ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ጥር፦ ከ1982 በፊት የታተመ በጉባኤው እጅ የሚገኝ እንደ ዘላለማዊ ዓላማ (እንግሊዝኛ) ያለ ማንኛውም ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ። እነዚህ መጽሐፎች የሌሏቸው ጉባኤዎች የቤተሰብ ኑሮ እና/ወይም ወጣትነትህ የተባሉትን መጽሐፎች በ3 ብር ሊያበረክቱ ይችላሉ። የካቲት፦ የቤተሰብህን ኑሮ አስደሳች አድርገው ወይም ራእይ— ታላቁ መደምደሚያ ደርሷል! የተባለው መጽሐፍ። ወይም በጥር የተበረከቱትን ጽሑፎች። መጋቢት፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። ሚያዝያ፦ መጽሔቶች።
◼ በእጃችን ያሉ አዳዲስ ጽሑፎች:- የ1994 የንቁ! ጥራዝ፤ የተለያዩ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጁ የብሬል ጽሑፎች (እባካችሁ በቂ መረጃ ለማግኘት ጠይቁ።)
◼ በቅርቡ ይመጣሉ ተብለው የሚጠበቁ ጽሑፎች፦ አማርኛ፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። (የጽሑፍ መጠየቂያ ቅጽ S-14-AM አሁኑኑ ሞልታችሁ መላክ ትችላላችሁ።)
◼ ልዩ የአገልግሎት ክልል የምንሸፍንበት የሚቀጥለው ዘመቻ ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባሉት ወራት እንዲደረግ ታቅዷል። ልዩ አቅኚ ሆነው ለማገልገል የሚፈልጉ የዘወትር አቅኚዎች ስማቸውን፣ ነጠላ ወይም ባለ ትዳር መሆናቸውን፣ ዕድሜያቸውን፣ የተጠመቁበትን ቀን፣ ከላይ ከተጠቀሱት ወራት ውስጥ በየትኞቹ ወራት ማገልገል እንደሚችሉና መናገር የሚችሏቸውን ቋንቋዎች በመጥቀስ ለጉባኤያቸው ሰብሳቢ የበላይ ተመልካች ሊያመለክቱ ይችላሉ። የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ እስከ ጥር 31, 1996 ድረስ እነዚህን ነጥቦች ከአስተያየታቸው ጋር በማከል ሊልክልን ይገባል።