የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ግንቦት 13 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 16 (37)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ስለ መምህራን የሚናገረውን ንቁ! መጽሔት አስመልክቶ የወጣውን ማስታወቂያ አንድ ወላጅ አንድን መምህር ሄዶ በማነጋገር ይህን መጽሔት ሲያበረክትለት ከሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ ጋር አያይዘህ አቅርብ። ከዚያም በገጽ 4 ላይ ካሉት ሐሳቦች አንዱን በመጠቀም በቅርብ ጊዜ የወጣ አንድ መጠበቂያ ግንብ ሲበረከት የሚያሳይ ሌላ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ውይይት ለማስቆም “ሥራ አለብኝ” የሚል ሐሳብ ሲሰነዘር ምን ብሎ መመለስ እንደሚቻል አሳይ።—ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 19-20ን ተመልከት።
20 ደቂቃ፦ “የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ለወጣቶችም ለአዋቂዎችም አስፈላጊ ነው።” ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በጥቅምት 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 9-12 አንቀጽ 6-16 ላይ ያለውን ሐሳብ በጥያቄና መልስ በሚደረግ ውይይት ይሸፍናል። ዋና ዋናዎቹን ነጥቦችና ቁልፍ የሆኑትን ጥቅሶች እያስጨበጥህ እለፍ።
15 ደቂቃ፦ “ጥርጣሬ እምነትህን እንዲያጠፋ አትፍቀድ።” በሐምሌ 1, 2001 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 18-21 ላይ በሚገኘው ርዕስ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።
መዝሙር 43 (98) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 20 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 6 (13)
9 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
18 ደቂቃ፦ የመጠበቂያ ግንብ ጥናት መሪው በጥቅምት 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 15 ከአንቀጽ 9-13 ያለውን ሐሳብ “ጥናት የአምልኮ ክፍል ነው” በሚል ርዕስ በጥያቄና መልስ ያቀርበዋል። ሁሉም ለግል ጥናትና ለጉባኤ ዝግጅት ቅድሚያ እንዲሰጡ አበረታታቸው።
18 ደቂቃ፦ በሰኔ 15, 2001 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 9-12 ላይ ባለው “ወላጆች የሌላቸውን ልጆች እና መበለቶችን በመከራቸው መጠየቅ” የሚል ርዕስ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። ከጉባኤያችሁ ሁኔታ ጋር ተጣጥሞ ሊቀርብ ይችላል።
መዝሙር 75 (169) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 27 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 42 (92)
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የግንቦት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አሳስባቸው። በሕመም ወይም በሌሎች ችግሮች ምክንያት ያሰቡትን ያህል ማገልገል ያልቻሉትም አነስተኛም ቢሆን ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አበረታታቸው። በገጽ 4 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም አንድ በዕድሜ የጎለመሰ አስፋፊ በቅርብ ጊዜ የወጣ የመጠበቂያ ግንብ እትም አንድ ወጣት አስፋፊ ደግሞ በቅርብ የወጣ ንቁ! መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል በሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርቡ አድርግ። ከእያንዳንዱ ሠርቶ ማሳያ በኋላ በመግቢያችን ላይ እንዴት በቀላሉ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ መጠቀም እንደምንችል እንዲያስተውሉ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ “የጉባኤያችሁ የአገልግሎት ክልል ሰፊ ነውን?” የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በውይይት ያቀርበዋል። (የአገልግሎት ክልላቸው አነስተኛ የሆነ ጉባኤዎች በሰኔ 1999 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የወጣውን “ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት” የሚል ርዕስ መከለስ ይችላሉ።) ጉባኤው ምን ያህል የአገልግሎት ክልሎች እንዳሉትና ባለፈው ዓመት ምን ያህሉ እንደተሸፈነ ተናገር። የቀረቡትን ሐሳቦች ጉባኤው እንዴት ሊሠራባቸው እንደሚችል ግለጽ። ከመጋቢት ጀምሮ በተደረገው ዘመቻ ምን እንደተከናወነና ወደፊት ብዙም ያልተሠራባቸውን ክልሎች ለመሸፈን ምን እንደታቀደ ጥቀስ።
18 ደቂቃ፦ “ጥናት ለማስጀመር አምላክ ከእኛ የሚፈልገው በተባለው ብሮሹር እየተጠቀምክ ነው?” (ለዚህ ውይይት ሁሉም በጥር 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን ውስጥ ያለውን አባሪ ይዘው መምጣት አለባቸው።) አንድ ጥሩ ዝግጅት ያደረገ አስፋፊ አንቀጽ 3 ላይ ያለውን የናሙና አቀራረብ ተጠቅሞ ጥናት እንዴት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ በማድረግ ጀምር። ከዚያ በኋላ ጎላ ብለው የሚታዩትን የብሮሹሩን ገጽታዎች በመጥቀስ ጥናት ለማስጀመር በሚያስችል ግሩም መንገድ እንዴት እንደተዘጋጀ ተናገር። በጥር 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ ያሉትን አቀራረቦች መከለሱ ያለውን ጠቀሜታ ግለጽ። አድማጮች የትኞቹን አቀራረቦች ውጤታማ ሆነው እንዳገኟቸው ጠይቅ። መጀመሪያ ላይ የቀረበው ሠርቶ ማሳያ በድጋሚ እንዲቀርብ በማድረግ ደምድም።
መዝሙር 53 (130) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 3 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 79 (177)
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሪፖርት ስንመልስ ተመላልሶ መጠየቆችንና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን የምንሞላው እንዴት እንደሆነ ግልጽ ለማድረግ ጥቂት ደቂቃዎች ወስደህ አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት ከተባለው መጽሐፍ ከገጽ 102-3 ላይ ያሉትን ነጥቦች በምሳሌ እያስደገፍክ አቅርብ። አስፋፊዎች በመጋቢት በሚያዝያና በግንቦት ወር በረዳት ወይም በዘወትር አቅኚነት በመካፈላቸው ያገኟቸውን በረከቶች እንዲናገሩ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ ማመራመር መጽሐፍ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን የሚጠቀመው ለምንድን ነው? አጠር ያለ ንግግር ካደረግክ በኋላ ከአድማጮች ጋር በውይይት አቅርበው። ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 8 አንቀጽ 2ን አንብብና መጽሐፍ ቅዱስ በአገልግሎታችን ጉልህ ስፍራ ሊኖረው የሚገባው ለምንና እንዴት እንደሆነ ግለጽ። በገጽ 6 ላይ የተዘረዘሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ምኅጻረ ቃላት ጥቀስና ከሌሎች ትርጉሞች የተወሰዱ ጥቅሶችን የምንጠቀመው ለምን እንደሆነ ተናገር። በጥቅምት 1, 1997 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 16 አንቀጽ 2 እና ገጽ 20 አንቀጽ 15 ላይ በቀረቡት ሊታሰብባቸው የሚገቡ ነጥቦች ላይ ተወያዩ። በማመራመር መጽሐፍ ውስጥ ያሉትን “ሐዋርያዊ ተተኪነት፣” “ምስሎች” እና “ሥላሴ” የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችን በመጠቀም አድማጮች የተለያዩ ትርጉሞችን ማወዳደር እውነትን በማስተማር ረገድ ጠቃሚ ሊሆን የሚችለው እንዴት እንደሆነ በምሳሌ እንዲያስረዱ ጋብዝ።
15 ደቂቃ፦ “እምነታችን ለመልካም ሥራ ያነሳሳናል።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በአንቀጽ 2 ላይ ስትወያዩ ቀናተኛ ከሆነ አንድ ምሥክር ጋር አጠር ያለ ቃለ ምልልስ አድርግ። አስፋፊው/ዋ ለሌሎች መመስከር እምነታቸውን የሚያሳይም የሚያጠናክርም የሆነው እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ አድርግ።
መዝሙር 26 (56) እና የመደምደሚያ ጸሎት።