ለመጪዎቹ ወራት ምን ዕቅድ አውጥታችኋል?
1 ያወጣነው ግብ ላይ መድረስ የምንችለው ጊዜያችንን በተሻለ መንገድ እንዴት እንደምንጠቀምበት አስቀድመን ዕቅድ ስናወጣ አይደለምን? መጪዎቹ ወራት ቲኦክራሲያዊ ፍላጎቶችን ለማስቀደም የተለያዩ አጋጣሚዎችን ይከፍቱልናል። (ምሳሌ 21:5) ከእነዚህ መካከል አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው?
2 “የአምላክ የሕይወት መንገድ” የተባለው የአውራጃ ስብሰባ ሁላችንም በእቅዳችን ውስጥ ልናስገባው የሚገባ አንዱ ወቅት ነው። በሁሉም የስብሰባው ቀናት መገኘት እንድትችሉ ከሥራ እረፍት ለመውጣት ወይም ከትምህርት ቤት ፈቃድ ለመጠየቅ ዝግጅት አድርጉ። ቀደም ብላችሁ ለጉዟችሁ የሚሆን ገንዘብ አጠራቅሙ እንዲሁም ሌሎች ዝግጅቶችን አድርጉ።
3 ትምህርት ቤት በሚዘጋበት ወቅት ወጣቶች ለአንድ ወይም ከአንድ ለሚበልጡ ወራት ረዳት አቅኚ እንዲሆኑ አጋጣሚ ይሰጣቸዋል። ሌሎችም አምስት ቅዳሜና እሑድ ባሉት በነሐሴ ወር ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል ከወዲሁ እቅድ ሊያወጡ ይችላሉ። መጪው የነሐሴ ወር የአገልግሎት ዓመቱን የምናጠናቅቅበት ወር እንደመሆኑ መጠን እያንዳንዱ ግለሰብ የተቻላቸውን ያህል ሙሉ በሙሉ በአገልግሎት እንዲካፈል ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል።
4 የአገልግሎት ክልሉን ለመሸፈን እርዳታ የሚያስፈልገውን በአቅራቢያህ የሚገኝ ጉባኤ ለማገዝ እቅድ ታወጣላችሁን? በአካባቢህ እርዳታ የሚያስፈልገው ጉባኤ የትኛው እንደሆነ የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ለሽማግሌዎች ሊነግራቸው ይችላል። የዕረፍት ጊዜህን ከመኖሪያህ ራቅ ባለ አካባቢ የምታሳልፍ ከሆነ በምትሄድበት አካባቢ ባለ ጉባኤ በሚደረጉ ስብሰባዎች ለመገኘትና በአገልግሎት ለመካፈል እቅድ አውጣ። የይሖዋ ምሥክር ያልሆኑ ዘመዶችህን የምትጠይቅ ከሆነ እውነትን ለእነርሱ ለማካፈል የሚያስችሉህን የተለያዩ መንገዶች ቀደም ብለህ ተዘጋጅባቸው።
5 ለመጪዎቹ ወራት ምን ዕቅድ አውጥታችኋል? በሕይወታችሁ ሁሉ መንግሥቱን ማስቀደማችሁን ለመቀጠል እንድትችሉ የሚረዳችሁንና መንፈሳዊ ኃይል የሚያስገኝላችሁን እንዲህ ያለውን አጋጣሚ አቅልላችሁ አትመልከቱ።—ማቴ. 6:33፤ ኤፌ. 5:15, 16