የሰኔ የአገልግሎት ስብሰባዎች
ሰኔ 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 42 (92)
8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።
15 ደቂቃ፦ ‘ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጁ መሆን።’ ጥያቄና መልስ። ከየካቲት 15, 1989 መጠበቂያ ግንብ (የእንግሊዝኛ) ገጽ 22-4 ላይ አጠር ያለ ሐሳብ ስጥ።
22 ደቂቃ፦ “‘ለሰው ሁሉ’ መመስከር።” አንድ ሽማግሌ በሰኔ ወር የሚበረከተው ታላቅ ሰው የተባለው መጽሐፍ መሆኑን ይገልጻል። ሽማግሌውና ተሞክሮ ያላቸው ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች በቀረቡት መግቢያዎች ላይ በጋራ ይወያያሉ። በአካባቢያችሁ ምን ዓይነት ሃይማኖቶች እንዳሉ በአጭሩ ከገለጽህ በኋላ ውይይት ለመጀመር እንድንችል አንዳንድ የመወያያ ነጥቦችን በአእምሯችን መያዝ እንዳለብን ግለጽ። አንድ ወይም ሁለት አጠር ያሉ ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ።
መዝሙር 47 (112) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 8 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 92 (209)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ፦ “የጌታን ንብረት በአግባቡ መያዝ።” አባሪው ላይ ያለውን ሐሳብ በመሸፈን አንድ ሽማግሌ በንግግር ያቀርበዋል።
20 ደቂቃ፦ “ሥራውን ለመፈጸም የሁላችንም ተሳትፎ ያስፈልጋል።” ጥያቄና መልስ። አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለማከናወን ሽማግሌዎች የፈቃደኛ ሠራተኞችን ትብብር ለምን እንደሚፈልጉ ግለጽ። እንደ መንግሥት አዳራሽ ጽዳትና ጥገና፣ የታመሙትንና አረጋውያንን መርዳት እንዲሁም የጉባኤውን ክልል መሸፈንን የመሳሰሉትን በጉባኤያችሁ ውስጥ ትብብር የሚጠይቁ ጉዳዮች ጥቀስ። ሽማግሌዎች ብዙ አስፋፊዎች በፈቃደኝነት ለሚሰጡት ድጋፍ ያላቸውን አድናቆት እንዲገልጹ ጋብዝ። እያንዳንዱ ሰው የሚያደርገው ጥረት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አበክረህ ግለጽ።
መዝሙር 36 (81) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 15 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 87 (195)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
17 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት ወይም ቅንዓቴ ቀጥቅዟልን? በሚል ጭብጥ ከመጠበቂያ ግንብ 24-108 ከገጽ 14-15 በአንቀጽ 14-16 ላይ ተመስርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ለበርካታ ዓመታት በትጋት ያገለገሉት ወንድሞችና እህቶች የቅዱስ አገልግሎታቸውን ጥራትና ብዛት መለስ ብለው እንዲገመግሙ አበረታታ።
18 ደቂቃ፦ “ተጋደሉ።” በመጠበቂያ ግንብ 1-107 ከገጽ 8-11 ላይ የተመሠረተ ንግግር። ከመስከረም 1 ጀምሮ አቅኚ እንዲሆኑ በሚያበረታታ መንፈስ የዘወትር አቅኚ ሆኖ ማገልገል ያለውን ጠቀሜታ አብራራ።
መዝሙር 80 (180) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 22 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 97 (217)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የጉባኤው ሒሳብ ምርመራ መቼ እንደተጠናቀቀ ግለጽ።
15 ደቂቃ፦ የመጽሔት ደንበኞች ማግኘት የሚቻልበት መንገድ። አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች በዝርዝር ተናገር:- የተበረከተላቸውን ሰዎች ሁሉ መዝግቦ መያዝ፣ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ተመልሶ ማነጋገር፣ ፍላጎቱ እንዳይቀዘቅዝ በቅርብ ጊዜ ከወጡ መጽሔቶች አዳዲስ ሐሳቦችን ማቅረብ። ጎረቤቶቻችንን፣ የሥራ ባልደረቦቻችንን፣ ሱቅ ውስጥ የሚሠሩ ሰዎችን፣ በነዳጅ ማደያዎች የሚሠሩትንና ሌሎችንም የመጽሔት ደንበኞች ማድረግ እንደሚቻል ጥቀስ። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ካሉ ኮንትራት እንዲገቡ ሐሳብ አቅርቡላቸው። የመጽሔት ደንበኞች በማፍራት ረገድ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ገንቢ ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ።
20 ደቂቃ፦ አቅኚዎች ሌሎችን ይረዳሉ። አቅኚዎች ሌሎችን በግል እንዲረዱ የሚያስችለውን ዝግጅት በመከለስ በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ ንግግር። ከዚህ ቀደም ሌሎችን የመርዳት ፕሮግራሞች ተጀምረው እንደነበር ግለጽ። (አዋጅ ነጋሪዎች 100፤ የመንግሥት አገልግሎታችን 7/79 1, 3) ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ የተጠመቁ ከአንድ ሚልዮን በላይ የሚሆኑ አዳዲስ አስፋፊዎች ስልጠና ያስፈልጋቸዋል። “አቅኚዎች ሌሎችን ይረዳሉ” የተባለው ፕሮግራም በአቅኚነት አገልግሎት ትምህርት ቤት የተካፈሉ የዘወትርና ልዩ አቅኚዎች ያገኙትን ተሞክሮና ስልጠና እንዲጠቀሙበት ያስችላቸዋል። የእያንዳንዱ አቅኚ ግብ በዓመት ሁለት አስፋፊዎች በስብከቱ ሥራ ይበልጥ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩና ተሳትፏቸውን ከፍ ለማድረግ እንዲጣጣሩ መርዳት ነው። ትኩረት የሚደረገው ፍቅራዊ የሆነና ደግነት የሞላበት ማበረታቻ በመስጠቱ ላይ ስለሆነ ድጋፍ የሚሰጣቸው አስፋፊዎች ምንም የሚፈሩበት ምክንያት አይኖርም። ይህ አዲስ ፕሮግራም በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ አስፋፊዎች ይበልጥ ውጤታማ አገልጋዮች መሆን እንዲችሉ ያግዛቸዋል።
መዝሙር 91 (207) እና የመደምደሚያ ጸሎት።