የ2000 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም
መመሪያዎች
በ2000 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት በሚከተሉት ዝግጅቶች መሠረት ይከናወናል።
ትምህርቶቹ የተወሰዱባቸው ጽሑፎች፦ ክፍሎቹ በሚከተሉት ጽሑፎች ላይ የተመሠረቱ ይሆናሉ:- መጽሐፍ ቅዱስ [1954]፣ መጠበቂያ ግንብ [wAM]፣ “ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሣሽነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው” (የ1990 እትም) [si]፣ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? [fyAM]፣ “መጽሐፍ ቅዱሳዊ የውይይት አርዕስት” [tdAM]፣ እና እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው? [gtAM]።
ትምህርት ቤቱ ልክ በሰዓቱ በመዝሙር፣ በጸሎትና አጠር ባለ ሰላምታ ይከፈታል። በፕሮግራሙ ውስጥ የተካተቱትን ክፍሎች አስቀድሞ መናገር አስፈላጊ አይደለም። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች እያንዳንዱን ክፍል ሲያስተዋውቅ ማብራሪያ የሚሰጥበትን ርዕስ ይናገራል። ክፍሎቹ በሚከተለው መንገድ ይከናወናሉ:-
ክፍል ቁ. 1፦ 15 ደቂቃ። ይህ ክፍል በአንድ ሽማግሌ ወይም በአንድ የጉባኤ አገልጋይ መቅረብ ይኖርበታል። ክፍሉ በመጠበቂያ ግንብ ወይም “ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሣሽነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው” በተባለው መጽሐፍ ላይ የተመሠረተ ይሆናል። ክፍሉ ከመጠበቂያ ግንብ በሚቀርብበት ጊዜ ለ15 ደቂቃ እንደ ማስተማሪያ ንግግር ሆኖ ይቀርባል። የክለሳ ጥያቄ አይኖረውም። “ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ” ከተባለው መጽሐፍ በሚቀርብበት ጊዜ ከ10 እስከ 12 ደቂቃ እንደ ማስተማሪያ ንግግር ይቀርብና በጽሑፉ ላይ ባሉት ጥያቄዎች በመጠቀም ከ3 እስከ 5 ደቂቃ የክለሳ ጥያቄ ይቀርባል። ዓላማው የተመደበውን ክፍል መሸፈን ብቻ ሳይሆን ለጉባኤው በጣም ጠቃሚ የሆነውን ሐሳብ እያጎሉ በትምህርቱ ተግባራዊ ጠቀሜታ ላይ ማተኮር ሊሆን ይገባል። በፕሮግራሙ ላይ የተጠቀሰውን ጭብጥ መጠቀም ይገባል።
ይህንን ክፍል እንዲያቀርቡ የተመደቡት ወንድሞች በተወሰነው ጊዜ ለመጨረስ ንቁ መሆን አለባቸው። አስፈላጊ ከሆነ ወይም ተናጋሪው ከጠየቀ በግል ምክር መስጠት ይቻላል።
ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦች፦ 6 ደቂቃ። ይህ ክፍል ትምህርቱን ጉባኤው ከሚያስፈልጉት ነገሮች ጋር በጥሩ ሁኔታ አዛምዶ ማቅረብ በሚችል ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ ሊቀርብ ይገባል። ጭብጥ መስጠት አያስፈልግም። የተመደቡትን ምዕራፎች ሐሳብ በመከለስ ብቻ መቅረብ የለበትም። የተመደቡትን ምዕራፎች አጠቃላይ ሐሳብ ከ30 እስከ 60 ሴኮንድ ውስጥ መከለስ ይቻላል። ቢሆንም ዋናው ዓላማ አድማጮች ትምህርቱ ለምን እና እንዴት ሊጠቅመን እንደሚችል እንዲገነዘቡ መርዳት ነው። ከዚህ በኋላ ተማሪዎቹ ወደየክፍላቸው መሄድ እንደሚችሉ የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ያስታውቃል።
ክፍል ቁ. 2፦ 5 ደቂቃ። ይህ ክፍል አንድ ወንድም የሚያቀርበው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ነው። ትምህርት ቤቱ በሚካሄድበት በዋናው አዳራሽም ይሁን በተጨማሪዎቹ ክፍሎች በዚሁ መንገድ ይቀርባል። ምንባቡ ብዙውን ጊዜ አጠር ያለ ስለሚሆን ተማሪው በመግቢያውና በመደምደሚያው ላይ መጠነኛ ማብራሪያ ለመስጠት ያስችለዋል። ከበስተኋላ ያለውን ታሪካዊ አመጣጥ፣ ትንቢታዊ ወይም መሠረተ ትምህርታዊ ትርጉሙንና የመሠረታዊ ሥርዓቶቹን ተግባራዊነት መጥቀስ ይቻላል። የተመደቡት ጥቅሶች በሙሉ ሳይቆራረጡ መነበብ ይኖርባቸዋል። የሚነበቡት ጥቅሶች ተከታታይ ካልሆኑ ግን ተማሪው ቀጥሎ የሚያነበውን ጥቅስ ቁጥር መናገር ይችላል።
ክፍል ቁ. 3፦ 5 ደቂቃ። ይህ ክፍል ለአንዲት እህት ይሰጣል። የዚህ ክፍል ትምህርት የተመሠረተው ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? በተባለው መጽሐፍ ወይም መጽሐፍ ቅዱሳዊ የውይይት አርዕስት በተባለው ቡክሌት ላይ ነው። መቼቱ መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት፣ ተመላልሶ መጠየቅ፣ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወይም ሌላ ዓይነት የመስክ አገልግሎት ገጽታ ሊኖረው ይችላል። አንዳንድ ጊዜ አንዲት ወላጅ ከትንሽ ልጅዋ ጋር ስትወያይ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል። በክፍሉ ውስጥ የሚሳተፉ ክፍሉን ሲያቀርቡ መቀመጥ ወይም መቆም ይችላሉ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በተለይ ተማሪዋ የቤቱን ባለቤት ወይም ልጅዋን ስለ ትምህርቱ እንዲያስቡና ጥቅሶቹ እንዴት በሥራ ላይ እንደሚውሉ እንዲገነዘቡ የምትረዳበትን መንገድ ለማየት ይፈልጋል። ይህን ክፍል እንድታቀርብ የተመደበችው ማንበብ የምትችል መሆን አለባት። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች አንድ ረዳት ይመድብላታል፤ ሆኖም ተጨማሪ ረዳት ማዘጋጀት ይቻላል። ተማሪዋ ክፍሏን የምታቀርበው የቤተሰብ ደስታ ከተባለው መጽሐፍ በሚሆንበት ጊዜ የቤቱ ባለቤት የተወሰኑ አንቀጾችን እንዲያነብ ማድረግ ወይም አለማድረግ ትችላለች። በአንደኛ ደረጃ ሊታሰብበት የሚገባው መቼቱ ሳይሆን ትምህርቱ ውጤታማ በሆነ መንገድ መቅረቡ ነው።
ክፍል ቁ. 4፦ 5 ደቂቃ። ይህ ክፍል ለአንድ ወንድም ወይም ለአንዲት እህት ይሰጣል። የዚህ ክፍል ትምህርት የተመሠረተው እስከ ዛሬ ድረስ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው በተባለው መጽሐፍ ላይ ነው። የእያንዳንዱ ክፍል ጭብጥ በፕሮግራሙ ላይ ሰፍሯል። ክፍሉ ለአንድ ወንድም በሚሰጥበት ጊዜ ለጠቅላላው ጉባኤ በንግግር መልክ መቅረብ ይኖርበታል። ክፍሉ ለእህት ከተሰጠ ለሦስተኛው ክፍል በተሰጠው መመሪያ መሠረት መቅረብ ይኖርበታል።
ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም፦ ይህ ክፍል በእያንዳንዱ ሳምንት ከመዝሙር ቁጥር በኋላ በቅንፍ ውስጥ ተቀምጧል። ፕሮግራሙን በመከተል በየሳምንቱ አሥር የሚሆኑ ገጾችን በማንበብ መላውን መጽሐፍ ቅዱስ በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ አንብቦ መጨረስ ይቻላል። በትምህርት ቤቱ ፕሮግራም ውስጥም ይሁን በክለሳ ጥያቄዎች ውስጥ ከተጨማሪው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም ምንም ክፍል አይወሰድም።
ማሳሰቢያ፦ ምክር መስጠትን፣ ጊዜ መጠበቅን፣ የክለሳ ጥያቄዎችና ክፍሎች መዘጋጀትን በሚመለከት ተጨማሪ ሐሳብ ወይም መመሪያ ለማግኘት የጥቅምት 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3ን ተመልከቱ።
ፕሮግራም
ጥር 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 4-6
መዝሙር ቁ. 33 (72) [ኤርምያስ 49-52]
ቁ. 1፦ የይሖዋን በረከቶች አድንቁ (w98 1/1 ገጽ 22-4)
ቁ. 2፦ ዘዳግም 6:4-19
ቁ. 3፦ የተለየ ሃይማኖት ካላቸው ወላጆች ጋር ሰላማዊ ዝምድና መያዝ (fy ገጽ 134-5 አን. 16-19)
ቁ. 4፦ ስለ ምሕረት የተሰጠ ትምህርት (gt ምዕ. 40)
ጥር 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 7-10
ቁ. 24 (50) [ሰቆቃወ ኤርምያስ 1-5]
ቁ. 1፦ እውነተኛውን አምላክ አስከብሩ (w98 1/1 ገጽ 30-1)
ቁ. 2፦ ዘዳግም 8:1-18
ቁ. 3፦ የእንጀራ ወላጅ መሆን የሚያስከትለው ፈታኝ ሁኔታ (fy ገጽ 136-9 አን. 20-5)
ቁ. 4፦ ኢየሱስ የመከራከሪያ ርዕስ ሆነ (gt ምዕ. 41)
ጥር 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 11-14
ቁ. 54 (132) [ሕዝቅኤል 1-9]
ቁ. 1፦ ለምናፈቅራቸው ሰዎች ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው? (w98 1/15 ገጽ 19-22)
ቁ. 2፦ ዘዳግም 11:1-12
ቁ. 3፦ ቁሳዊ ነገሮች ለማግኘት የምታደርጉት ጥረት ቤተሰባችሁን እንዲከፋፍል አትፍቀዱ (fy ገጽ 140-1 አን. 26-8)
ቁ. 4፦ ኢየሱስ ፈሪሳውያንን ነቀፈ (gt ምዕ. 42)
ጥር 24 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 15-19
ቁ. 70 (162) [ሕዝቅኤል 10-16]
ቁ. 1፦ እውነት ያለው የመለወጥና የማስማማት ኃይል (w98 1/15 ገጽ 29-31)
ቁ. 2፦ ዘዳግም 19:11-21
ቁ. 3፦ የአልኮል ሱሰኝነት የሚያስከትለው ጉዳት (fy ገጽ 142-3 አን. 1-4)
ቁ. 4፦ ጀልባ ላይ ሆኖ የተናገራቸው አምስት ምሳሌዎች (gt ምዕ. 43 አን. 1-8)
ጥር 31 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 20-23
ቁ. 6 (13) [ሕዝቅኤል 17-21]
ቁ. 1፦ ውዳሴና ሽንገላን በተመለከተ ያለው ቅዱስ ጽሑፋዊ አመለካከት (w98 2/1 ገጽ 29-31)
ቁ. 2፦ ዘዳግም 20:10-20
ቁ. 3፦ የአልኮል ሱሰኛ የሆነን የቤተሰብ አባል መርዳት (fy ገጽ 143-7 አን. 5-13)
ቁ. 4፦ ደቀ መዛሙርቱ ከኢየሱስ ትምህርቶች ጥቅም ያገኙበት መንገድ (gt ምዕ. 43 አን. 9-19)
የካቲት 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 24-27
ቁ. 100 (222) [ሕዝቅኤል 22-27]
ቁ. 1፦ ብሩህ አመለካከት ለመያዝ የሚያስችል ትክክለኛ መሠረት (w98 2/1 ገጽ 4-6)
ቁ. 2፦ ዘዳግም 25:5-16
ቁ. 3፦ በቤተሰብ አባላት ላይ የሚፈጸም ጥቃትና ማስወገድ የሚቻልበት መንገድ (fy ገጽ 147-50 አን. 14-22)
ቁ. 4፦ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ከኢየሱስ ተጨማሪ ትምህርት በማግኘት ተባረኩ (gt ምዕ. 43 አን. 20-31)
የካቲት 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 28-30
ቁ. 80 (180) [ሕዝቅኤል 28-33]
ቁ. 1፦ የአመስጋኝነትን መንፈስ አዳብሩ (w98 2/15 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ ዘዳግም 28:1-14
ቁ. 3፦ መለያየት መፍትሄ ነውን? (fy ገጽ 150-2 አን. 23-6)
ቁ. 4፦ ኢየሱስ አንድ አስፈሪ ማዕበል ጸጥ አሰኘ (gt ምዕ. 44)
የካቲት 21 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 31-34
ቁ. 21 (46) [ሕዝቅኤል 34-39]
ቁ. 1፦ ዘዳግም—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 40-1 አን. 30-4)
ቁ. 2፦ ዘዳግም 32:35-43
ቁ. 3፦ የጋብቻ ችግሮችን መፍታት የሚቻልበት ቅዱስ ጽሑፋዊ መንገድ (fy ገጽ 153-6 አን. 1-9)
ቁ. 4፦ በአጋንንት ተይዞ የነበረ ሰው ደቀ መዝሙር ሆነ (gt ምዕ. 45)
የካቲት 28 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 1-5
ቁ. 18 (42) [ሕዝቅኤል 40-45]
ቁ. 1፦ የኢያሱ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 42 አን. 1-5)
ቁ. 2፦ ኢያሱ 2:8-16
ቁ. 3፦ ትዳር የሚጠይቀውን ግዴታ ማሟላት (fy ገጽ 156-8 አን. 10-13)
ቁ. 4፦ ልብሱን ነካች (gt ምዕ. 46)
መጋቢት 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 6-9
ቁ. 1፦ ወላጆች—ልጆቻችሁን ከአደጋ ጠብቁ! (w98 2/15 ገጽ 8-11)
ቁ. 3፦ በቅዱስ ጽሑፉ መሠረት ለፍቺ የሚያበቃ ምክንያት (fy ገጽ 158-9 አን. 14-16)
ቁ. 4፦ ለቅሶ ወደ ታላቅ ደስታ ተለወጠ (gt ምዕ. 47)
መጋቢት 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 10-13
ቁ. 58 (138) [ዳንኤል 3-7]
ቁ. 1፦ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ግርማ ሞገስ ምን ይላል? (w98 2/15 ገጽ 23-7)
ቁ. 2፦ ኢያሱ 11:6-15
ቁ. 3፦ ቅዱሳን ጽሑፎች ስለ መለያየት ምን ይላሉ? (fy ገጽ 160-2 አን. 17-22)
ቁ. 4፦ ኢየሱስ ተአምራት ቢሠራም እንኳ አልተቀበሉትም (gt ምዕ. 48)
መጋቢት 20 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 14-17
ቁ. 1፦ ‘እንደኛው ዓይነት ስሜት የነበራቸው’ ታማኝ ሰዎች (w98 3/1 ገጽ 26-9)
ቁ. 2፦ ኢያሱ 15:1-12
ቁ. 3፦ በእርጅና ዘመንም ተደጋግፎ መኖር (fy ገጽ 163-5 አን. 1-9)
ቁ. 4፦ በገሊላ የተካሄደ ሦስተኛ የስብከት ዙር (gt ምዕ. 49)
መጋቢት 27 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 18-20
ቁ. 44 (105) [ሆሴዕ 3-14]
ቁ. 1፦ ኢየሱስ ምድር ላይ ያሳለፋቸውን የመጨረሻ ቀናት በዓይነ ሕሊና መመልከት (w98 3/15 ገጽ 3-9)
ቁ. 2፦ ኢያሱ 18:1-10
ቁ. 3፦ የትዳርን ማሰሪያ እንደ አዲስ ማጠናከር (fy ገጽ 166-7 አን. 10-13)
ቁ. 4፦ ደቀ መዛሙርቱን ለሚደርስባቸው ስደት ማዘጋጀት (gt ምዕ. 50)
ሚያዝያ 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 21-24
ቁ. 1፦ ኢያሱ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 45-6 አን. 21-4)
ቁ. 2፦ ኢያሱ 21:43-22:8
ቁ. 3፦ በልጅ ልጆቻችሁ ተደሰቱ፤ እንዲሁም ዕድሜያችሁ እየገፋ ሲሄድ ከሚያስከትለው ሁኔታ ጋር ራሳችሁን አስማሙ (fy ገጽ 167-70 አን. 14-19)
ቁ. 4፦ የልደት ቀን ሲከበር የተፈጸመ ነፍስ ግድያ (gt ምዕ. 51)
ሚያዝያ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መሳፍንት 1-4
ቁ. 1፦ የመሳፍንት መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 46-7 አን. 1-7)
ቁ. 2፦ መሳፍንት 3:1-11
ቁ. 3፦ የትዳር ጓደኛችሁን በሞት ማጣታችሁ የሚያስከትልባችሁን ሐዘን መቋቋም (fy ገጽ 170-2 አን. 20-5)
ቁ. 4፦ ኢየሱስ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን በተአምር መገበ (gt ምዕ. 52)
ሚያዝያ 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መሳፍንት 5-7
ቁ. 1፦ ኢየሱስ ለ70ዎቹ ከሰጠው መመሪያ ትምህርት ማግኘት (w98 3/1 ገጽ 30-1)
ቁ. 2፦ መሳፍንት 5:24-31
ቁ. 3፦ አረጋውያን ወላጆችን ማክበር የሚቻልባቸው ክርስቲያናዊ መንገዶች (fy ገጽ 173-5 አን. 1-5)
ቁ. 4፦ ኢየሱስ በውኃ ላይ ሲራመድ (gt ምዕ. 53)
ሚያዝያ 24 የጽሑፍ ክለሳ። ከዘዳግም 4 እስከ መሳፍንት 7 ያለውን ጨርሱ
ግንቦት 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መሳፍንት 8-10
ቁ. 1፦ የሌሎችን ሰብዓዊ ክብር ጠብቁ (w98 4/1 ገጽ 28-31)
ቁ. 2፦ መሳፍንት 9:7-21
ቁ. 3፦ ፍቅርና አሳቢነት አሳዩ (fy ገጽ 175-8 አን. 6-14)
ቁ. 4፦ ከሰማይ የወረደ እንጀራ—ከማን የተላከ ስጦታ ነው? (gt ምዕ. 54)
ግንቦት 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መሳፍንት 11-14
ቁ. 37 (82) [ማቴዎስ 1-8]
ቁ. 1፦ በርናባስ፣ “የመጽናናት ልጅ” (w98 4/15 ገጽ 20-3)
ቁ. 2፦ መሳፍንት 13:2-10, 24
ቁ. 3፦ ብርታት ለማግኘት ምንጊዜም ይሖዋን ተጠባበቁ (fy ገጽ 179-82 አን. 15-21)
ቁ. 4፦ ብዙዎች ኢየሱስን መከተል ያቆሙበት ምክንያት (gt ምዕ. 55)
ግንቦት 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መሳፍንት 15-18
ቁ. 9 (26) [ማቴዎስ 9-14]
ቁ. 1፦ ያለ ሠራዊት የተገኘ ዓለም አቀፍ ደኅንነት (w98 4/15 ገጽ 28-30)
ቁ. 2፦ መሳፍንት 17:1-13
ቁ. 3፦ ለአምላክ ያደሩ መሆንንና ራስ መግዛትን አዳብሩ (fy ገጽ 183-4 አን. 1-5)
ቁ. 4፦ ሰውን የሚያረክሰው ምንድን ነው? (gt ምዕ. 56)
ግንቦት 22 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መሳፍንት 19-21
ቁ. 18 (42) [ማቴዎስ 15-21]
ቁ. 1፦ መሳፍንት—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 50 አን. 26-8)
ቁ. 2፦ መሳፍንት 19:11-21
ቁ. 3፦ የራስነትን ሥልጣን በተመለከተ ያለው ተገቢ አመለካከት (fy ገጽ 185-6 አን. 6-9)
ቁ. 4፦ ኢየሱስ ለተጨነቁ ሰዎች ያሳየው ርኅራኄ (gt ምዕ. 57)
ግንቦት 29 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሩት 1-4
ቁ. 43 (98) [ማቴዎስ 22-26]
ቁ. 1፦ የሩት መጽሐፍ ማስተዋወቂያና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 51-3 አን. 1-3, 9-10)
ቁ. 2፦ ሩት 3:1-13
ቁ. 3፦ ፍቅር በቤተሰብ ውስጥ የሚጫወተው ትልቅ ሚና (fy ገጽ 186-7 አን. 10-12)
ቁ. 4፦ ኢየሱስ የተፈጠረውን አለመግባባት ፈታ (gt ምዕ. 58)
ሰኔ 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 1-3
ቁ. 1፦ የ1 ሳሙኤል መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 53-4 አን. 1-6)
ቁ. 2፦ 1 ሳሙኤል 1:9-20
ቁ. 3፦ የአምላክን ፈቃድ በቤተሰብ መልክ ማድረግ (fy ገጽ 188-9 አን. 13-15)
ቁ. 4፦ በእርግጥ ኢየሱስ ማን ነው? (gt ምዕ. 59)
ሰኔ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 4-7
ቁ. 38 (85) [ማርቆስ 5-9]
ቁ. 1፦ ይሖዋ ማን ነው? (w98 5/1 ገጽ 5-7)
ቁ. 2፦ 1 ሳሙኤል 4:9-18
ቁ. 3፦ ቤተሰብና የወደፊት ዕጣችሁ (fy ገጽ 190-1 አን. 16-18)
ቁ. 4፦ የክርስቶስ መንግሥታዊ ክብር አጭር እይታ (gt ምዕ. 60)
ሰኔ 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 8-11
ቁ. 69 (160) [ማርቆስ 10-14]
ቁ. 1፦ ንጹህ አቋም መጠበቅ ወሮታ አስገኘ (w98 5/1 ገጽ 30-1)
ቁ. 2፦ 1 ሳሙኤል 8:4-20
ቁ. 3፦ td 14መ መጽሐፍ ቅዱስ ኃጢአት ስለ ፈጸሙ መላእክት ምን ይናገራል?
ቁ. 4፦ እምነት ያለው ኃይል (gt ምዕ. 61)
ሰኔ 26 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 12-14
ቁ. 1፦ ሀብት ደስተኛ ሊያደርግህ ይችላልን? (w98 5/15 ገጽ 4-6)
ቁ. 2፦ 1 ሳሙኤል 14:1-14
ቁ. 3፦ td 17ሀ ምድር የተፈጠረችው ገነት እንድትሆን ነበር
ቁ. 4፦ ስለ ትሕትና የተሰጠ ትምህርት (gt ምዕ. 62)
ሐምሌ 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 15-17
ቁ. 4 (8) [ሉቃስ 4-8]
ቁ. 1፦ ኤውንቄና ሎይድ—በዓርአያነት የሚጠቀሱ አስተማሪዎች (w98 5/15 ገጽ 7-9)
ቁ. 2፦ 1 ሳሙኤል 16:4-13
ቁ. 3፦ td 17ሐ ምድር ሕይወት አልባ አትሆንም
ቁ. 4፦ ሌሎችን ከማሰናከል ተጠበቁ (gt ምዕ. 63)
ሐምሌ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 18-20
ቁ. 67 (156) [ሉቃስ 9-12]
ቁ. 1፦ በማሳመን ችሎታ ተጠቅማችሁ ልብ ንኩ (w98 5/15 ገጽ 21-3)
ቁ. 2፦ 1 ሳሙኤል 19:1-13
ቁ. 3፦ td 19ሀ ሐሰተኛ ነቢያትን ለይተህ ማወቅ ትችላለህ?
ቁ. 4፦ ስለ ይቅር ባይነት የተሰጠ ትምህርት (gt ምዕ. 64)
ሐምሌ 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 21-24
ቁ. 13 (33) [ሉቃስ 13-19]
ቁ. 1፦ የቤተሰብ ኃላፊነታችሁን ተሸከሙ (w98 6/1 ገጽ 20-3)
ቁ. 2፦ 1 ሳሙኤል 24:2-15
ቁ. 3፦ td 22ሀ መንፈሳዊ ፈውስ ምን ያህል ጠቃሚ ነው?
ቁ. 4፦ ወደ ኢየሩሳሌም የተደረገ ምስጢራዊ ጉዞ (gt ምዕ. 65)
ሐምሌ 24 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 25-27
ቁ. 62 (146) [ሉቃስ 20-24]
ቁ. 1፦ ትክክለኛ ፍርድ—መቼና እንዴት? (w98 6/15 ገጽ 26-9)
ቁ. 2፦ 1 ሳሙኤል 25:23-33
ቁ. 3፦ td 22ለ የአምላክ መንግሥት—ዘላቂ አካላዊ ፈውስ የሚገኝበት ዝግጅት
ቁ. 4፦ የዳስ በዓል ሲከበር የተፈጠረ አደጋ (gt ምዕ. 66)
ሐምሌ 31 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 28-31
ቁ. 21 (46) [ዮሐንስ 1-6]
ቁ. 1፦ 1 ሳሙኤል—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 57-8 አን. 27-35)
ቁ. 2፦ 1 ሳሙኤል 31:1-13
ቁ. 3፦ td 22ሐ ዘመናዊ የእምነት ፈውስ ከአምላክ የመነጨ አይደለም
ቁ. 4፦ የፖሊስ መኮንኖቹ ኢየሱስን ሳያስሩ የቀሩበት ምክንያት (gt ምዕ. 67)
ነሐሴ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 1-4
ቁ. 97 (217) [ዮሐንስ 7-11]
ቁ. 1፦ የ2 ሳሙኤል መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 59 አን. 1-5)
ቁ. 2፦ 2 ሳሙኤል 2:1-11
ቁ. 3፦ td 22መ በልሳን መናገር የአምላክን ሞገስ ለማግኘት ማረጋገጫ ነውን?
ቁ. 4፦ ኢየሱስ መለኮታዊ ምንጭ ያለው መሆኑና ወደፊት በሰማይ የሚኖረው ሕይወት (gt ምዕ. 68 አን. 1-11)
ነሐሴ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 5-8
ቁ. 77 (174) [ዮሐንስ 12-18]
ቁ. 1፦ “በጠበበው በር ለመግባት ተጋደሉ” (w98 6/15 ገጽ 30-1)
ቁ. 2፦ 2 ሳሙኤል 7:4-16
ቁ. 3፦ td 23ለ ወደ ሰማይ የሚሄዱት እነማን ናቸው?
ቁ. 4፦ ሰዎችን ነፃ የሚያወጣው እውነት (gt ምዕ. 68 አን. 12-16)
ነሐሴ 21 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 9-12
ቁ. 1፦ መልካም ባልንጀሮች ሁኑ (w98 7/1 ገጽ 30-1)
ቁ. 2፦ 2 ሳሙኤል 11:2-15
ቁ. 3፦ td 24ለ ሲኦል የማቃጠያ ቦታ አይደለም
ቁ. 4፦ የአባትነት ጥያቄ (gt ምዕ. 69)
ነሐሴ 28 የጽሑፍ ክለሳ። ከመሳፍንት 8 እስከ 2 ሳሙኤል 12 ያለውን ጨርሱ
ቁ. 79 (177) [ሥራ 5-10]
መስከረም 4 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 13-15
ቁ. 82 (183) [ሥራ 11-16]
ቁ. 1፦ ልጆቻችሁ በሕይወታቸው ጥሩ ጅምር እንዲኖራቸው አድርጉ (w98 7/15 ገጽ 4-6)
ቁ. 2፦ 2 ሳሙኤል 13:20-33
ቁ. 3፦ td 24ሐ እሳት የመደምሰስ ምሳሌ ነው
ቁ. 4፦ ዓይነ ስውር ሆኖ የተወለደ ሰው መፈወስ (gt ምዕ. 70)
መስከረም 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 16-18
ቁ. 52 (129) [ሥራ 17-22]
ቁ. 1፦ አንድ ክርስቲያን ከቀብር ሥነ ሥርዓት ጋር ለተያያዙ ልማዶች የሚኖረው አመለካከት (w98 7/15 ገጽ 20-4)
ቁ. 2፦ 2 ሳሙኤል 16:5-14
ቁ. 3፦ td 24ሠ የሀብታሙ ሰውና የአልዓዛር ታሪክ ዘላለማዊ ሥቃይ መኖሩን አያረጋግጥም
ቁ. 4፦ አንድ ለማኝ ፈሪሳውያንን ግራ አጋባ (gt ምዕ. 71)
መስከረም 18 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 19-21
ቁ. 1፦ ሕሊናህን ልታምነው ትችላለህ? (w98 9/1 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ 2 ሳሙኤል 20:1, 2, 14-22
ቁ. 3፦ td 25ለ ክርስቲያኖች ለበዓላት ያላቸው አመለካከት
ቁ. 4፦ ኢየሱስ ሰባዎቹን ላከ (gt ምዕ. 72)
መስከረም 25 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 22-24
ቁ. 43 (98) [ሮሜ 2-9]
ቁ. 1፦ 2 ሳሙኤል—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 63 አን. 28-31)
ቁ. 2፦ 2 ሳሙኤል 23:8-17
ቁ. 3፦ td 26ሀ በምስሎች መጠቀም ለአምላክ ክብር አያመጣም
ቁ. 4፦ በእርግጥ ባልንጀራችን ማን ነው? (gt ምዕ. 73)
ጥቅምት 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 1-2
ቁ. 1፦ የ1 ነገሥት መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 64-5 አን. 1-5)
ቁ. 2፦ 1 ነገሥት 2:1-11
ቁ. 3፦ td 26ለ የምስል አምልኮ የሚያስከትላቸው መዘዞች
ቁ. 4፦ ኢየሱስ ለማርታ የሰጠው ምክር (gt ምዕ. 74 አን. 1-5)
ጥቅምት 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 3-6
ቁ. 45 (106) [1 ቆሮንቶስ 4-13]
ቁ. 1፦ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ለሚገቡ ነገሮች ቅድሚያ ስጡ (w98 9/1 ገጽ 19-21)
ቁ. 2፦ 1 ነገሥት 4:21-34
ቁ. 3፦ td 26ሐ መመለክ ያለበት ይሖዋ ብቻ ነው
ቁ. 4፦ በጸሎት የመጽናት አስፈላጊነት (gt ምዕ. 74 አን. 6-9)
ጥቅምት 16 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 7-8
ቁ. 49 (114) [1 ቆሮንቶስ 14–2 ቆሮንቶስ 7]
ቁ. 1፦ በሹማምንት ፊት መመሥከር (w98 9/1 ገጽ 30-1)
ቁ. 2፦ 1 ነገሥት 7:1-14
ቁ. 3፦ td 27ለ ሁሉም ሃይማኖቶች ጥሩ ናቸውን?
ቁ. 4፦ ኢየሱስ ላከናወናቸው ተዓምራት የተሰጠ ተገቢ ምላሽ (gt ምዕ. 75)
ጥቅምት 23 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 9-11
ቁ. 56 (135) [2 ቆሮንቶስ 8–ገላትያ 4]
ቁ. 1፦ ክርስቲያኖች ጥሎሽን በተመለከተ ያላቸው አመለካከት (w98 9/15 ገጽ 24-7)
ቁ. 2፦ 1 ነገሥት 11:1-13
ቁ. 3፦ td 29ሐ የአምላክን መኖር በተመለከተ ያለው እውነታ
ቁ. 4፦ ኢየሱስ ፈሪሳውያንንና ሕግ ዐዋቂዎችን አጋለጠ (gt ምዕ. 76)
ጥቅምት 30 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 12-14
ቁ. 1፦ አምላክ ለአንተ እውን ነውን? (w98 9/15 ገጽ 21-3)
ቁ. 2፦ 1 ነገሥት 13:1-10
ቁ. 3፦ td 29ረ ሁሉም ሰው የሚያመልከው አንዱን አምላክ አይደለም
ቁ. 4፦ ኢየሱስ ለቀረበለት የውርስ ጥያቄ መልስ ሰጠ (gt ምዕ. 77)
ኅዳር 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 15-17
ቁ. 50 (123) [ፊልጵስዩስ 3–1 ተሰሎንቄ 5]
ቁ. 1፦ በመንፈሳዊ እድገት ማድረጋችሁን ቀጥሉ! (w98 10/1 ገጽ 28-31)
ቁ. 2፦ 1 ነገሥት 15:9-24
ቁ. 3፦ td 31ለ ኢየሱስ ክርስቶስ—የአምላክ ልጅና በእርሱ የተሾመ ንጉሥ ነው
ቁ. 4፦ ኢየሱስ የእርሱን መመለስ በንቃት እንዲጠባበቁ ደቀ መዛሙርቱን አሳሰበ (gt ምዕ. 78)
ኅዳር 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 18-20
ቁ. 39 (86) [2 ተሰሎንቄ 1–2 ጢሞቴዎስ 3]
ቁ. 1፦ ቅራኔዎችን በሰላማዊ መንገድ ፍቱ (w98 11/1 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ 1 ነገሥት 20:1, 13-22
ቁ. 3፦ td 31ሠ ለመዳን በኢየሱስ ማመን ብቻ በቂ ነውን?
ቁ. 4፦ የጠፋ ሕዝብ፤ ግን ሁሉም አይደለም (gt ምዕ. 79 አን. 1-5)
ኅዳር 20 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 21-22
ቁ. 61 (144) [2 ጢሞቴዎስ 4–ዕብራውያን 7]
ቁ. 1፦ 1 ነገሥት—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 68-9 አን. 23-6)
ቁ. 2፦ 1 ነገሥት 22:29-40
ቁ. 3፦ td 33ሐ የአምላክ መንግሥት መግዛት የሚጀምረው የክርስቶስ ጠላቶች ገና በሕይወት እያሉ ነው
ቁ. 4፦ በሰንበት መፈወስን የተቃወሙትን ሰዎች ስህተት ማጋለጥ (gt ምዕ. 79 አን. 6-9)
ኅዳር 27 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 1-3
ቁ. 1፦ የ2 ነገሥት መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 69 አን. 1-4)
ቁ. 2፦ 2 ነገሥት 2:15-25
ቁ. 3፦ td 34ሀ “የዓለም ፍጻሜ” ሲባል ምን ማለት ነው?
ቁ. 4፦ የበጎች በረቶችና መልካሙ እረኛ (gt ምዕ. 80)
ታኅሣሥ 4 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 4-6
ቁ. 1፦ ከሲሞናዊነት ተጠበቁ (w98 11/15 ገጽ 28)
ቁ. 2፦ 2 ነገሥት 5:20-27
ቁ. 3፦ td 36ለ የዘላለም ሕይወት እንዲሁ ሕልም አይደለም
ቁ. 4፦ ኢየሱስን ለመግደል የሞከሩበት ምክንያት (gt ምዕ. 81)
ታኅሣሥ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 7-9
ቁ. 1፦ ገንዘብ ስናበድርም ሆነ ስንበደር ልንከተላቸው የሚገቡ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች (w98 11/15 ገጽ 24-7)
ቁ. 2፦ 2 ነገሥት 7:1, 2, 6, 7, 16-20
ቁ. 3፦ td 36ሠ በምድር ላይ የዘላለም ሕይወት የሚያገኙ ሰዎች ቁጥር የተወሰነ አይደለም
ቁ. 4፦ የማይድኑት እነማን ናቸው? (gt ምዕ. 82 አን. 1-6)
ታኅሣሥ 18 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 10-12
ቁ. 81 (181) [ራእይ 2-12]
ቁ. 1፦ የኢየሱስ ልደት እውነተኛው ታሪክ (w98 12/15 ገጽ 5-9)
ቁ. 2፦ 2 ነገሥት 11:1-3, 9-16
ቁ. 3፦ td 38ሐ ክርስቲያኖች የራስነት መሠረታዊ ሥርዓት ማክበር አለባቸው
ቁ. 4፦ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እየተጓዘ ሳለ ያከናወናቸው ነገሮች (gt ምዕ. 82 አን. 7-11)
ታኅሣሥ 25 የጽሑፍ ክለሳ። ከ2 ሳሙኤል 13 እስከ 2 ነገሥት 12 ያለውን ጨርሱ
ቁ. 97 (217) [ራእይ 13-22]