዳንዱ አስፋፊ “የተወሰነ የመጽሔት ትእዛዝ . . . ከእያንዳንዱ እትም የተወሰነ መጠን ያለው ቅጂ” እንዲኖረው ያበረታታል። ካለዚያ ወቅታዊ መጽሔቶችን እናጣና በትራክቶች ወይም በብሮሸሮች ለመጠቀም እንገደዳለን። እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ቋሚ የመጽሔት ትእዛዝ ቢኖረው ጥሩ ነው። ትእዛዝህን በመጽሔት ማደያ ጠረጴዛ ላይ ላለው ወንድም ስጥ። ቋሚ የመጽሔት ትእዛዝ ያለን መሆኑ የሚያመጣቸውን ጥቅሞች ጥቀስ።

17 ደቂቃ፦ “ማደግህ በግልጥ ይታይ።”

18 ደቂቃ፦ “ዘወትር የምስጋናን መሥዋዕት በማቅረብ የአምላክን መንግሥት አስቀድሙ።” በጥያቄና መልስ። በግል ልንደርስባቸው የምንችላቸውን አንዳንድ ጠቃሚ ግቦች ጥቀስ። ሌሎች የበለጠ እንዲሠሩ ልንረዳቸው የምንችልባቸውን መንገዶች አብራራ።

መዝሙር 172 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥቅምት 31 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 53

8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም በኅዳርና በታኀሣሥ ወራት በረዳት አቅኚነት መሳተፍን እንዲያስቡበት አበረታታ። ይህን ለማድረግ በቂ ጊዜ ማግኘት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ሐሳብ ስጥ። በኅዳር ወር ስለሚበረከተው ጽሑፍ ግለጽ።

7 ደቂቃ፦ “ራእይ መደምደሚያው ለተባለው መጽሐፍ ጥናታችን ከፍተኛ ግምት ስጡት” የሚለውን ርዕስ ከልስ። ዘወትር የመዘጋጀትንና በስብሰባው ላይ የመገኘትን አስፈላጊነት አሳስብ።

30 ደቂቃ፦ “አምላካዊ ፍርሃት” የወረዳ ስብሰባ ይከለሳል። ይህ የእያንዳንዱ ቀን ክለሳ ክፍል በዋና ዋና ነጥቦቹ ላይ ሊያተኩሩና የጉባኤው አባላት ቁልፍ ነጥቦቹን በሕይወታቸውና በመስክ ላይ እንዲሠሩበት ሊያስረዱ ለሚችሉ ብቃት ላላቸው ሁለት ወይም ሦስት ወንድሞች በቅድሚያ ይሰጣል።

መዝሙር 10 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ