የኅዳር የአገልግሎት ስብሰባዎች
ኅዳር 4 የሚጀምር ሳምንት
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የአገሪቱንና የጉባኤውን የነሐሴ ወር የአገልግሎት ሪፖርት በሚመለከት አንዳንድ ሐሳቦችን አቅርብ። የጥያቄ ሣጥን።
15 ደቂቃ፦ “የአምላክን ቃል በትክክል የምትጠቀም ነህን?” ጥያቄና መልስ። ማመራመር ከተሰኘው መጽሐፍ ከገጽ 57-58 ላይ “መጽሐፍ ቅዱስን እንድንመረምር የሚያደርጉን ምክንያቶች” ከሚለው ተጨማሪ ሐሳቦችን አቅርብ።
20 ደቂቃ፦ ‘ይህም የዘላለም ሕይወት ነው።’ (አንቀጽ 1-5) በአንቀጽ 1 ላይ የተመረኮዘ አጭር የመግቢያ ሐሳብ ካቀረብክ በኋላ ጥሩ ችሎታ ያላቸው አስፋፊዎች አንቀጽ 2-5 ላይ ባለው መግቢያ ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርቡ አድርግ። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስጀመርን ግብ ጠበቅ አድርገህ ግለጽ።
መዝሙር 32 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 11 የሚጀምር ሳምንት
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
20 ደቂቃ፦ “ይሖዋ ረዳቴ ነው።” ማስተዋል ከተባለው መጽሐፍ ጥራዝ 1 ገጽ 516 “Courage” ከሚለው ርዕስ ጨምረህ አቅርብ። ሰኔ 8, 1992 የእንግሊዝኛ ንቁ! ገጽ 16-18 ላይ “ከሌሎች የተለየሁ መሆን ያለብኝ ለምንድን ነው?” ከሚለው ርዕስና ኅዳር 15, 1993 መጠበቂያ ግንብ ላይ ካሉት የጥናት ርዕሶች ንዑስ ርዕሶቹን ጎላ አድርገህ ግለጽ። ትምህርቱ በተለይ ከዓለም የተለዩ የመሆንን፣ ከቤት ወደ ቤት የመስበክን፣ በመንገድ ላይ በሚደረገው ምሥክርነት ሁሉንም ዓይነት ሰዎች የማነጋገርን፣ ጽሑፎቻችንን የማበርከትንና ክርስቲያናዊ ያልሆኑ ባሕሎችን የማስወገድን አስፈላጊነት የሚያብራራ ይሁን። ክፍሉ በንግግርና ከ3-5 ደቂቃ በሚፈጅ ጥያቄና መልስ ይቅረብ።
15 ደቂቃ፦ ‘ይህም የዘላለም ሕይወት ነው።’ (አንቀጽ 6-8) ጥናት ለማስጀመር ቀጥተኛ የሆነ ጥያቄ ማቅረብ ያለውን ጠቀሜታ ተወያዩ። ተሞክሮ ያላቸው አስፋፊዎች ከአንቀጽ 6-7 ላይ ባለው አቀራረብ ተጠቅመው ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርቡ አድርግ። በመጀመሪያ ጉብኝት ጊዜ ጥናት ማስጀመር የቻሉባቸው ጊዜያት ካሉ አድማጮች እንዲናገሩ ጋብዛቸው። አንድ ሰው ጥናት እንዲጀምር ቀጥተኛ ግብዣ በቀረበለት ጊዜ “እሺ! ወደ ቤት ግቡ። መጽሐፍ ቅዱስ ባጠና ደስ ይለኛል” በማለት መለሰ። ከእርሱ ጋር ጥናት ተጀመረ፤ በቀጣዩ ሳምንት መላው ቤተሰብ በጥናቱ ላይ ተገኘ። በአጭር ጊዜ ውስጥም ሁሉም ስብሰባ ላይ መገኘትና በምሥክርነቱ ሥራ መካፈል ጀመሩ! የሰኔ 1996 የመንግሥት አገልግሎታችንን አባሪ በሚቀጥለው ሳምንት በሚደረገው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ይዘው እንዲመጡ አሳስብ።
መዝሙር 172 እና የመደምደሚያ ጸሎት
ኅዳር 18 የሚጀምር ሳምንት
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ “ተልዕኮ ተሰጥቶናል።” ጥያቄና መልስ። 1-109 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 21, 22 አንቀጽ 13-16ን በአጭሩ ከልስ።
25 ደቂቃ፦ እድገት የሚያደርጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን መምራት። በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ ንግግር። ከአንድ ዓመት ለሚበልጥ ጊዜ እውቀት በተባለው መጽሐፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስንመራ ቆይተናል። አንዳንድ ተማሪዎች መጽሐፉን አጥንተው የጨረሱ ሲሆን ሌሎች ተማሪዎችም መጽሐፉን ወደማጠናቀቁ ተቃርበዋል። አዳዲስ ሰዎች እውነትን በፍጥነት እንዲማሩና በሕይወታቸው እንዲሠሩበት እንዲሁም የጉባኤ አባላት እንዲሆኑ የመርዳት ግብ ይዘን መጽሐፉን እንድናስጠና ማበረታቻ ተሰጥቶን ነበር። በማስተማሩ ሥራ ውጤታማ መሆን እንድንችል በሰኔ 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን መጽሔት ላይ የወጣው አባሪ ጥሩ ሐሳቦችን አቅርቧል። በዚህ እትም ከአንቀጽ 3-13 ላይ የሰፈረውን ተማሪዎችን በጥሩ ችሎታ ለማስተማር ማድረግ የምንችላቸውን አንዳንድ ነገሮች በአጭሩ ከልስ። ቀጥሎም ከአንቀጽ 14-22 ላይ እንደተጠቆመው አዎንታዊ እርምጃ እንዲወስዱ ለመርዳት ምን ሊደረግ እንደሚቻል ትኩረት ስጥበት። አንቀጽ 15, 17, 20-21ን አንብብ። የጉባኤው አስፋፊዎች ጥሩ ውጤቶችን ያገኙት እንዴት እንደሆነ የሚገልጹ አንዳንድ ጠቃሚ ሐሳቦችን አቅርብ። ጥሩ ውጤቶች እንዴት እንደተገኙ የሚያሳይ ጥቂት አዎንታዊ ዘገባዎችን ተናገር። መጽሐፍ ቅዱስ በማስጠናቱ ሥራ የበለጠ እንዲካፈሉ አበረታታ።
መዝሙር 85 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 25 የሚጀምር ሳምንት
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ “አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም” እና “አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም።” የስብሰባውን ጎላ ያሉ ገጽታዎች ግለጽና በንግግርህ መደምደሚያ ላይ የሁለቱን ስብሰባ ጭብጦች ደግመህ ተናገር።
18 ደቂቃ፦ ከጥቅምት—ታኅሣሥ 1994 ንቁ! ላይ “ንጹሕ ለመሆን ያለውን ትግል ማሸነፍ” የሚለውን ክፍል ከልስ። ተግባራዊ የሆኑ የክለሳ ጥያቄዎችን ለማቅረብ የመጨረሻዎቹን አምስት ደቂቃዎች ተጠቀም።
12 ደቂቃ፦ በታኅሣሥ የሚበረከተው ጽሑፍ ምን እንደሆነ ግለጽ። የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ የተሰኘውን መጽሐፍ በግለት አበርክቱ። መጽሐፉን ለማበርከት የሚያስችለው አንደኛው መንገድ ከ84ኛው ታሪክ የሚጀምረውን ክፍል 6 ላይ ያለውን ስለ ኢየሱስ ሕይወት በሚናገረው ላይ በማተኮር ነው። ወይም ወላጆች ጥሩ ባሕርያትን ለምሳሌ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ሥር በአምላክ ላይ መታመንንና መደገፍን (ታሪክ 58) ወይም ንጹሕ ሥነ ምግባርን (ታሪክ 24)፣ ሐቀኝነትን (ታሪክ 47) እና ትህትናን (ታሪክ 69) የመሰሉትን ባሕርያት ለልጆቻቸው ለማስተማር መጽሐፉ የሚረዳቸው እንዴት እንደሆነ ልታሳይ ትችላለህ። በእድሜ የገፉ ብዙ ሰዎችም ይህን መጽሐፍ በማንበባቸው የመጽሐፍ ቅዱስን አጠቃላይ ይዘት ለማወቅ ችለዋል። እባክህ ልጆች ይህን መጽሐፍ በትምህርት ቤት፣ ከቤት ወደ ቤትና በሌሎች ቦታዎች ለሌሎች ልጆች እንዲያበረክቱና ጥናት ለማስጀመር እንዲጣጣሩ አበረታታ። በየትኛውም አጋጣሚ ፍላጎት ያለው ሰው ከተገኘ ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ ቁርጥ ያለ ቀጠሮ ሊያዝ ይገባል።
መዝሙር 180 እና የመደምደሚያ ጸሎት