ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ታኅሣሥ:- ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት ወይም በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። ጥር:- ከ1986 በፊት የታተመ ማንኛውም ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ። እነዚህ መጽሐፎች የሌሏቸው ጉባኤዎች የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ (እንግሊዝኛ) የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት ይችላሉ። የካቲት:- ሕይወት እንዴት ተገኘ? በዝግመተ ለውጥ ወይስ በፍጥረት? (እንግሊዝኛ)፣ ራእይ —ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!፣ ወይም ጉባኤው ያለው ማንኛውም ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ። መጋቢት:- ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት ይደረጋል።
◼ ጉባኤዎች በቅርቡ ከሚልኩት የጽሑፍ ትእዛዝ ጋር የ2000 የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ጥራዞችን ማዘዝ መጀመር ይኖርባቸዋል። ጥራዞቹ በእንግሊዝኛና በፈረንሳይኛ ይገኛሉ። ጥራዞቹ ደርሰውን እስክንልክላችሁ ድረስ በጉባኤያችሁ የጽሑፍ መላኪያ ዝርዝር ላይ “በቅርቡ የሚደርስ” ተብሎ ይወጣል። ጥራዞች የሚገኙት በልዩ ትእዛዝ ነው።
◼ በ2001 የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው እሑድ ሚያዝያ 8 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ሲሆን በ2002 ደግሞ ሐሙስ መጋቢት 28 ይሆናል።