የጥቅምት የአገልግሎት ስብሰባዎች
ማስታወሻ፦ በጥቅምትና በኅዳር እያንዳንዱ ጉባኤ የአውራጃ ስብሰባ ይኖረዋል። ስለዚህ ጉባኤዎች ተግባራዊ በሆነ መንገድ የፕሮግራሙን ክፍሎች እንደገና ለማስተካከል ነፃነት ሊሰማቸው ይገባል። እባካችሁ፣ ከወዲሁ ጥሩ የማስተማር ችሎታ ያላቸው ሦስት ወንድሞች በኅዳር ወር የአውራጃ ስብሰባውን ፕሮግራም ክለሳ ለማቅረብ እንዲዘጋጁ መድቡ።
ጥቅምት 4 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 84 (190)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
17 ደቂቃ፦ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎች መልስ መፈለግ። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄ ካለው ፍላጎት ያሳየ ሰው ጋር የተገናኘ አንድ አስፋፊ የጥያቄውን መልስ ለማግኘት ወደ አንድ የጉባኤ አገልጋይ ይሄዳል። የጉባኤ አገልጋዩ በቀጥታ መልሱን ከመንገር ይልቅ እንዴት ፈልጎ ማግኘት እንደሚችል ያስረዳዋል። በመጀመሪያ፣ የትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ጥናት 7 አንቀጽ 8-9 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ይከልሳል። ከዚያም በአገልግሎት ክልላቸው ውስጥ በተደጋጋሚ ለሚነሣ አንድ ጥያቄ መልስ ለማግኘት አብረው ምርምር ያደርጋሉ። ከጉዳዩ ጋር ዝምድና ያላቸውን ጽሑፎች ይመለከቱና መጽሐፍ ቅዱስ ለሚሰጠው መልስ የቀረበውን መሠረታዊ ምክንያት ግልጽ የሚያደርጉ አሳማኝ ነጥቦች ይፈልጋሉ። አድማጮች ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት እንዲህ ዓይነት የሚክስ ጥናት እንዲያደርጉ አበረታታ።
18 ደቂቃ፦ ለመጽሔቶች ትኩረት ስጡ! ጉባኤው ባለፈው ወር ያበረከተውን ጠቅላላ የመጽሔቶች ቁጥር ተናገር። ይህ ቁጥር ከማኅበሩ ከደረሳችሁ የመጽሔቶች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል ልዩነት ይታያል? ከፍተኛ ልዩነት የሚታይ ከሆነ ምን መደረግ አለበት? አድማጮች ቀጥሎ በቀረቡት ነጥቦች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ:- (1) እያንዳንዱ አስፋፊ በቂ ሆኖም ተገቢ መጠን ያለው መጽሔት ማዘዝ አለበት። (2) እያንዳንዱን ቅዳሜ የመጽሔት ቀን አድርጋችሁ ተመልከቱት። (3) በግል የአገልግሎት ፕሮግራማችሁ ውስጥ በየወሩ መጽሔት ለማበርከት የሚያስችል ዝግጅት አድርጉ። (4) በመጽሔቶች ተጠቅማችሁ ውይይት በመጀመር ከአሁኑ ይበልጥ መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት ለመስጠት ዕቅድ አውጡ። (5) የንግድና የተለያየ ሙያ ያላቸውን ሰዎች ሊማርኩ የሚችሉ ከሙያቸው ጋር የሚስማማ ርዕስ ያላቸውን መጽሔቶች ለማበርከት ሞክሩ። (6) ያበረከታችኋቸውን መጽሔቶች በትክክል መዝግባችሁ ያዙ፤ እንዲሁም በቅርብ የወጡትን እትሞች ይዛችሁ በመመለስ የመጽሔት ደንበኞች ለማፍራት ሞክሩ። (7) የመጽሔት ክምችት እንዳይፈጠር ማንኛውንም የቆየ ቅጂ በጥሩ ሁኔታ ተጠቀሙበት። በቅርብ የወጡትን መጽሔቶች አሳይና ፍላጎት ሊያነሳሱ የሚችሉትን ርዕሶች ጠቁም። አንድ ጎልማሳ እና አንድ ወጣት ወንድም (እህት) እያንዳንዳቸው መጽሔት ለማበርከት የሚያስችል አጠር ያለ አቀራረብ በሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርቡ አድርግ።—የመስከረም 1995 የመንግሥት አገልግሎታችንን አባሪ ተመልከት።
መዝሙር 44 (105) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 11 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 22 (47)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ፦ ልናወጣቸው የምንችላቸው ግቦች። ንግግርና ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። በመጋቢት 15, 1997 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 11 ላይ የሚገኘው ሣጥን ውስጥ የቀረቡትን ተግባራዊ ግቦች ከልስ። በረዳት ወይም በዘወትር አቅኚነት አገልግሎት እንዲካፈሉ አበረታታ። እነዚህ ግቦች ላይ መድረሳችን በግል ጥቅም የሚያስገኝልን እንዴት እንደሆነ ግለጽ። አድማጮች አንዳንድ ቲኦክራሲያዊ ግቦች ላይ በመድረሳቸው የተሰማቸውን ደስታ እንዲናገሩ ጋብዝ።
20 ደቂቃ፦ “ከስብሰባዎች የበለጠ ደስታ ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?” ጥያቄና መልስ። ስብሰባዎች ላይ አንዳችን ለሌላው አሳቢነት ማሳየትና የብርታት ምንጭ መሆን የምንችልበትን መንገድ የሚጠቁሙ አንዳንድ ምሳሌዎችን ተናገር። አድማጮች ከራሳቸው ተሞክሮ በመነሳት ምሳሌዎች እንዲሰጡ ጋብዝ።
መዝሙር 65 (152) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 18 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 91 (207)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና የመስክ አገልግሎት ተሞክሮዎች። እባክህ፣ በሚቀጥለው ሳምንት ሁሉም የመስከረም የመንግሥት አገልግሎታችንን ቅጂ ይዘው እንዲመጡ አሳስባቸው።
13 ደቂቃ፦ “የመኖሪያ ቦታ ልትቀይር ነውን?” በጸሐፊው የሚቀርብ የሚያበረታታ ንግግር። አስፋፊዎች ወደ ሌላ ጉባኤ መዛወሩን አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኙት ማንኛውንም መንፈሳዊ ኪሳራ ማስወገድ እንዲቻል የሄዱበትን አዲስ አካባቢ ጥሩ አድርገው መላመዳቸው አስፈላጊ ነው። እንዲህ ዓይነቶቹን ዕቅዶች ለሽማግሌዎች የማሳወቁንና አዲሱን ጉባኤ በማግኘት ረገድ የእነርሱን እርዳታ የመጠየቁን አስፈላጊነት አጉላ።
22 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
መዝሙር 59 (139) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 15 (35)
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በኅዳር ወር ሁሉም ለዘላለም መኖር መጽሐፍ ለማበርከት እንዲዘጋጁ እርዳቸው። “አምላክ ለሚቀርብለት ጸሎት መልስ ይሰጣልን?” በሚለው ጥያቄ ላይ የሚያተኩር አቀራረብ ማዘጋጀት የሚቻልበትን መንገድ ግለጽ። ለዘላለም መኖር መጽሐፍ ምዕራፍ 27 አንቀጽ 1-3 ላይ በሚገኙት ነጥቦች ተጠቀም። አንድ ጥቅስ የሚጠቀስበት ቀለል ያለ አቀራረብ በሠርቶ ማሳያ አቅርብ።
15 ደቂቃ፦ “የአምላክ ትንቢታዊ ቃል ይፈጸማል!” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ ሸፍነው። አዲስ ከወጣው መጽሐፍ ላይ የምንኖርበት ጊዜ የያዘውን ትርጉም የሚያጎሉ ጥቂት ዝርዝር ሐሳቦች ተናገር።
15 ደቂቃ፦ “የተመደበልንን የአገልግሎት ክልል ለመሸፈን ድፍረት ማዳበር።” የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ጥያቄና መልስ አማካኝነት በመስከረም የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የወጣው ርዕስ የያዛቸውን ዋና ዋና ነጥቦች ይከልሳል። እባክህ አንቀጽ 4-6ን አንብብ። ጠበኛ የሆኑ የቤት ባለቤቶች ሲያጋጥሙን ምን ማለት እንዳለብንና ምን ማለት እንደሌለብን የሚያሳዩ አጠር ያሉ አራት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። ሠርቶ ማሳያዎቹ በእውነታው ላይ የተመሠረቱ እንጂ ለማሳቅ ብለው የሚቀርቡ መሆን የለባቸውም። ‘የዋሕና ዝግተኛ መንፈስ’ ማሳየት ያለውን ጥቅም እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ። ከዚህ በፊት ያሉትን ክፍሎች በማሳጠር ይህ ክፍል እስከ 22 ደቂቃ ሊራዘም ይችላል። የመጨረሻዎቹን 3 ደቂቃዎች ተጠቅመህ በኅዳርና በታኅሣሥ ሁሉም ለዘላለም መኖር መጽሐፍ እንዲያበረክቱ አበረታታ።
መዝሙር 64 (151) እና የመደምደሚያ ጸሎት።