በሚያዝያ ወር መጽሔት ለማበርከት ተዘጋጁ
በ1996 የቀን መቁጠሪያ ላይ እንደተገለጸው በዚህ ዓመት የጌታ ራት ሚያዝያ 2 ይከበራል። ሁላችንም በዚህ ታላቅ በዓል ስሜታችን ተነሳስቶ በሚያዝያ ወር በሚደረገው የመጽሔት ስርጭት በቅንዓት እንካፈል። የምንጠቀምባቸው መጽሔቶች ምንኛ ወቅታዊ ናቸው! የሚያዝያ 1 መጠበቂያ ግንብ ባለፈው ዓመት የአውራጃ ስብሰባ ላይ በቀረበው “የዘላለሙን ንጉሥ አወድሱ!” በሚለው የሕዝብ ንግግር ላይ ያተኩራል። የሚያዝያ 15 መጠበቂያ ግንብ “የሐሰት ሃይማኖት ፍጻሜ ቀርቧል” የሚል ጭብጥ በነበረው ባለፈው ዓመት ልዩ የሕዝብ ንግግር ላይ ያተኮረ ሐሳብ ይዟል። ሚያዝያ 21 የሚቀርበው “በጠማማ ትውልድ ውስጥ ያለ ነቀፋ መኖር” የሚለው የዚህ ዓመት ልዩ ንግግር ተጨማሪ ኃይል ሊሰጠን ይገባል። የሚያዝያ 22 ንቁ! “ጦርነት የማይኖርበት ጊዜ” የሚል ርዕስ አለው።
በሚያዝያ ከሌላው ወር ይበልጥ መጽሔት ማሰራጨት አለብን። ዕቅድ የምናወጣበት ጊዜ አሁን ነው። ብዙዎች ረዳት አቅኚ ለመሆን ይፈልጋሉ። ተጨማሪ የሚያዝያ ወር መጽሔቶች ቅጂዎችን እንደ አስፈላጊነቱ ማዘዝ ይቻላል። መጽሔት የሚበረከትባቸው ቀናት መመደብ ይቻላል። ሁሉም ሰው መሳተፍ እንዲችል ጠዋት፣ ከሰዓት እና/ወይም ማታ ለማበርከት ዕቅድ አውጡ። ሁላችንም ‘ቃሉን የምናደርግ’ እንሁን። በመዝሙር 69:9 ላይ ስለ መሲሑ እንደተተነበየው እኛም “የቤትህ ቅናት ይበላኛል” ለማለት ያብቃን።— ያዕ. 1:22፤ ዮሐ. 2:17