የስብሰባ መጋበዣ ወረቀቶችን በሚገባ ተጠቀሙባቸው
1 የጉባኤ ስብሰባ መጋበዣ ወረቀቶች የመንግሥት አዳራሹን አድራሻና የስብሰባዎቹን ትክክለኛ ሰዓት በአካባቢያችን ላሉት ሰዎች ለማሳወቅ ይጠቅማሉ። ለምታገኙት ለእያንዳንዱ ሰው አንድ የስብሰባ መጋበዣ ወረቀት መስጠት ተገቢ ነው። ይህን ለማድረግ እንዲቻል እያንዳንዱ ጉባኤ በቂ መጠን ያለው የስብሰባ መጋበዣ ወረቀቶች እንዲኖረው ያስፈልጋል። በየዓመቱ በጥር ወር የስብሰባ ሰዓታቸውን የሚቀይሩ ጉባኤዎች አዲሱን የስብሰባ ሰዓት የያዘ በቂ መጠን ያለው የስብሰባ መጋበዣ ወረቀቶች በእጃቸው እንዲኖር አዲስ የስብሰባ መጋበዣ ወረቀት እንዲዘጋጅላቸው አስቀድመው በጥቅምት ማዘዝ ይኖርባቸዋል። የስብሰባ መጋበዣ ወረቀቶች ማዘዣ ቅጽ የተዘጋጀው ለዚሁ ዓላማ ነው። የስብሰባ መጋበዣ ወረቀቶቹን ካገኛችሁ በኋላ በተሻለ መንገድ ጥቅም ላይ ልታውሏቸው የምትችሉት እንዴት ነው?
2 ብዙ አስፋፊዎች የስብሰባ መጋበዣ ወረቀቶቹን መስጠት ራሳቸውን ለማስተዋወቅና ውይይት ለመጀመር ውጤታማ መንገድ ሆኖ አግኝተውታል። የስብሰባ ሰዓቱን ወይም በስተጀርባ ያለውን መልእክት መጥቀስ ስለ ሥራችንም ሆነ ስለ ሥራው ዓላማ ለመወያየት መንገድ ሊከፍት ይችላል። በሚቀጥለው ጊዜ የሚቀርበውን የሕዝብ ንግግር ጭብጥ መጥቀስ ይቻላል። ወላጆች ከቤት ወደ ቤት ሲሄዱ ትንንሽ ልጆቻቸው የስብሰባ መጋበዣ ወረቀቶችን እንዲያበረክቱ በማድረግ በአገልግሎቱ እንዲሳተፉ ማድረግ ይችላሉ። በደብዳቤ ምሥክርነት በመስጠት የሚሳተፉ አስፋፊዎች ደብዳቤው ውስጥ አንድ የስብሰባ መጋበዣ ወረቀት በመጨመር ሰውዬው ስብሰባ እንዲካፈል ሊጋብዙት ይችላሉ። ሰዎቹን ቤታቸው በማናገኝበት ጊዜ የስብሰባ መጋበዣ ወረቀቶችን ትተን መሄድ እንችላለን፤ ነገር ግን ከውጭ ሌላ ሰው እንዳያያቸው በበሩ ስር በደንብ መግባታቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
3 የስብሰባ መጋበዣ ወረቀቶች ቅን ልብ ያላቸውን ሰዎች ወደ እውነት ለመምራት ትልቅ ድርሻ አበርክተዋል። መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት የነበራትን የረዥም ጊዜ ፍላጎት በስብሰባ መጋበዣ ወረቀቶች አማካኝነት ለማሟላት የቻለች አንዲት ሴት እንዳለች የሚናገር ተሞክሮ አለ። ወደ አምላክ ስትጸልይ ካመሸች በኋላ በነጋታው ጠዋት ምሥክር የሆኑ ባልና ሚስት የበርዋን ደወል ይደውላሉ። በሩ ላይ በተሠራው ቀዳዳ እየተመለከተች በሩን እንደማትከፍት ነገረቻቸው። ምሥክሮቹ አንድ የስብሰባ መጋበዣ ወረቀት በበሩ ስር ሰደዱላት። ጽሑፉ “መጽሐፍ ቅዱስን ይማሩ” የሚል ርዕስ አለው። ጽሑፉን ካየች በኋላ በሩን ከፈተች። ወዲያውኑ ጥናት ተጀመረላትና ከጊዜ በኋላ ተጠመቀች። የአምላክ መንፈስ ያለውን ኃይል በፍጹም አቅልላችሁ አትመልከቱ። አገልግሎታችንን ሙሉ በሙሉ ስናከናውን በስብሰባ መጋበዣ ወረቀቶች ዘወትር በሚገባ እንጠቀም።