የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/94 ገጽ 2
  • የታኅሣሥ የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የታኅሣሥ የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ታኅሣሥ 5 የሚጀምር ሳምንት
  • ታኅሣሥ 12 የሚጀምር ሳምንት
  • ታኅሣሥ 19 የሚጀምር ሳምንት
  • ታኅሣሥ 26 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 12/94 ገጽ 2

የታኅሣሥ የአገልግሎት ስብሰባዎች

ታኅሣሥ 5 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 105

12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በቅርብ የወጡትን መጽሔቶች ስናበረክት ሊጎሉ የሚችሉ አንድ ወይም ሁለት ትኩረት የሚስቡ ርዕሰ ትምህርቶችን ጠቁም። አንድ ብቁ አስፋፊ ከእነዚህ ርዕሶች በአንዱ ተጠቅሞ አንድ አቀራረብ እንዲያሳይ አድርግ።

15 ደቂቃ፦ “በቅርብ ልንከተለው የሚገባ ምሳሌ።” በጥያቄና መልስ።

18 ደቂቃ፦ “በክርስቶስ ትንቢቶች ላይ እንዲያተኩሩ ሌሎችን አነሳሱ።” ከአድማጮች ጋር ተወያይበት። ሁለት አጫጭር ትዕይንቶችን አዘጋጅ። ትክክለኛ የቤት ወደ ቤት መዝገብ የመያዝን አስፈላጊነት አጥብቀህ ግለጽ፤ ምን ነገሮች መመዝገብ እንዳለባቸው በአጭሩ ጠቁም።

መዝሙር 114 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ታኅሣሥ 12 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 19

13 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ማኅበሩ ለተላከለት መዋጮ ያቀረበው ምስጋና ካለ አክለህ አቅርብ። ዓለማዊ በዓልን አስመልክቶ ለሚቀርቡ የመልካም ምኞት መግለጫዎች እንዴት ምላሽ መስጠት እንደሚቻል የሚጠቁሙ ጥቂት ሐሳቦችን ጥቀስ።— የታኅሣሥ 1990 የመንግሥት አገልግሎታችን መጽሔት ገጽ 8 ተመልከት።

14 ደቂቃ፦ “ለትምህርታችሁ የማያቋርጥ ትኩረት ስጡ።” በትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች የሚሰጥ ንግግር። በተለይ ጉባኤው የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ማሳሰቢያ በማጉላት “የ1995 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም” ላይ የሚገኙትን መመሪያዎች ከልስ።

18 ደቂቃ፦ “ለአምላክ ቤት አድናቆት አሳዩ።” በጥያቄና መልስ። ለስብሰባ ሲመጡ ሰዓት የማክበርን አስፈላጊነት በተመለከተ ተጨማሪ ሐሳብ ስጥ።— መጠበቂያ ግንብ 12–111 ገጽ 26–9 ተመልከት።

መዝሙር 53 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ታኅሣሥ 19 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 172

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ጉባኤው ለመስክ አገልግሎት ያደረገውን ዝግጅት ጥቀስ። በቅርብ ጊዜ ውሰጥ የወጡትን መጽሔቶች በጉባኤው ክልል ውስጥ ማበርከት የሚቻልባችውን መንገዶች ጠቁም።

20 ደቂቃ፦ “ለትንቢታዊው ቃል ትኩረት ስጡት።” የዚህ መጽሔት አባሪ። ከ1–8 ያሉትን አንቀጾች በጥያቄና መልስ በሽማግሌ የሚቀርብ። ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሰውን ጥቅሶች ትርጉም አብራራ።

15 ደቂቃ፦ “ተከታዮቹ እንዲሆኑ አበረታቷቸው።” ከአድማጮች ጋር ተወያይበት። ሁለት አጫጭር ትዕይንቶችን አዘጋጅ። ሁሉም በየሳምንቱ ለመስክ አገልግሎት ከሚያውሉት ጊዜ ጥቂቱን ተመላልሶ መጠየቆችን ለማድረግ እንዲጠቀሙበት ሐሳብ ስጥ።

መዝሙር 177 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ታኅሣሥ 26 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 85

5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ስለ መጪው የልዩ ስብሰባ ቀን አንዳንድ ጉዳዮችን አስታውሳቸው።

15 ደቂቃ፦ “ለትንቢታዊው ቃል ትኩረት ስጡት።” የዚህ መጽሔት አባሪ። ከ9–13 ያሉትን አንቀጾች በጥያቄና መልስ በሽማግሌ የሚቀርብ። ለጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት የመዘጋጀትን፣ በጥናቱ ላይ ዘወትር የመገኘትንና የመሳተፍን አስፈላጊነት አጉላ። በእነዚህ አስጨናቂ ጊዜያት ለመመሪያነት በጣም ለሚያስፈልጉን መንፈሳዊ ትምህርቶች ያለህን አድናቆት አሳይ።

15 ደቂቃ፦ ከ1994 የዓመት መጽሐፍ ማበረታቻ አግኙ። ከገጽ 80 (አን. 3) እስከ 82 (የላይኛው ክፍል)፣ ከ83 (አን. 3) እስከ 85 (የላይኛው ክፍል)፣ ከ85 (አን. 3) እስከ 87፣ 96–97፣ 100–101 እና 115 ገጽ ላይ ያሉትን ተሞክሮዎች ሞቅ ባለ መንፈስ አቅርብ። ኢሳይያስ 54:17⁠ን እና የዓመቱን ጥቅስ ጠቅሰህ ሁሉም ብሩህ አመለካከት እንዲኖራቸው አበረታታቸው። እንግሊዝኛ ማንበብ የሚችሉ ሁሉ ለራሳቸው የሚሆን የዓመት መጽሐፍ ቅጂ እንዲያዙ አሳስባቸው። (እንግሊዝኛ አንባቢዎች የሌሏቸው የአማርኛ ጉባኤዎች ያለፈውን የክልል የበላይ ተመልካች ሪፖርት ተመርኩዘው ጉባኤው ስለሚያስፈልጉት ነገሮች ሊገልጹ ይችላሉ።)

10 ደቂቃ፦ በጥር ወር ጽሑፎችን ለማበርከት ተዘጋጁ። ከ1982 በፊት የታተሙትን ማናቸውንም ባለ 192 ገጽ መጽሐፍት መጠቀም ይቻላል። ጉባኤው ከነዚህ ጽሑፎች ውስጥ አንዱም ከሌለው ታላቁን አስተማሪ ማዳመጥ (አማርኛ) የተባለውን መጽሐፍ ከቅርንጫፍ መጠየቅ ይችላል። ጉባኤ በዚህ መጽሐፍ የሚጠቀም ከሆነ ጽሑፉን ከቤት ወደ ቤት ለማበርከት የሚያገለግል አንድ አቀራረብ አዘጋጅ። ሌላ መጽሐፍ የምትጠቀሙ ከሆነ ለእሱ የሚስማሙ አንድ ወይም ሁለት አቀራረቦችን አዘጋጅ። ለአቀራረብ የሚረዱ ሐሳቦች ማመራመር ከተባለው መጽሐፍ ከ9–15 ላይ ወይም ከሐምሌ የመንግሥት አገልግሎታችን ማግኘት ይቻላል። አንድ ብቁ አስፋፊ ይህን አቀራረብ ተጠቅሞ ትዕይንት እንዲያቀርብ አድርግ።

መዝሙር 33 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ