ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ነሐሴ 29, 2005 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከሐምሌ 4 እስከ ነሐሴ 29, 2005 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-7ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. ስለ ተስፋችን ለሰዎች በምንናገርበት ጊዜ “[“ምክንያታዊነታችሁ፣” NW] በሁሉ ዘንድ የታወቀ ይሁን” የሚለውን ምክር ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? እንዲህ ማድረጋችን አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድን ነው? (ፊልጵ. 4:5፤ ያዕ. 3:17 NW) [be ገጽ 251 አን. 1-3, ሣጥኑ]
2. ምክንያታዊ መሆን የሚያስፈልግበትን ጊዜ ማወቃችን ከሰዎች ጋር ጥሩ ውይይት ማድረግ እንድንችል የሚረዳን እንዴት ነው? [be ገጽ 253 አን. 1-2]
3. ከሰዎች ጋር ስንወያይ በጉዳዩ ላይ እንዲያመዛዝኑ ለመርዳት ጥያቄዎችን ጥሩ አድርጎ መጠቀም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? [be ገጽ 253 አን. 3-4]
4. ንግግራችንን አሳማኝ ለማድረግ የትኞቹን ነጥቦች ልብ ልንል ይገባል? [be ገጽ 255 አን. 1-4, ሣጥኑ፤ ገጽ 256 አን. 1, ሣጥኑ]
5. የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ እውነት መሆኑን ለሰዎች ለማስረዳት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆኑ ማስረጃዎችን ለመጠቀም ካሰብን ምን ነገሮችን ልናስታውስ ይገባል? [be ገጽ 256 አን. 3-5, ሣጥኑ]
ክፍል ቁጥር 1
6. ኢየሱስ በምድር ላይ እንደኖረ የሚያረጋግጥ ምን ግልጽ ማስረጃ አለ? [w03 6/15 ገጽ 4-7]
7. ‘የቅኖች አፍ የሚታደጋቸውና’ የጻድቃን ቤት ‘ጸንቶ የሚኖረው’ እንዴት ነው? (ምሳሌ 12:6, 7) [w03 1/15 ገጽ 30 አን. 1-3]
8. መጽሐፍ ቅዱስ አድርግ፣ አታድርግ የሚሉ ዝርዝር ደንቦችን የያዘ ባለመሆኑ ‘የጌታ ፈቃድ ምን እንደሆነ ማስተዋል’ የምንችለው እንዴት ነው? (ኤፌ. 5:17) [w03 12/1 ገጽ 21 አን. 3 እስከ ገጽ 22 አን. 3]
9. ድህነትን ወይም አስቸጋሪ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታን ለመቋቋም የትኞቹን የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች ተግባራዊ ማድረግ ይጠቅማል? [w03 8/1 ገጽ 5 አን. 2-5]
10. በነጻ በመስጠት ረገድ ይሖዋ የተወልን ምሳሌ እኛም ምን እንድናደርግ ሊያነሳሳን ይገባል? (ማቴ. 10:8) [w03 8/1 ገጽ 20-22]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ሰሎሞን በገነባው ቤተ መቅደስ መግቢያ ላይ የነበሩት ያቁም እና ቦዔዝ የተባሉ ሁለት ምሰሶዎች ምን ያመለክታሉ? (1 ነገ. 7:15-22) [1 ነገ. 7:21 የግርጌ ማስታወሻ፤ it-1 ገጽ 348 አን. 2]
12. ሰሎሞን በገሊላ የሚገኙ 20 ከተሞችን ለጢሮስ ንጉሥ ለኪራም መስጠቱ ከሙሴ ሕግ ጋር አይጋጭም? (1 ነገ. 9:10-13)
13. “የእግዚአብሔር ሰው” የተሰጠውን ትዕዛዝ በመጣስ ከፈጸመው ድርጊት ምን ትምህርት እናገኛለን? (1 ነገ. 13:1-25)
14. የይሁዳ ንጉሥ የነበረው አሳ ደፋር እንደነበረ ያሳየው እንዴት ነው? ከእርሱ ምሳሌስ ምን ትምህርት እናገኛለን? (1 ነገ. 15:11-13)
15. ከንጉሥ አክዓብና ከናቡቴ ጋር በተያያዘ የተፈጸመው ታሪክ ስለ ራስ ከሚገባው በላይ ማሰብ አደገኛ መሆኑን የሚያሳየው እንዴት ነው? (1 ነገ. 21:1-16)