የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/96 ገጽ 2
  • የጥር ወር የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥር ወር የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ጥር 1 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 8 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 15 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 22 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 29 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
km 1/96 ገጽ 2

የጥር ወር የአገልግሎት ስብሰባዎች

ጥር 1 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 121

7 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።

13 ደቂቃ፦ “በማስተዋል ስበኩ።” በዋና ዋናዎቹ ነጥቦች ላይ ተወያዩና “ቤተሰብ/ልጆች”ን በተመለከተ በገጽ 11 ላይ የቀረቡትን ሁለት መግቢያዎች በመጠቀም ማመራመር ከተባለው መጽሐፍ የተወሰዱ አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በአሁኑ ጊዜ በጉባኤው እጅ ያሉ የቆዩ ጽሑፎች የትኞቹ እንደሆኑ ለጉባኤው አስታውቅ።

25 ደቂቃ፦ “የይሖዋን ዝግጅቶች ታደንቃላችሁን?” ሁሉንም አንቀጾች እያነበብክ አወያያቸው። ሁሉም የሚያስፈልጋቸውን ጽሑፍ ለጽሑፍ አገልጋዩ እንዲያዙ ንገራቸው።

መዝሙር 172 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 8 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 4

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ጉባኤው ለጉባኤው እንቅስቃሴም ሆነ የመንግሥቱ ምሥራች በዓለም ዙሪያ እንዲሰበክ ላደረገው የገንዘብ ድጋፍ ተገቢ ምስጋና አቅርብ።

15 ደቂቃ፦ በቅድሚያ የተሰጠ የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሞያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርግ ሰነድ ከችግር በመጠበቅ በኩል ያለው ጥቅም። አንድ ሽማግሌ እያንዳንዱ ሰው በቅድሚያ የተሰጠ የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሞያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርገውን ሰነድ በተገቢው ሁኔታ መሙላቱና ሰነዱን መያዙ አስፈላጊ እንደሆነ እንዲሁም ልጆች ዘወትር የመታወቂያ ካርዱን መያዛቸው ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ከጉባኤው ጋር ይወያያል። የካርዱ ርዕስ እንደሚያሳየው ካርዱ በሕክምና ላይ ሊደረግልን የምንፈልገውን (ወይም የማንፈልገውን) ነገር በቅድሚያ ያስታውቃል። ካርዱ በየዓመቱ መታደስ ያለበት ለምንድን ነው? በቅርቡ የተሞላ ካርድ ጊዜው እንዳለፈበት ወይም በአሁኑ ጊዜ ግለሰቡ ያለውን አቋም እንደማያንጸባርቅ ተደርጎ ከሚታይ ካርድ ይልቅ ተቀባይነት አለው። ስለ ራስህ መናገር በማትችልበት ወቅት ሰነዱ ስለ አንተ ይናገራል። ካርዶቹ ዛሬ ማታ ይታደላሉ። እቤት ወስደን በጥንቃቄ መሙላት ይገባናል፤ ቢሆንም አይፈረምባቸውም። ባለፉት ሁለት ዓመታት እንዳደረግነው ሁሉ የሚፈረመውና የምሥክሮቹ ስምና ፊርማ የሚሰፍረው በመጽሐፍ ጥናቱ መሪዎች ተቆጣጣሪነት በጉባኤው መጽሐፍ ጥናት በሚደረግበት ቦታ ነው። በምስክርነት የሚፈርሙት ሰዎች የካርዱ ባለቤት በሰነዱ ላይ እንደፈረመ መመልከት አለባቸው። ይህም ጥር 15 የሚጀምር ሳምንት ውስጥ የሚደረገው የመጽሐፍ ጥናት ፕሮግራም ካበቃ በኋላ ይከናወናል። (ምን መደረግ እንዳለበት በዝርዝር ለማወቅ ጥር 1994 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 2 ተመልከት። በተጨማሪም ጥቅምት 15, 1991 የተላከውን ደብዳቤ ተመልከት።) የተጠመቁ አስፋፊዎች በሙሉ በቅድሚያ የተሰጠ የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሞያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርገውን ሰነድ መሙላት ይችላሉ። ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ከሁኔታቸውና ከአቋማቸው ጋር በሚስማማ መንገድ ሐሳቡን ከዚህ ካርድ ላይ በመውሰድ የራሳቸውን መመሪያ ሊያዘጋጁ ይችላሉ። ወላጆች ያልተጠመቁ ልጆቻቸው የመታወቂያ ካርዱን እንዲሞሉ ሊረዷቸው ይችላሉ።

20 ደቂቃ፦ “ሰሚዎች ብቻ ሳይሆን አድራጊዎች ሁኑ።” ጥያቄና መልስ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ማስተዋል በተባለው መጽሐፍ ጥራዝ 2 ገጽ 521 በአንቀጽ 1 እና 2 ላይ ተመርኩዘህ የታዛዥነትን አስፈላጊነት አብራራ።

መዝሙር 34 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 15 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 174

12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “በድፍረት ተናገሩ።” በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግርና ውይይት። ጉባኤው እሑድ ዕለት ለአገልግሎት ያለውን ዝግጅት አስታውስ። ለሰጡት ጥሩ ድጋፍ ምስጋና ካቀረብክ በኋላ ምን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ ሐሳብ አቅርብ።

15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት። (ወይም በጥቅምት 1, 1995 መጠበቂያ ግንብ ከ25-8 ባሉት ገጾች ላይ በሚገኘው “ስለ ጊዜው አጣዳፊነት ያላችሁ ስሜት እንዳይቀዘቅዝ ጠብቁት” በሚለው ርዕስ ላይ የተመሠረተ ንግግር።)

18 ደቂቃ፦ “የሰዎችን ሕይወት ለማትረፍ ተመላልሶ መጠየቅ አድርጉ።” የተሰጡትን አቀራረቦች ከጉባኤው ጋር እያነበብክ አብራራ። ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት በተባለው አዲሱ መጽሐፍ ወይም ለዘላለም መኖር በተባለው መጽሐፍ አማካኝነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስጀመር ግብ እንዲያወጡ አበረታታቸው።

መዝሙር 204 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 22 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 6

8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

17 ደቂቃ፦ “ከ1996 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ጥቅም ማግኘት— ክፍል 1።” በትምህርት ቤት የበላይ ተመልካች የሚቀርብ ንግግር። በጥቅምት 1995 የመንግሥት አገልግሎታችን ውስጥ በሚገኘው የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ ላይ ለተማሪ ክፍሎች የቀረቡትን መመሪያዎች ከልስ።

20 ደቂቃ፦ “የአገልግሎቱ ሥራ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኘው እንዴት ነው?” አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 10 ላይ የተመሠረተ ለጉባኤው በሚስማማ መልኩ የሚቀርብ ንግግር።

መዝሙር 222 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 29 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 13

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የጥቅምት የአገልግሎት ሪፖርት። በተጨማሪም ጉባኤው ባለፈው ወር የነበረውን አማካይ የአገልግሎት እንቅስቃሴ ጥቀስ።

15 ደቂቃ፦ “አገልግሎትህን ለማስፋት የምትችልባቸው መንገዶች።” አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 9 ላይ የተመሠረተ ግለት ባለው ተናጋሪ፣ ቢቻል በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ ንግግር። ሁሉንም በተለይም ከዚህ በፊት ረዳት አቅኚ ሆነው የማያውቁትን የተጠመቁ አስፋፊዎች በመጋቢት ወይም በሚያዝያ ረዳት አቅኚ ለመሆን ቀደም ብለው ዕቅድ እንዲያወጡ አበረታታ። እንዲሁም የምሥራቹ አገልጋዮች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ ሄደው ሕይወት አድን የሆነውን መልእክት በሚልዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች የሚያደርሱ ተጨማሪ የዘወትር አቅኚዎችና ልዩ አቅኚዎች እንደሚያስፈልጉ ጠበቅ አድርገህ ግለጽ።

20 ደቂቃ፦ በየካቲት ወር ራእይ መደምደሚያው የተባለውን መጽሐፍ አበርክቱ። የራእይ መጽሐፍ ለረዥም ጊዜ ትርጉሙን መረዳት የማይቻል ምሥጢር ተደርጎ ይታይ የነበረው ለምን እንደሆነ አብራራ። ይህ መጽሐፍ አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት በማስረዳት በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ከአንቀጽ 6 እስከ አንቀጽ 9 ያሉትን ሐሳቦች ከልስ። አስፋፊዎች ከቤት ወደ ቤት ሲያገለግሉ አንዳንድ የመነጋገሪያ ነጥቦች እንዲኖራቸው እነዚህን ሐሳቦች በአእምሯቸው እንዲይዙ አበረታታቸው። በገጽ 98-9 ላይ የሚገኘውን “የራእይ መጽሐፍ አደረጃጀት” የሚለውን ሣጥን አውጣና የራእይን መጽሐፍ ጭብጥ ለመረዳት ባሉት ማራኪ ሥዕሎች ላይ እንዲያተኩሩ አድርግና በእነዚህ ሥዕሎች ተጠቅመው እንዴት ውይይት መጀመር እንደሚችሉ ግለጽ። በመጽሐፉ ፊትና ጀርባ በውስጥ በኩል ያሉትን ትኩረት የሚስቡ ሥዕሎች አሳያቸውና ውይይት ለመጀመር እንዴት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ተናገር። ቅዳሜና እሑድ አገልግሎት ሲወጡ የመጽሐፉን ቅጂ ይዘው እንዲሄዱ አሳስባቸው። የገንዘብ ችግር ያለባቸው አስፋፊዎች የራሳቸውን ቅጂ ይዘው ሄደው ለሰዎች እንዲያሳዩና መጽሐፉን ለማግኘት የሚፈልጉ ሰዎች ሲያጋጥሟቸው ትእዛዝ እንዲቀበሉ ሐሳብ አቅርብላቸው። ከዚያ በኋላ በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት የሚበረከት ቅጂ ካለው አስፋፊ ጋር ሊሄዱ ይችላሉ።

መዝሙር 143 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ