መጋቢት 8 የሚጀምር ሳምንት
መጋቢት 8 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
lv ምዕ. 10 አን. 9-15፤ በገጽ 114 ላይ የሚገኘው ሣጥን
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 1-4
ቁ. 1፦ 1 ሳሙኤል 2:18-29
ቁ. 2፦ ኢየሱስ ክፉዎች ከሞቱ በኋላ እንደሚሠቃዩ አስተምሯል? (rs ገጽ 175 አን. 1)
ቁ. 3፦ ቅዱሳን መጻሕፍት ይሖዋ ለልጆች ፍቅር እንዳለው ይገልጻሉ
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ስትናገር ድምፅህ በደንብ ይሰማል? የአገልግሎት ትምህርት ቤት በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 109 አንቀጽ 2 ጀምሮ እስከ ምዕራፉ መጨረሻ ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።
20 ደቂቃ፦ “ከሁሉ ለላቀው የአምላክ ስጦታ አድናቆታችንን መግለጽ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። በአንቀጽ 3 ላይ ከተወያያችሁ በኋላ የመታሰቢያውን በዓል ልዩ የመጋበዣ ወረቀት ለማሰራጨት ጉባኤው ያደረገውን የመስክ አገልግሎት ስምሪት ዝግጅት ተናገር። አንድ ረዳት አቅኚ የመጋበዣ ወረቀቱን እንዴት ለሰዎች እንደሚሰጥ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ። ከዚያም ረዳት አቅኚ ለመሆን የትኞቹን ማስተካከያዎች ማድረግ እንዳስፈለገውና እንዲህ በማድረጉ ምን ጥቅም እንዳገኘ እንዲናገር ጋብዘው።