የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች
የመታሰቢያው በዓል የሚከበርበት ቀን ማክሰኞ ሚያዝያ 2 ከመድረሱ በፊት ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች እነሆ:-
◼ ተናጋሪውን ጨምሮ ሁሉም ሰዎች በዓሉ የሚከበርበት ትክክለኛ ሰዓትና ቦታ ሊነገራቸው ይገባል።
◼ ትክክለኛው ዓይነት ቂጣና ወይን መዘጋጀት ይገባዋል።— የካቲት 15, 1985 የእንግሊዝኛ መጠበቂያ ግንብ ገጽ 19 ተመልከቱ።
◼ አመቺ የሆነ ጠረጴዛ፣ የጠረጴዛ ልብስ፣ ሳህኖችና ብርጭቆዎች ቀደም ብለው ወደ መንግሥት አዳራሾቹ መጥተው መቀመጥ ይኖርባቸዋል።
◼ የመንግሥት አዳራሹ ወይም ሌላው የመሰብሰቢያ ቦታ ቀደም ብሎ በሚገባ መጽዳት ይኖርበታል።
◼ አስተናጋጆች እንዲሁም ቂጣውንና ወይኑን የሚያዞሩት አስቀድሞ ሊመረጡና ተገቢ የሆነውን የአሠራር ሥርዓትና የእነርሱን ተግባር በተመለከተ መመሪያ ሊሰጣቸው ይገባል።
◼ የአካል ችግር ያለባቸውንና በቦታው መገኘት የማይችሉትን ቅቡዓን ለማስተናገድ ዝግጅት መደረግ ይኖርበታል።
◼ የበዓሉ ሥርዓት በአንድ የመንግሥት አዳራሽ ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ እንዲከናወን ታቅዶ ከሆነ በኮሪደሩ፣ በመግቢያው፣ በሕዝብ መተላለፊያዎችና በመኪና ማቆሚያዎች ላይ ጭንቅንቅ እንዳይፈጠር በጉባኤዎቹ መካከል ጥሩ ቅንጅት ሊኖር ይገባል።