በድፍረት ተናገሩ
1 በአሁኑ ጊዜ ሰዎች ሰብዓዊ ሥራ መሥራታቸው፣ የቤተሰባቸውን ፍላጎት ለማሟላት እንደ ሱቅ ወደመሳሰሉ ቦታዎች መሄዳቸው ወይም መዝናናታቸው የተለመደ ነገር ነው። በዚህ ምክንያት ሰዎች ከቤት ወጣ ይላሉ። ሰዎች ቤታቸው ካልተገኙ አንድ ቦታ ሄደዋል ማለት ነው። ግባችን ሰዎችን ማነጋገር ስለሆነ መንገድ ላይ፣ ገበያ ውስጥ ወይም መሥሪያ ቤት የምናገኛቸውን ሰዎች የማናነጋግርበት ምክንያት የለም። ጳውሎስ ‘የሚያገኛቸውን ሰዎች’ ቀረብ ብሎ የመመስከር ልማድ ነበረው። (ሥራ 17:17) በዚያን ጊዜ ያገኙትን ሰው ማነጋገር ውጤታማ የስብከት ዘዴ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ዛሬም ቢሆን ይህ ዘዴ ውጤታማ ዘዴ ነው።
2 ብዙውን ጊዜ ከቤት ወደ ቤት ስንሄድ ሰዎች ዝም ብለው በእግራቸው ሲንሸራሸሩ ወይም ሰው ሲጠብቁ እናያቸዋለን። ብሩህ በሆነ ቀን ከቤት ውጪ ተቀምጠው ወይም ሲሠሩ ልናገኛቸው እንችላለን። ውይይት ለመጀመር የሚያስፈልገን ወዳጃዊ የሆነ ፈገግታ ወይም ሰላምታ ብቻ ሊሆን ይችላል። በዚያው አካባቢ የሚኖሩ ከሆነ ቤታቸው ሄደን አጥተናቸው ሊሆን እንደሚችልና ከእነርሱ ጋር ለመነጋገር የሚያስችል አጋጣሚ በማግኘታችን እንደተደሰትን ልንነግራቸው እንችላለን። ብዙዎች ደፈር ብለው ውይይት በመጀመራቸው አስደሳች ተሞክሮዎች አግኝተዋል።
3 ድፍረት ጥሩ ውጤቶችን ያስገኛል፦ አንድ ወንድም የቆሙ፣ አውቶቡስ የሚጠብቁ፣ ዘና ብለው የሚራመዱ ወይም መኪናቸው ውስጥ የተቀመጡ ሰዎችን ቀረብ ብሎ እንደሚያነጋግራቸው ተናግሯል። ሞቅ ባለ ፈገግታና ደስ በሚል የድምፅ ቃና ሊጠይቃቸው እንደመጣ ጎረቤታቸው ሆኖ ይቀርባቸዋል። በዚህ ዘዴ በመጠቀም ብዙ ጽሑፎችን ከማበርከቱም በላይ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች አስጀምሯል።
4 ስለዚህ በሚቀጥለው ጊዜ እሑድ ወይም በሌሎች ቀናት ከቤት ወደ ቤት ስትመሰክር ሰዎችን ቤታቸው ካላገኘሃቸው ደፈር ብለህ በመንገድ ወይም በሌላ በማንኛውም ቦታ የምታገኛቸውን ሰዎች ለምን አታነጋግርም? (1 ተሰ. 2:2) እርግጥ አብዛኞቻችሁ ብዙውን ጊዜ በመንገድ ላይ ስትመሰክሩ ቆይታችኋል። ሆኖም እዚህ ላይ ለመግለጽ የተፈለገው ነጥብ ሰው እስክታገኙ ድረስ በአውቶቡስ ፌርማታ ቁጭ ብላችሁ ከመጠበቅ ወይም አንድ ሰው አነጋግራችሁ የሚቀጥለውን ሰው እስከምታነጋግሩ ብዙ መንገድ በመሄድ ብዙ ደቂቃዎች ከማጥፋት ይልቅ በድፍረት ሰዎችን አነጋግሩ የሚል ነው። የሰዎችን ፊት በማየት ብቻ በጭፍኑ አትፍረዱ። ሰውዬው ብዙም የማይቸኩል ከሆነ ፊት ለፊት እየተመለከትከው ወዳጃዊ ሰላምታ ለማቅረብ ሞክር። በሌላ በኩል አብዛኛውን ጊዜ የምታገለግሉት መንገድ ላይና ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ከሆነ ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት በይበልጥ በማሳለፍ ድፍረት አሳዩ። እንዲህ የምታደርጉ ከሆነ ውጤታማ አገልግሎት ከማከናወናችሁ በተጨማሪ ከአገልግሎታችሁ ታላቅ ደስታ ታገኛላችሁ።