የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም
ታኅሣሥ 11 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 24 (50)
8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ጉባኤው ታላቅ ሰው የተባለው መጽሐፍ ካለው በአገልግሎት ላይ በጥሩ ሁኔታ ማስተዋወቅ የሚቻልበትን መንገድ አሳይ።
15 ደቂቃ:- “ቀኑን ሙሉ ይሖዋን ፍሩ።” በጥር 8, 1998 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ገጽ 26 ላይ አምላክን ስለመፍራት የተጠቀሰውን ማብራሪያ ጨምረህ አቅርብ። ይሖዋን መፍራት የሚያስገኘውን ጥቅም ጎላ አድርገህ ተናገር።
22 ደቂቃ:- “የእኩዮች ተጽዕኖ እና የስብከት መብትህ።” በንግግርና በቃለ ምልልስ የሚቀርብ። የእኩዮች ተጽዕኖ ቢያጋጥማቸውም በስብከቱ ሥራ በትጋት መካፈላቸውን መቀጠል ለቻሉ ግለሰቦች ቃለ ምልልስ አድርግ።
መዝሙር 27 (57) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 18 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 65 (152)
15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። በሃይማኖት ምክንያት እስካልተደረገ ድረስ ክርስቲያናዊ አመጣጥ በሌላቸው በዓሎች ላይ መካፈሉ ስህተት ነውን? ለሚለው ጥያቄ መልስ ስጥ።—ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 178-80 ላይ ያለውን ተመልከት።
12 ደቂቃ:- “የ2001 ቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት።” በትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች የሚቀርብ ንግግር። ሁሉም ሳምንታዊውን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም ተከታትለው እንዲያነቡ እንዲሁም በትምህርት ቤቱ የሚሰጣቸውን ክፍል በደንብ ለማቅረብ እንዲተጉ አበረታታ።
18 ደቂቃ:- “በድፍረት ትሰብካላችሁን?” በርዕሱ ውስጥ በሚገኙ ጥቅሶች ላይ ሐሳብ ስጥ። አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ገጽ 86 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ ተጠቅመህ በጣም ደፋር መሆን የምንችለውና በመስክ አገልግሎት ላይ ውጤታማ መሆን የምንችለው እንዴት እንደሆነ ተናገር።
መዝሙር 71 (163) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 86 (193)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አድማጮች በስብከቱ እንቅስቃሴያቸው በቅርብ ያገኙት ተሞክሮ ካለ እንዲናገሩ ጋብዝ። በጥር ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። በሕይወት ተርፎ እና መንግሥትህ ትምጣ የተባሉትን መጻሕፍት አሳያቸውና እንዴት ማበርከት እንደሚቻል ሐሳብ ስጥ። (በሕይወት መትረፍ ገጽ 5 ላይ የሚገኘውን ሥዕል፤ መንግሥትህ ትምጣ ገጽ 25 ላይ የሚገኘውን ሣጥን እና ገጽ 148-9 ላይ የሚገኘውን ሥዕል መጠቀም ትችላለህ።)
10 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
25 ደቂቃ:- “የመንግሥት አዳራሻችሁን በመንከባከብ ረገድ የአንተ ድርሻ ምንድን ነው?” የሚለውን በጥያቄና መልስ በሚደረግ ውይይት አቅርበው።
መዝሙር 64 (151) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 81 (181)
8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ጉባኤያችሁ በአዲሱ ዓመት ስብሰባ የሚያደርግበትን ሰዓት የሚቀይር ከሆነ እያንዳንዱ ሰው አዲስ በተቀየረው ሰዓት አዘውትሮ እንዲገኝ በደግነት አበረታታ። ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁ እንዲሁም ፍላጎት ላላቸው ሌሎች ሰዎች ስለተደረገው ለውጥ ንገሯቸው። እንዲሁም አዲሱን የስብሰባ ፕሮግራም የሚያሳየውን የመጋበዣ ወረቀት መጠቀም ጀምሩ። የአገሪቱንና የጉባኤውን የመስከረም ወር አገልግሎት ሪፖርት አስመልክተህ ሐሳብ ስጥ። አስፋፊዎች የታኅሣሥ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አሳስባቸው።
17 ደቂቃ:- ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ መዘጋጀት የሚቻለው እንዴት ነው? አንድ አባት በአገልግሎት ላይ ይበልጥ ውጤታማ መሆን የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ከቤተሰቡ ጋር ይወያያል። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን በሙሉ ተከታትሎ መርዳት ያለብን ለምን እንደሆነ የሚገልጹ ቅዱስ ጽሑፋዊ ማስረጃዎችን ጠበቅ አድርጎ ይናገራል። በሐምሌ 1, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 22 አንቀጽ 18 ላይ የሚገኙትን መመሪያዎች በመጠቀም ተመላልሶ መጠየቆችን ለማድረግ ዝግጅት ያደርጋሉ። የቤተሰቡ አባላት በሙሉ ተመላልሶ መጠየቅ ሊደረግላቸው የሚገባቸው ሰዎች እንዳገኙ ይናገራሉ። እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል በመጀመሪያ ቀን ያገኘውን ምላሽ ይናገርና የቀሩት ተመላልሶ መጠየቅ ሲደረግ የሚጠቀምበትን ሐሳብና ጥቅስ ይጠቁሙታል። አንዳንዶቹ ጥሩ ማስታወሻ መያዝ አስፈላጊ እንደሆነ ጎላ አድርገው የሚገልጹ ሲሆን ማስታወሻ ደብተራቸው እንዳይጠፋባቸው ምን ማድረግ እንደሚችሉ ይናገራሉ። ሌሎቹ ደግሞ የያዙትን ማስታወሻ ዘወትር እንዴት እንደሚከልሱና ተመላልሶ መጠየቅ የሚያደርጉበትን ጊዜ እንደሚመድቡ ይገልጻሉ። አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ከተባለው ብሮሹር ላይ ውጤታማ በሆነ መንገድ ሊጠቀሙባቸው የሚችሉትን ነጥቦች ይመርጣሉ። ወላጆች አንደኛው ልጅ በሚቀጥለው ጊዜ ተመላልሶ መጠየቅ ሲያደርግ ምን እንደሚል እንዲያሳይ ያደርጋሉ። በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ ቁርጥ ያለ ቀን ይመድባሉ።
20 ደቂቃ:- ከግንቦት 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ ላይ “ይሖዋን የሚያስከብር አስደሳች ሠርግ” የሚለውን በጥያቄና መልስ ተወያዩበት። በውይይቱ ውስጥ ተስማሚ በሚሆንባቸው ቦታዎች ላይ ስትደርሱ የሚከተሉትን ነጥቦች አጉሉ:- 1) የጥሪ ወረቀት የሚዘጋጅ ከሆነ ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ ሰጥተው መግለጽ የሚኖርባቸው የጋብቻ ንግግር የሚሰጥበትን ሰዓትና ቦታ መሆን አለበት። የቤተሰቡ አባላት በተለይ ደግሞ ራሳቸውን ለይሖዋ የወሰኑት የጋብቻ ንግግር የሚቀርብበትን ጊዜ ለሠርጉ የሚያስፈልገውን ምግብና ሌሎች ነገሮች ለማዘጋጀት ከመጠቀም ይልቅ በንግግሩ ላይ ለመገኘት ጥረት ማድረግ ያለባቸው ለምን እንደሆነ ጠይቃቸው። 2) የይሖዋ ምሥክር ያልሆኑ ሰዎች በጋብቻ ንግግር ላይ እንዲገኙ ሲጋበዙ ለሥነ ሥርዓቱ የሚስማማ ልብስ ለብሰው መምጣት እንደሚጠበቅባቸው መንገር ጥሩ ነው። ይህ ሁኔታ ለፎቶግራፍ አንሺዎችም ይሠራል። 3) እንደተጠቀሰው ፎቶግራፍ አንሺዎች ለሥነ ሥርዓቱ ተገቢ የሆነውን ልብስ ለብሰው መምጣት ይገባቸዋል። ፎቶግራፍ አንሺው ክራቫት ማሰር የሚኖርበት ሲሆን ጂንስ መልበስ የለበትም። ፎቶግራፍ አንሺዎች የተመልካቾችን እይታ እንዳይጋርዱ ወይም አድማጮችን እንዳያውኩ (ለምሳሌ ያህል ፍላሽ በተደጋጋሚ በመጠቀም) ከአስተናጋጆች የሚሰጣቸውን መመሪያ መከተል ይገባቸዋል። 4) በሠርግ ሥነ ሥርዓቶቻችን ላይ የመንግሥቱን ዜማዎችንም መጠቀም ይኖርብናል። የመንግሥቱን ዜማዎች በመንግሥት አዳራሽ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በግብዣ ሥነ ሥርዓትም ላይ መጠቀም ይቻላል። ሙዚቃው አድማጮች እርስ በርስ መደማመጥ እስኪቸገሩ ድረስ መጮኽ የለበትም። በሚያዝያ 15, 1984 እና ኅዳር 15, 1986 መጠበቂያ ግንብ እትሞች ላይ ስለ ሠርግ ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
መዝሙር 94 (212) እና የመደምደሚያ ጸሎት።