የየካቲት ወር የአገልግሎት ስብሰባዎች
የካቲት 5 የሚጀምር ሳምንት
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።
15 ደቂቃ፦ “የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል በየዕለቱ እውነትን ማወጅ።” ጥያቄና መልስ። አንቀጽ 5ን አንብብ።
20 ደቂቃ፦ “የራእይ መጽሐፍ የእውነተኛ ደስታ ቁልፍ ነው።” የተሰጡትን አቀራረቦች አብራራና አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በተጨማሪም “ቤተሰቦችን ደስተኛ ለማድረግ የሚረዱ ዝግጅቶች” የሚለውን በሰኔ 1995 መአ ላይ የወጣውን ትምህርት ተመልከት።
መዝሙር 19 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 191
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። “በሚያዝያ ወር መጽሔት ለማበርከት ተዘጋጁ።” ምሥራቹን በማስታወቁ ሥራ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ያላቸውን ዋጋ ጎላ አድርገህ ግለጽ። ርዕሰ ትምህርቱን አንብብና ጉባኤው በሚያዝያ ከሌላው ወር በተለየ ሁኔታ መጽሔት ለማበርከት ምን እንደሚያደርግ በጥቅሉ ግለጽ።
13 ደቂቃ፦ “ሰሚ ጆሮ ማግኘት የምችለው እንዴት ነው?” ጥያቄና መልስ። ሁለት አስፋፊዎች በትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ገጽ 165-7 ከ10-21 ባሉት አንቀጾች ላይ በተሰጡት አንዳንድ ሐሳቦች በመጠቀም ከቤት ወደ ቤት በመሄድ አዲስ ሰው ሲያነጋግሩ ይበልጥ ግለት ለማሳየት የሚሞክሩት እንዴት እንደሆነ እንዲወያዩ አድርግ።
20 ደቂቃ፦ “የይሖዋን የጽድቅ ደረጃዎች መጠበቅ።” አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ከ127-132 ባሉት ገጾች ላይ የተመሠረተ። ከ127-130 ባሉት ገጾች ላይ የተመሠረተ የአሥር ደቂቃ ንግግር ካቀረብክ በኋላ “አካላዊ ንጽሕና” እና “መዝናኛ” የሚሉት ንዑስ ርዕሶች በጥያቄና መልስ ይቀርባሉ። በተለይ ዘወትር የመታጠብን፣ ልብሶቻችንን አጥበን አስፈላጊ ከሆነ የመተኮስን፣ ግድግዳዎችን፣ የቤት ዕቃዎችን፣ የመታጠቢያ ገንዳዎችን፣ መደርደሪያዎችን፣ የመብራት ማብሪያና ማጥፊያዎችን፣ መስኮቶችን፣ የቤታችንን ወለል የማጽዳትንና የማጠብን እንዲሁም ቆሻሻን ከቤት ወይም ከደጃፍ ላይ የማስወገድን አስፈላጊነት ጎላ አድርገህ ግለጽ። በተጨማሪም ‘የዓለም ክፍል ላለመሆን’ ቴሌቪዥን በማየት እንዲሁም ከዓለማዊ ዘመዶቻችንና ከምናውቃቸው ዓለማዊ ሰዎች ጋር ባለን ቅርርብ ረገድ ጠንቃቃ የመሆንን አስፈላጊነት ግለጽ።
መዝሙር 34 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 19 የሚጀምር ሳምንት
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ “ከ1996 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ጥቅም ማግኘት— ክፍል 2።” በትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች የሚቀርብ ንግግር። የአምላክን ቃል በየዕለቱ የማንበብን አስፈላጊነት ጠበቅ አድርገህ ግለጽ።
20 ደቂቃ፦ “እንዲያስተውሉ እርዷቸው።” የተሰጡትን ተመላልሶ ለመጠየቅ የሚያስችሉ አቀራረቦች ከልስ። በትራክቶች፣ በደስታ ኑር! ወይም አምላክ ስለ እኛ ያስባልን? በተባሉት ብሮሹሮችም ሆነ እውቀት ወይም ለዘላለም መኖር በተባሉት መጻሕፍት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስጀመርን ግብ ጎላ አድርገህ ግለጽ። ከዚያም በጉባኤያችሁ ውስጥ ምን ያህል ሰዎች በብሮሹሮች እያጠኑ እንዳሉ በትክክል ተናገር። ቁጥሩ አነስተኛ ከሆነ በብዙ አገሮች ውስጥ ከሚገኙት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች መካከል ግማሹ ወይም ከዚያ በላይ በደስታ ኑር! እንደተባለው ባሉ ብሮሹሮች እንደሚያጠኑ ተናገር። በዚህ ብሮሹር ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ ማስጠናት የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ጠቃሚ ፍንጭ ስለሚሰጠውና ከጥቂት ጊዜ በፊት ስለተዘጋጀው ባለ ሁለት ገጽ ወረቀት ሐሳብ ስጥ። አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።
መዝሙር 53 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 113
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ ሰዎችን የሚማርኩ አቀራረቦች መዘጋጀት። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ወይም ሌላ ሽማግሌ ከሁለት ወይም ከሦስት አስፋፊዎች ጋር ሆነው በትዳር ውስጥ ስለሚያጋጥሙ ችግሮች፣ ስለ ወጣት ጥፋተኞች ወይም ሥራ ለማግኘት ስላሉት አስቸጋሪ ሁኔታዎች የመሳሰሉ በአካባቢው ያሉ ሰዎችን ስሜት የሚያንጸባርቅ አቀራረብ መጠቀሙ የሚያስገኛቸውን ጥቅሞች ይወያያሉ። በምትኖሩበት አካባቢ የሚናፈሱ አንዳንድ ትኩስ ዜናዎችን ጥቀስና እነዚህ ዜናዎች ውይይት ለመጀመር እንዴት ሊያገለግሉ እንደሚችሉ ተወያዩ።
20 ደቂቃ፦ በመጋቢት ወር ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት። ውይይት ለመጀመር ልንጠቀምባቸው የምንችላቸውን አንዳንድ የመጽሐፉን አስደሳች ገጽታዎች ጥቀስ። (1) በገጽ 4-5, 86, 124-5, 188-9 ላይ እንዳሉት በመሳሰሉ ማራኪ ሥዕሎች ላይ እንዲያተኩሩ አድርግ። (2) እያንዳንዱ ምዕራፍ የክለሳ ጥያቄዎች በማቅረብ እንደሚደመድም አሳይና እነዚህን ጥያቄዎች መግቢያ አድርገን ልንጠቀምባቸው የምንችለው እንዴት እንደሆነ ተናገር። የቤቱ ባለቤት መልሶቹን ለማወቅ ይፈልግ እንደሆነ ልንጠይቀው እንችላለን። በገጽ 11, 22, 61, 149 ላይ ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል አንዳንዶቹን ጥቀስ። (3) ገጽ 102 ላይ ያለውን ሣጥን ጥቀስና “የመጨረሻውን ቀን ልዩ የሚያደርጉት አንዳንድ ገጽታዎች” ፍላጎት ለማነሳሳት እንዴት ልንጠቀምባቸው እንደምንችል ሐሳብ አቅርብ። (4) መጽሐፉ በተለይ እድገት የሚያደርጉ ጥናቶችን ለመምራት እንዲያገለግል ተብሎ የተዘጋጀው እንዴት እንደሆነ ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። ምዕራፎቹ አጫጭር ናቸው፣ ትምህርቱ ቀላል ነው፣ ሰውን የመንካት ኃይል ያላቸው ጥቅሶች ተጠቅሰዋል እንዲሁም ጥያቄዎቹ ቁልፍ በሆኑ ነጥቦች ላይ ያተኩራሉ። ሁሉም ጥናቶች የማስጀመር ግብ ይዘው መጽሐፉን እንዲያበረክቱ አሳስባቸው።
መዝሙር 121 እና የመደምደሚያ ጸሎት።